ኣማርኛ PDF (2015):

Calais booklet – Amharic

እንኳን ወደ ካሌ በደህና መጣችሁ !
ለስደተኞችና ለተዘዋዋሪዎች የተዘጋጀ የመረጃ መምሪያ
ድንበር የለሽ፤ እኛ ማን ነን?
እንኳን ወደ ካሌ በደህና መጣችሁ፤ ስለከተማዋ ገለፃ
ማህበራትና እንቅስቃሴዎች በካሌ
መብትዎን ይወቁ፤ እስራት በፈረንሳይ
እርግዝና በካሌ
በእንግሊዝ እና በሌሎች የአውሮፓ ሕብረት ሀገሮች ስለሚቀርቡ የጥገኝነት ጥያቄዎች ገለፃ
ደብሊን 3ኛ
በእንግሊዝ ሀገር ጥገኝነት ስለመጠየቅ
በተለይ የሚታዩ (ልዩ) ጉዳዮች፤ የስቃይ ሰለባዎች እና የተመሳሳይ ፆታ የወሲብ ባህሪ ያላቸዉ ወይም በእንግሊዘኛዉ ምህፃረ ቃል «ኤል፤ ጂ ፤ቢ፤ቲ፤ አይ፤ ኪው» በመባል የሚታወቁ ሰዎች ጉዳይ
አውሮፓ ዉስጥ ለመጓዝ የሚረዱ ጠቃሚ ምክሮች
ፈረንሳይ
ኔዘርላንድ
ጀርመን
ዴንማርክ
ቤልጅየም
ስዊድን
ኦስትሪያ

« ድንበር የለሾች » እነማን ናቸው ? ለምንድን ነው ይህን መምሪያ የሚሰጡኝ ?
እኛ (ድንበር የለሾች) በአንድ ቦታ ተወስኖ የማይቆይ ቡድን አባላት ስንሆን እ.አ.አ. ከ2009 ጀምሮ በካሌ እየሰራን ነው። ጥቂቶቻችን የምንኖረው በካሌ ነው። ሌሎች በተለያዩ አገራት ይሚኖሩ ሲሆን ወደ ካሌ የሚመጡት ለአጭር ግዜ ቆይታ ነው። እንደ ተቁርቋሪ እና ለለዉጥ እንደሚተጋ አካል፤ እኛ ማንኛውም ሰው በፈለገበት ቦታ እና ጥሩ ሕይወት መኖር ይገባዋል ብለን ስለምናምን በምንኖረበት እና በሌላም ቦታ የሚኖሩ ስደተኞችን እንደግፋቸዋለን። የመንቀሳቀስ መብት የማንኛውም ሰው መብት ነው ብለን እናምናለን፤ ስለሆነም በድንበሮች ያልታጠረ (ድንበር የለሽ) ዓለም እንዲኖር እንፈልጋለን። እናንተን ለመደገፍ ካሌን እና አውሮፓን በተመለከተ ጥቂት ጠቃሚ መረጃ ልንሰጣችሁ እንፈልጋለን። ወደ ምትፈልጉበት ቦታ ለመድረስ የምታደርጉት ጉዞ መልካም እና ከአደጋ ነፃ እንደሚሆን ተስፋ እናደርጋለን።
ድንበር የለሾች በካሌ ምን ይሠራሉ ?
ቀጥተኛ እርዳታ እናቀርባለን፤ የሕይወት መሠረታዊ ፍላጎቶችን እንደ ጥሩ ምግብ፣ መጠለያ እና የመንቀሳቀስ ነፃነት ከተነፈጉ ሰዎች ጋር አብረን እንሰራለን።
በዚህ ስራችን ገንዘብ አናገኝበትም፤ ከመንግሥት ወይም ከቤተ-ክርስቲያን ጋር አብረን አንሰራም። በዚህ መምሪያ ያልተካተተ ማንኛውም ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልጋችሁ ወይም ለተጨማሪ ማብራሪያ ጥያቄ ካላችሁ ከዚህ ቀጥሎ በተሰጠው አድራሻ ያግኙን።
ስልክ
07 53 47 51 59 (ፈረንሳይ ውስጥ ሁናችሁ ለምትደዉሉ)
00 33 75 34 75 159 (ከፈረንሳይ ውጭ ሁናችሁ ለምትደዉሉ)
ኢሜል አድራሻ calais_solidarity@riseup.net / calaisolidarity@gmail.com
ድህረ ገፅ https://calaismigrantsolidarity.wordpress.com

ስለካሌ ከተማ ገለፃ
እንኳን ወደ ካሌ በደህና መጣችሁ ! ካሌ 73,000 ነዋሪዎች ያላት መካከለኛ ስፋት ያላት ከተማ ስትሆን እንደ ኮኬል፣ ማርክ እና ሳንጋት ያሉ አጎራባች ከተሞች ጋር ሲደመር የአካባቢው ነዋሪዎች ቁጥር 105,000 ይደርሳል። ካሌ በሰሜን ፈረንሳይ ትገኛለች፤ ለቤልጅም ቅርብ ስትሆን ወደ እንግሊዝ አገር መሻገሪያም ነች።
ለረጅም ጊዜ ካሌ የእንግሊዝ ከተማ ነበረች። በአውሮፓ አህጉር እና በእንግሊዝ መካከል በጀልባ፤ ወይም ከ1994 እ.አ.አ ጀምሮ በውስጥ ለውስጥ የመተላለፊያ መስመር ዋነኛ የመሻገሪያ ቦታ ናት። አብዛኛው የከተማዋ ክፍል በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወድሞ የነበረ ሲሆን ግማሽ የሚሆነው ሕዝቧም በወቅቱ ከተማውን ለቆ መሄድ ግዴታ ሆኖበት ነበር።
ካሌ ከድሮ ጀምሮ የኢንዱስትሪ ከተማ ብትሆንም በተከታታይ ቀውሶች በከፍተኛ ደረጃ የተመታች እና ከ20 በመቶ የሚበልጠው ሕዝቧ ስራ እጥ ነው። ከሌላው የፈረንሳይ ክፍል ይልቅ አብዛኛው ሕዝቧ ወጣት የሆነ ከተማ ነች።
ሰደተኞች በካሌ
ሰደተኞች በካሌ ለብዙ ዓመታት ኑረዋል።በ1990ዎቹ የመጀመሪያ አመታት የምስራቅ አውሮፓ ኮሚኒስት መንግስታት ከወደቁ በኋላ ስደተኞች ከነዚህ ሀገራት ወደ ካሌ መምጣት ጀመሩ፤ እዚያም እንቅስቃሴያቸው በድንበር ጠባቂዎች ተገታ። ከ1990ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ የሚመጡ ስደተኞች በአብዛኛው በቀድሞዋ ዩጎዝላቪያ የነበረውን ጦርነት ሸሽተው የመጡ እና ልጆች ያላቸው ብዙ ቤተሰቦች የተካተቱባቸው ነበሩ።
ሕዝቡን በመቀስቀስ እና መንግስትን በማግባባት ማህበራት የሰደተኞች ማዕከል ለመክፈት ችለው ነበር። እ.አ.አ. በ1999 ከካሌ ውጭ ሳንጋት በሚባል ቦታ ለመጠለያ የሚሆን ትልቅ ሕንፃ ተሠራ። ይህ መጠለያ የሚተዳደረው በቀይ መስቀል ነበር። ለሶስት ዓመታት ያህል ብዙ ሺህ ሰዎችን አስጠልሏል።
እ.አ.አ. በ2002 የመንግስት ለውጥን ተከትሎ የሳንጋት ማዕከል ተዘጋ። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ መንግስት ማንኛውም ቋሚ ሰፈራ ወይም ለስደተኞች የሚደረግ ጥሩ አቀባበል እንደይደረግ ከልክሏል። መጠለያዎች በየጊዜው ሲፈርሱ ሰደተኞች ለመጠለያ ከያዙት ቦታ (ያለፍቃድ የተያዘ እንደመሆኑ) ተፈናቅለዋል።
ከጊዜ ብዛት ሰደተኞቹ የሚነሱባቸው/የሚመጡባቸዉ ሀገራት ተለውጧል፤ ኩርዶች፣ አፍጋናዊያን፣ ኢራናዊያን፣ ቪየትናማዊያን፣ አልባናዊያን፣ ሶሪያዊያን፤ ኤርትራዊያን፣ ሱዳናዊያን፣ ወዘተ።
በ2009 በካሌ የሚገኙት ስደተኞች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር በወቅቱ የመገናኛ ብዙኃንን ትኩረት ስቦ ነበር። መንግስት በወሰደዉ እርምጃ ካምፖችን እና ሕገወጥ የስደተኞች መጠለያዎችን አፈረሰ። ነገር ግን ምንም መፍትሔ አልሆነም፤ ስደተኞች አሁንም አሉ። አፍጋኒስታናዉያንን ጨምሮ ሁሉንም ስደተኞች ወደ መጡባቸው ሀገራት ለመመለስ የተደረጉ ሙከራዎች በፍርድ ቤት ክልከላ ምክንያት ሊሳኩ አልቻሉም።
ከ2009እ.ኤ.አ. ጀምሮ እጅግ ብዙ ሰዎች በካሌ የጥገኝነት ጥያቄ አቀርበዋል። ነገር ግን በመላ ፈረንሳይ የጥገኝነት ጥያቄዎች አቀባበል ሁኔታ እየከፋ ሄዷል። ከጥሩ የመኖሪያ ቤት ጀምሮ መሠረታዊ መብቶቻቸው እንዲከበሩላቸው ዘወትር ፍርድ ቤቶችን መጠየቅ አለባቸው።
በ2014(እ.ኤ.አ) በካሌ የጥገኝነት ፈላጊዎች ቁጥር እንደገና በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረ ሲሆን ከበፊቱ የበለጠ የመገናኛ ብዙኃንን ትኩረት ስቧል። ስደተኞች ባሉበት ቦታ የሚኖሩ አንዳንድ የአካባቢው ነዋሪዎች የስደተኞችን መኖር የሚቃወሙና ለጠብ የሚጋበዙ እየሆኑ መጥተዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ዘረኛ ቡድኖች (እንደ « ካሌን አናድን » የመሳሰሉት) ድጋፍ እያገኙ የመጡ ይመስላል። የአዲስ ስደተኞችን መድረስ ተከትሎ መንግስት « ዡል ፌሪ » ተብሎ የሚጠራ የቀን ማዕከል ከፍቷል ነገር ግን ከከተማ ውጭ በጣም ሩቅ ስለሆነ ከተማ ውስጥ ለሚቀሩት ችግራቸውን አይቀርፍም።

ድርጅቶች፣ ማህበራት እና እንቅስቃሴዎች በካሌ
ምግብ የት ማግኘት እችላለሁ ?
ዡል ፌሪ የቀን ማዕከል :-
በማንኛዉም ቀን ከ11 ሰዓት እስከ 2 ሰዓት ትኩስ/የሞቀ ሀላል የሚባል ምግብ አለ።
ችግሩ፥ እዚያ ለመድርስ መንገዱ ሩቅ እና አንዳንዴም ፖሊሶች ወይም « ፋሺስቶች » በመንገድ ላይ ያጋጥማሉ። ወደዚያ ሲሄዱ ለብቻ ከመሄድ ይልቅ በቡድን መሄድ ይመረጣል።

የተለያዩ ማህበራት ራሳችሁ ልታበስሉት የሚትችሉት ምግብ በሳምንት አንዴ ወይም ሁለቴ በአከባቢዉ ለሚገኙ ካምፖች በእርዳታ መልክ ይሰጣሉ። በተጨማሪም ብዙ ሱፐር ማርኬቶች ያልተበላሹ ምግቦችን ይጥላሉ። አንዳንዴ ከሱፐር ማርኬቶች ቀጥሎ በሚገኙ የቆሻሻ መጣያዎች ውስጥ እንዳንድ የሚበሉ ነገሮች ልታገኙ ትችላላችሁ።
ያመኛል፤ ህክምና የት ማግኘት እችላለሁ ?
የሆስፒታሉ ድንገተኛ ክፍል ማንኛውም አስቸኳይ የጤና እክል ያጋጠመውን ሰው ያክማል። የ « ፓስ » (PASS) ክሊኒክ (ከሆስፒታሉ የመኪና ማቆሚያ ቀጥሎ በስተግራ በኩል ያለው የቆርቆሮ (ብረት) ቤት ያለምንም የጤና ኢንሹራንስ ወይም ወረቀቶች ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ከሰዓት በኋላ ከ7 :30 እስከ 11 :30 ህሙማንን ያስተናግዳል።
ጥገኝነት ፈላጊዎች ዓለም አቀፍ የጤና ሽፋን መብት አላቸው (የጥገኝነት ጥያቄያችሁን የሚከታታለውን ማህበር ወይም ድርጅት ጠይቁ)።
ገላዬን የት መታጠብ እችላለሁ ?
በ’ፓስ’ ክሊኒክ (ከሆስፒታሉ የመኪና ማቆሚያ በስተግራ የሚገኘው የቆርቆሮ/ብረት ቤት)፤ ከቀኑ 7 :30 ላይ የሚደርሱ የመጀመሪያዎቹ 20 ወንዶች ገላቸውን እዚያ መታጠብ ይችላሉ።
በ « ዡል ፌሪ » የቀን ማዕከል ከቀኑ እስከ 9 ሰዓት ድረስ ባለው ጊዜ ገላችሁን መታጠብ ትችላላችሁ። ሳሙናና የማድረቂያ ፎጣ እነሱ ይሰጧችኋል። ነገር ግን አንድ ሰው በአራት ደቂቃ ውስጥ ታጥቦ መጨረስ ይኖርበታል።
የሴቶች ቤት :-በዚህ ቤት ውስጥ ሴቶች እና ልጆች ብቻ መተኛት፣ ገላ መታጠብ እና ምግብ ማብሰል ይችላሉ። ይህ ቤት በ ’ዡል ፌሪ’ የቀን ማዕከል ውስጥ ይገኛል። ‘ላ ቪ አክቲቭ’ የተባለ ድርጅት ቦታውን በኃላፊነት ይቆጣጠራል፤ ነገር ግን አብዛኛውን ጊዜ የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴዎችን የሚያስተባብሩት ሴቶቹ ራሳቸው ናቸው። አንዳንዴ የመተኛ ቦታዎች እጥረት አለ፤ ነገር ግን ሴቶች ብቻ ገላቸውን ለመታጠብ ሁል ጊዜ ወደዚያ መሄድ ይችላሉ።  በውሾች በሚታገዙት የጥበቃ ሠራተኞች በኩል ማለፍ ወይም አምሽታችሁ ከደረሳችሁ ከግቢ ውጭ ያለውን የመጥሪያ ደወል መጠቀም አለባችሁ!! በፈለጋችሁበት ጊዜ የመግባትና የመውጣት መብት አላችሁ።
ብርድ ልብስ፣ ድንኳን፣ አልባሳት ከየት ማግኘት እችላለሁ ?
ብርድ ልብሶች ፣ አልባሳት ወይም ድንኳን ካስፈለጋችሁ ድንበር የለሾችን መጠየቅ ትችላላችሁ። ገነር ግን እነሱ መደበኛ ድርጅት ስላልሆኑ ሁሌም ላይኖራቸው ይችላል። እንዳንዴ ሰዎች የእርዳታ ቁሳቁሶችን በተሽከርካሪ ሞልተው ወደ ጫካዎች በመዉሰድ ድንኳኖችን፣ « ስሊፒንግ ባግ » ወይም ብርድ ልብሶችን ያድላሉ። አንዳንዴ « ሜደሳን ዱ ሞንድ » የተባለ ድርጅት እነዚህን ቁሳቁሶች በብዛት ወደ ጫካው ያመጣል (በተለይ ፖሊስ የስደተኞችን መኖሪያ ማፍረሱን ተከትሎ)። አለመታደል ሆኖ እነዚህን ቁሳቁሶች በነፃ ሁል ጊዜ ልታገኙ የምትችሉበት የተወሰነ ቦታ የለም። ወደ ካሌ በሚላኩ/በሚመጡ ዕርዳታዎች ላይ የተመሠረተ ነው።
በሁለት ሳምንት አንዴ (ቅዳሜ ቀን) ከ « ኖትር ዳም» ቤተ-ክርስቲያን አጠገብ፤ «ሩ ደ ክሯ» የሚባል መንገድ ላይ የሚገኝ የልብስ መድብር አልባሳት ያከፋፍላል። አንዳንድ ቀናት ከምግብ በኋላ (ቁርስ፣ ምሳ ወይም እራት በኋላ) ድንበር የለሾችም ሊረዱ ይችላሉ።

የጥገኝነት ጥያቄ ወይም አስተዳደራዊ ሂደቶችን በተመለከተ ማን ሊረዳኝ ይችላል ?
«ሰኩር ካቶሊክ» (Secours catholique) : ሕግ-ነክ የምክር አገልግሎት ቢያስፈልጋችሁ ወይም ጥገኝነት መጠየቅ ብትፈልጉ ወደ «ሰኩር ካቶሊክ» መሄድ ጥሩ ሃሳብ ነው። ከየትኛውም ሀገር የመጣችሁ ብትሆኑ እነሱ የምክር አገልግሎት ሊሰጧችሁ ከመቻላቸው ባሻገር ሊደገፏችሁም ይሞክራሉ።
ስልክ/ኢንተርኔት የት መጠቀም እችላለሁ ?
በካሌ ቤተ-መጻህፍት («ሜዲያቴክ») በ «ፖን ላልታን» መንገድ ቁጥር 16 ላይ ከትልቁ ገበያ ማዕከል እና ከቲያትር ቤቱ አጠገብ የሚገኘው የካሌ ቤተ-መጻህፍት ከጧቱ አራት ሰዓት ጀምሮ ክፍት ሲሆን እሁድ እና ሰኞ ግን ዝግ ነው። ችግር :- የመታወቂያ ካርድ ወይም ፓስፖርት ወይም ጥገኝነት መጠየቃችሁን የሚያሳይ ወረቀት ማሳየት ይጠበቅባችኋል።
ስልኬን የት ቻርጅ ማድረግ እችላለሁ ?
ሰኩር ካቶሊክ :- ከሰኞ እስከ ዓርብ ከጧቱ 3ሰዓት እስከ ማታ 11 ሰዓት ድረስ።
ዡል ፌሪ የቀን ማዕከል :- ሁልጊዜ ከሰዓት በኋላ ከ8 ሰዓት እስከ 11ሰዓት።
ስልኮችን ቻርጅ ለማድረግ ፍቃደኛ የሚሆኑ አንዳንድ ሰዎችም አሉ። የእነዚህን ሰዎች አድራሻ በአካባቢው ጠይቁ።
እግር ኳስ የት መጫወት እችላለሁ??
በየሳምንቱ እሁድ 9 ሰዓት አካባቢ ሰዎች (ከተለያዩ ማኅበርሰብ የሚመጡ ስደተኞችና በካሌ አካባቢ የሚኖሩ ፈረንሳዊያን) በከተማዉ ባለው ሜዳማ ቦታ ላይ እግር ኳስ ይጫወታሉ። ማንኛውም ሰው መጥቶ መጫወት ይችላል። ብዙ ጊዜ ሰዎች የስፖርት አልባሳት እና ጫማዎችን ወደዚያ ይዘው ስለሚመጡ እናንተም ከዚያ መጠቀም ትችላላችሁ።
ሌላ ቋንቋ የት መማር እችላለሁ ?
በሳምንቱ አብዛኛው ቀናት ውስጥ የፈረንሳይኛ እና እንግሊዝኛ ትምህርት የሚሰጡባቸው ቦታዎች አሉ። ሰኩር ካቶሊክ (Secours catholique) እና ስኳት ጋሎ (squat Galloo) ሄዳችሁ ጠይቁ።
የስነ ተዋልዶ ጤና፤ ነፃ የወሊድ መቆጣጠሪያ እና የምክር አገልግሎት የት ማግኘት እችላለሁ ?
በፈረንሳይ ሀገር ወሊድን መቆጣጠር ነፃ እና ሕጋዊ ነው። በፓስ (PASS) ክሊኒክ የወንዶች ኮንዶም ማግኘት የሚቻል ሲሆን በቤተሰብ ዕቅድ ማዕከል ደግሞ ማንኛውም ዓይነት የወሊድ ማቆጣጠሪያ (ክኒን፣ የሴቶች ኮንዶም፣ መርፌ፣ ሉፕ፣ ወዘተ) ማግኘት ይችላሉ። የቤተሰብ ዕቅድ ማዕከል አድራሻ፥ ሩ ሞሊዬን መንገድ ቁጥር 70 አንደኛ ፎቅ፣ 62100 ካሌ። (rue Mollien, n°70, 1 er étage, 62100 Calais) የስልክ ቁጥር፥ 03 21 21 62 33 ነዉ።
በግብረ ሥጋ የሚተላለፍ በሽታዎች (ኤች አይ ቪ፣ ሄፓቲቲስ ቢ፣ ወዘተ) ምርመራ ማድረግ ከፈለጋችሁ፣ በምርመራ ማዕከል « ሶንትር ደ ዴፒስታዥ » (centre de dépistage) ማንነታችሁን ለመግልፅ ሳትገደዱ ነፃ የደም ምርመራ ማድረግ ትችላላችሁ። አድራሻ ፥Centre de dépistage anonyme et gratuit (ሶንትር ደ ዴፒስታዥ አኖኒም ኤ ግራቱዊ (ነፃ እና ማንነትን የማይጠየቅ የጤና ምርመራ ማዕክል), 1601 ቡለቫርድ ዴ ዡስት (Boulevard des Justes), 62100 ካሌ። የአውቶቡስ መስመር ቁጥር 3፣7 እና 8 መጠቀም ትችላላችሁ።
የስልክ ሲም ካርድ እንዴት ማውጣት እችላለሁ ?
የስልክ ሲም ካርድ ማውጣት ከፈለጋችሁ የሊይካ (Lyca) ስም ካርድን መምረጥ ጥሩ ሃሳብ ነው። ምክንያቱም ከሌሎች የሊይካ ሲም ካርድ ተጠቃሚዎች ጋር በነፃ መደዋወል ስለሚያስችላችሁ እና ሲም ካርዱን ለማውጣት ትክክለኛ ስማችሁን ማስመዝገብ ስለማያስፈልጋችሁ ነው።
ሲም ካርዳችሁን ለማስመዝገብ 323 ላይ ደውሉ። በኢንግሊዝኛ ወይም ፈረንሳይኛ ወይም በዓረቢኛ ይናግሯችኋል። የሆነ ስም መስጠት ያስፈልጋል፣ በተጨማሪም በካሌ የሚገኝ የመንገድ ስም፣ ቁጥር እና የፖስታ ኮድ (የፖስታ ኮድ ቁጥር 62100 ነው) እና የሆነ ፓስፖርት ቁጥር (የዩኬ ፓስፖርት ሁል ጊዜ 9 ቁጥሮች ይይዛል ልምሳሌ፥ 450100397) ። እነሱ የሚያጣሩት/የሚያረጋግጡት የሰጣችሁት አድራሻ በትክክል ስለመኖሩ ብቻ ነው። የናንተን እዉነተኛ አድራሻ እንድትሰጡ አትገደዱም ነገር ግን የምትሰጡት አድራሻ በከተማዉ ዉስጥ ያለ ወይም የሚታወቅ መሆን አለበት (በከተማዉ ዉስጥ የሌለ ወይም የማይታወቅ አድራሻ መስጠት የለባችሁም)። እነሱ የሰጣችሁትን የፓስፖርት ቁጥር ትክክለኝነት አያረጋግጡም። ወደ 323 የደወላችሁትን ስልክ ስትጨረሱ ስልካችሁን ማጥፋት እና እንደገና ማብራት አለባችሁ። አሁን ይሰራል።

ፖሊስ፣ በፖሊስ መያዝ፣ መታሰር እና በቁጥጥር ስር መዋል/ማቆየት/
ፖሊስ ቢይዘኝ እና ጥቃት ቢያደርስብኝ ምን ማድረግ ይኖርብኛል ?
በፖሊስ ጥቃት ከደረሰባችሁ ከጎናችሁ ነን። ስልጣናቸውን ያለአግባብ የሚጠቀሙ ከሆነ፤ ማንም ሰው ወረቀት ያለውም ሆነ የሌለውም በፖሊስ ላይ ቅሬታ የማቅረብ መብት አለው። የፖሊስ ጥቃትን በተመለከተ ቅሬታ ማቅረብ ከፈለጋችሁ ጠበቃ አማክሩ ወይም ድጋፍ ከፈለጋችሁ በ06 05 86 21 50 (የሊይካ ሞባይል ቁጥር ነው) መደወል ትችላላችሁ። ይህ የምትደውሉለት አካል መንግሥታዊ የታወቀ ቡድን አይደለም። ነገር ግን መረጃ በማሰባሰብ የፖሊስ ጥቃት የሚደረሰባቸውን ሰዎች የሕግና የጤና ዕርዳታ በተቻለ ጊዜ እንዲያገኙ የሚሞክር ትንሽ ቡድን ነው።
በካሌ የሚገኙ ስደተኞች ላይ የሚደርሱ የፖሊስ ጥቃቶች ተደጋጋሚ፣ ተዘውታሪ እና ሀይለኛ ናቸው። ብዙ ሰደተኞች ወደ መሠረታዊ አገልግሎት ቦታዎች በመሄድ ላይ እንዳሉ በዘፈቀደ ይታሰራሉ። ለምሳሌ፥ ከጫካ ውሃ ወደሚገኝበት ቦታ በመሄድ ላይ እንዳሉ፣ ወደ ሆስፒታል ለመሄድ አውቶቡስ ሊሳፈሩ ሲሉ፣ በሱፐር ማርኬት የሆነ ነገር በመግዛት ላይ ሳሉ፣ ወይም ምግብ ከሚከፈፈልበት ቦታ ደርሰው በመመለስ ላይ ሳሉ። ብዙ ስደተኞች በፖሊስ ተደበድበዋል አስለቃሽ ጭስም ተጠቅተዋል፣ በዚህም የተነሳ እግራቸው ተሰብሯል፣ በክንዳቸው እና በፊታቸው ላይ ጉዳቶች ደርሰውባቸውል። ፖሊስ ስደተኞችን በሚያሳድድበት ወቅት የከፍተኛ ፍጥነት መንገዶች ላይ ባለፉት ጥቂት ወራት በርካታ የሞት አደጋዎች እንደተከሰቱ የሚያሳዩ ሪፖርቶችም አሉ።
ታስራችሁ ከሆነ፥ መብታችሁና ሕጎች
የውጭ ዜጎችን ማንነት አጣርቶ ለማወቅ እስከ 16 ሰዓት ያህል ጊዜ ሊወስድ ይችላል። ምንም እንኳን ወረቀት ባይኖራችሁም ወደ ፖሊስ ጣቢያ ልትወሰዱና በሰዓታት ውስጥ ልትፈቱ ትችላላችሁ። በአጠቃላይ የፖሊስ ጥበቃ የሚጀምረው ከታሰራችሁበት ጊዜ ጀምሮ ነው። ፖሊስ ስለመብታችሁ በምትረዱት ቋንቋ ሊነግራችሁ ይገባል (መብቶችን ማሳወቅ) ።
በእስር ቤት ውስጥ ከዚህ በታች የተዘርዘሩት መብቶች አላችሁ፥
ጓደኛ ወይም የቤተሰብ አባል መታሰራችሁን እንዲያወቅ የማድረግ
የእስር ቤቱን ድርጅት ለማግኘት ስልክ የመደወል
አስተርጓሚ የማግኘት
ሐኪም የማግኘት
ከጠበቃ እርዳታ እና ምክር የማግኘት።
በፖሊስ ጥበቃ ስር እያላችሁ ጥያቄዎችን ያለመመለስ መብት አላችሁ። ፖሊስ እንድትፈርሙ በሚያቀርብላችሁ ወረቀት ላይ አስተርጓሚ እስኪተረጉምላችሁ ድረስ ባትፈርሙበት የተሻለ ነው። መፈረም የለባችሁም። ነገር ግን በትክክል ምን እንደሚል ማወቅ አለባችሁ። እያንዳንዱ በፅሑፍ የሰፈረውን ቃል በሙሉ (የታሰራችሁበትን ጊዜና ቦታ ወዘተ) በጥንቃቄ ተመልከቱ። ትንሽ ስህተት ጠበቃው እናንተን ከእስር ቤት ለማውጣት ይረዳዋል። እናንተን በፍርድ ቤት ሊረዳችሁ የሚችል ፖሊስ የፈፀመው ስህተት መኖሩን ካወቃችሁ ለፖሊሱ አትንገሩት ምክንያቱም ሊያስተካክለው ይችላል።
ምርመራውን ለማከናወን ከሚያስፈልገው ጊዜ በላይ በእስር ቤት ልትቆዩ አይገባም። በዚህ ጉዳይ ላይ ይህ ማለት የእስረኛውን ሙሉ ማንነት (ሙሉ ስም፣ አድራሻ፣ ዜግነት፣ የወላጆቹን ስሞች) እና ቃል መቀበል ማለት ነው።
የፖሊስ ማቆያ ማዕከል
የፈረንሳይ ቪዛ ከሌላችሁ፣ የፖሊስ አለቃው « ኦ.ኪው.ቴ.ኤፍ » (የፈረንሳይን ምድር የመልቀቅ ግዴታ) ሊልክላችሁ ይችላል። ይህም ማለት ታስራችሁ ከሆነ ወደ ማቆያ ማዕከል ትወሰዳላችሁ። እዚያ ያሉ ሕጐች እስር ቤት ካሉት ትንሽ ይለያሉ። እቃዎቻችሁን ሌላ ሰው እንዲያመጣላችሁ ማድረግ እና እናንተ ጋር ማቆየት ትችላላችሁ። ስልካችሁንም መያዝ ትችላላችሁ (ምንም እንኳ ካሜራ ያለውን የስልክ ቀፎ ፖሊስ ቢነጥቅም)። ጥበቃዎች ገንዘባችሁን ያስቀምጡላችኋል። ማንኛውም ሰው ሊጐበኛችሁ ይችላል። እናንተን ለመጎብኘት የሚመጡ ሰዎች ሙሉ ስማችሁን ማወቅ እና የመታወቂያ ካርዳቸዉን ማሳየት ይኖርባቸዋል። አልባሳት የታሸገ ምግብ እና ትምባሆ (ያልተከፈተ እሽግ) እና ጥሬ ገንዘብ ሊያመጡላችሁ ይችላሉ።
ከሀገር እንድትወጡ ማዘዣ ከደረሳችሁ (ኦ.ኪው.ቴ.ኤፍ፣ አ.ፔ.ኤር.ኤፍ፣ ወዘተ) አቤቱታ ለማቅረብ የ24ሰዓት ጊዜ አላችሁ። በማቆያ ማዕከሉን ውስጥ የሚስሩት እርዳታ ቡድን አባላትን አነጋግሩ፤ እነሱ ይረዷችኋል። በፈረንሳይ ማቆያ ማዕከል ከፍተኛው የመቆያ ጊዜ 45 ቀናት ብቻ ነው። በሂደቱ ወቅት ለሚያስፈልግ ማንኛውም ጉዳይ አስተርጓሚ የማግኘት መብት አላችሁ።
በመጀመሪያዎቹ 5 ቀናት ውስጥ በፖሊስ መያዛችሁ ሕጋዊ መሆን አለመሆኑን ወይም በናንተ ጉዳይ ፖሊስ ምንም አይነት ስህተት መስራት አለመስራቱን በሚወስነው ወይም « ዢ.ኤል.ዴ » (የነፃነት እና በቁጥጥር ስር የመዋል ጉዳዮች ዳኛ) ከሚባለው ልዩ ዳኛ ዘንድ ሊያቀርቧችሁ ግዴታ አለባቸዉ። በጉዳያችሁ አካሄድ ላይ ስህተት መኖሩን መረጋገጥ ካቻላችሁ (ለምሳሌ በእስር ቤት ውስጥ መብቶቻችሁን ማክበር ሳይችሉ ከቀሩ፣ በጉዳዮቻችሁ የጊዜ ሰሌዳ አካሄድ ላይ ስህተት ከሰሩ) ሊለቋችሁ ይገባል።
በጉዳያችሁ አካሄድ ላይ ስህተት እንዲፈልግ ለጠበቃችሁ ልትነግሩ ይገባል። ከ20 ቀናት በኋላ እንደገና ከዳኛው ዘንድ ትቀርባላችሁ።በዚህ ጊዜ ልታቀርቧቸው የምትችሏቸው መረጃዎች በ20ዎቹ ቀናት ውስጥ የተከሰቱ / የተፈፀሙ መሆን አለባቸው።
እናንተን ከፈረንሳይ ለማስወጣት ፈረንሳይ እናንተ የመጣችሁበትን ሀገር (የትዉልድ ሀገራችሁ ነው በለው የሚያስቡትን ሀገር) ኤምባሲ ፍቃድ ትፈልጋለች። ከመንግሥት ባለስልጣን ጋር ቃለ-መጠይቅ ይኖራችኋል። በቃለ-መጠይቅ ወቅት ከባለሥልጣኑ ጋር ብቻችሁን ለመሆን መጠየቅ ችትላላችሁ፤ መብታችሁ ነው። ቃለ-መጠይቁን ማድረግ አለባችሁ ነገር ግን በወቅቱ ጥሩ ስሜት ይማይሰማችሁ ከሆነ (በህመም ምክንያት) ቆይታችሁ (ሲሻላችሁ) በሌላ ጊዜ ለማድረግ መጠየቅ ትችላላችሁ።
ከሀገር እንዲለቁ የተወሰነባቸዉ ሰዎች በሚታሰሩበት ማዕከል (ዲፖርቴሽን ሴንተር) ውስጥ ከሆናችሁ የጥገኝነት ጥያቄ ለማቅረብ 5 ቀናት አላችሁ። ከዚያም ጉዳያችሁ በፍጥነት ይታያል።

እርግዝና
የእርግዝና ምርመራ ለማደርግ የምትፈልጉ ሴቶች ካሌ በሚገኘው የቤተሰብ ዕቅድ ማዕከል ሂዱ። አድራሻ :- Centre de planification et d’éducation familiale (ሶንትር ደ ፕላኒፊካሲዮን ኤ ዴዱካሲዮን ፋሚሊያል), 70 rue Mollien, premier étage, 62100 Calais (70 ሩ ሞሊየን / ሞሊየን መንገድ የቤት ቁጥር 70), 62100 ካሌ። ስልክ፥ 03 21 21 62 33 (ምናልባት ፈረንሳይኛ ብቻ ሊናገሩ ይችላሉ) ወይም ፓስ ( PASS ) ኪሊኒክ መሄድ ትችላላችሁ።
ከዚህ በኋላ በትልቅ ሆስፒታል መደበኛ ክትትል እንደታደርጉ ቀጠሮዎችን ይሰጧችኋል።
ነፍሰጡር ከሆናችሁ እና የጥገኝነት ጥያቄ ለማቅረብ ከወሰናችሁ የፈረንሳይ ሕግ  « ተጋላጭ » አድርጐ ለሚወስዳቸዉ እንደ ትናንሾች እና የታመሙ ሰዎች ቅድሚያ ይሰጣችኋል። ይህ ማለት እንደ ስደተኛ ተቀባይነት ለማግኘት እና ለረጅም ጊዜ የሚያገለግሉ የመኖሪያ ወረቀቶችን ለማግኘት ከፍተኛ ዕድል አላችሁ ማለት አይደለም። ነገር ግን እንደ መኖሪያ ቤት፣ የጤና ዋስትና (ኢንሹራንስ) እና ገንዘብ የመሳሰሉትን ማህበራዊ አገልግሎቶች ወዲያውኑ (እንድትጠብቁ ሳይደረግ) ታገኛላችሁ።
ነፍሰ ጡር ብሆን እና እርግዝናውን/ፅንሱን ባልፈልግ ወይም መቀጠል ባልችል ምን ማድረግ ይገባኛል ? እርጉዝ ከሆንሽ ፅንሱን ለማስወጣት ወይም ለመውለድ ለመወሰን ነፃ ነሽ። ያንቺ ምርጫ ነው ! ምንም እንኳ አቅመ ደካማ ብትሆኚ ፅንሱን ለማቋረጥ ወይም ለመውለድ በራስሽ የመወሰን መብት አለሽ።
በፈረንሳይ ሀገር እስከ 12ኛው ሳምንት የእርግዝና ጊዜ ፅንሱን የማቋረጥ መብት አለሽ። በልዩ የሕክምና ምክንያት ከ12ኛው ሳምንት በኋላም ፅንሱን ማስወጣት ሊፈቀድ ይችላል። ፅንስ ለማቋርጥ ገንዘብ መክፈል አይገባሽም፤ ፅንስ የማስወጣት ስራዉ በሆስፒታል ወይም በልዩ ማዕከል በጥሩና በምቹ ሁኔታ ሊደረግ ይችላል። ፅንስ በሚቋረጥበት ጊዜ የሚደርስ አደጋ ሥጋት በጣም ዝቅተኛ ሲሆን ለወደፊቱ በጤናሽ እና በመዉለድ ዕድልሽ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ የለውም።
መደረግ ያለበት
1 – ነፍሰ ጡር ለመሆንሽ ማረጋገጫ የእርግዝና መርምራ አድርጊ :- የእርግዝና መመርመሪያዎችን ከሱፐር ማርኬት ወይም ከመድሃኒት መደብር መግዛት ትችያለሽ። በፈረንሳይኛ « ቴስት ደ ግሮሴስ » (test de grossesse) ይባላል።
2 – የምርመራው ውጤት እርጉዝ መሆንሽን ካረጋገጠ በተቻለ መጠን ወዲያውኑ ከ « (ሶንትር ደ ፕላኒፊካሲዮን ኤ ዴዱካሲዮን ፋሚሊያል (Centre de planification et d’éducation familiale / የቤተሰብ ዕቅድ ማዕከል) ቀጠሮ ውሰጂ። አድራሻ :- Centre de planification et d’éducation familiale (ሶንትር ደ ፕላኒፊካሲዮን ኤ ዴዱካሲዮን ፋሚሊያል), 70 rue Mollien, premier étage, 62100 Calais (70 ሩ ሞሊየን / ሞሊየን መንገድ የቤት ቁጥር 70), 62100 ካሌ። ስልክ፥ 03 21 21 62 33 (ምናልባት ፈረንሳይኛ ብቻ ሊናገሩ ይችላሉ)። ስምሽን፣ የልደት ቀን እና የወር አበባ ለመጨርሻ ጊዜ ያየሽበትን ጊዜ ይጠይቃሉ።ሌላው አማራጭ ወደ ፓስ ኪሊኒክ (clinique PASS) በመሄድ ያለሽበትን ሁኔታ ለእነሱ ማስረዳት ነው። ከፈለግሽ የሚደግፍሽ ጓደኛ ይዘሽ መሄድ ትችያለሽ። ዕድሜሽ ከ 18 ዓመት በታች ከሆነ የፈለግሽዉን አንድ አዋቂ ሰው (ከ18 ዓመት በላይ የሆነ)ወይም ሴት ይዘሽ መሄድ አለብሽ።
3 – በ « ሶንትር ደ ፕላኒፊካሲዮን » አጭር ምርመራ ያደርጉልሽና ከዚያ ለመጀመሪያው የሕክምና የምክር አገልግሎት በትልቅ ሆስፒታል ቀጠሮ ያመቻቹልሻል።
4 – የመጀመሪያውን የሕክምና ምክር አገልግሎት በካሌ ከተማ በሚገኘዉ ትልቅ ሆፒስታል ታደርጊያለሽ። የሆስፒታሉ ሰራተኞች እንዳንድ ጊዜ ስደተኛ ሴቶች  በዚህ ሆስፒታል ፅንስ እንዲያቋርጡ ስለማይፈልጉ ችግር ሊፈጥሩ ይችላሉ። ይህ ስህተት ከመሆኑም ባሻገር እነሱ የመከልከል መብት ወይም ስልጣን የላቸውም። ይህን ከዚህ በታች በፈረንሳይኛ ቋንቋ የሰፈረዉን የሕግ አንቀጽ/ፅሑፍ ለነሱ ማሳየት ትችላላችሁ: –
«  La loi fait obligation aux structures hospitalières de prendre en charge les IVG de femmes étrangères sans papiers. La loi DHOS/DSS/DGAS n°141 du 16 mars 2005 demande :
La prise en charge des soins urgents des étrangers-res RESIDANT en France de manière irrégulière et non-bénéficiaires de l’aide médicale d’Etat
Et donne ainsi accès à l’IVG à toute femme étrangère séjournant en France. »
የደም ምርመራ ያደርጉና በ « ሶኖግራም » የሆዳችሁን ውስጥ ምስል በፎቶ ይወስዳሉ። ዶክቶሩ የምርመራውን ውጤት መግለጫ ይፅፍና ፅንሱን ለማስወረድ የቀጠሮ ቀን ይሰጣል። ፅንሱ የሚወጣው የመጀመሪያው ምርመራ ከተደረገ ከ7 ቀናት በኋላ ብቻ ነው፤ ድንገተኛ ካልሆነ በስተቀር። የ7 ቀናት ጊዜ የማሰቢያ ጊዜ ይባላል፤ ምናልባት ሀሳብሽን መቀየር ብትፈልጊ እና ፅንሱን መዉለድ እና ህጻኑን ማሳደግ  ብትፈልጊ ሐሳብሽን የማሳወቂያ ጊዜ ነው።
5 – ዕድሜሽ ከ18 ዓመት በታች ከሆነ ፅንሱን ከማስወጣትሽ በፊት  « ሶሻል ወርከር »  (የማህበረሰብ እና የቤተሰብ ጉዳይ ባለሙያ) ማነጋገር አለብሽ። የሶሻል ወርከሮችን አድራሻ ከ « ሶንትር ደ ፕላኒፊካሲዮን » ማግኘት ትችያለሽ።
6 – ፅንሱ የሚወጣበት ቀን፤ ሁለት ዘዴዎች አሉ :-
የሕክምና ዘዴ (በእንክብል አማካኝነት) :- ይህ ሊሆን ይሚችለው እስከ 5ኛ ሳምንት ዕድሜ ላለው ፅንስ ሲሆን ሆስፒታል መሄድ ሳያስፈልግ ሊፈፀም ይችላል። ከ5ኛ እስከ 7ኛው ሳምንት ዕድሜ ክልል ዉስጥ ያለ ፅንስ ሊወጣ የሚችለው ሆስፒታል በመሄድ ነው።
የቀዶ ጥገና ዘዴ :- እስከ 12ኛ ሳምንት ዕድሜ ያለው ፅንስ በቀዶ ጥገና ማስወጣት ይችላል። ለማህፀን አካባቢ ወይም ለአጠቃላይ የሰዉነት ክፍል በሙሉ ማደንዘዣ ይሰጣል። የሚከናወነው በቀን ሲሆን ለጥቂት ሰዓታት በሆስፒታል መቆየትሽ ግድ ነዉ።
7 – ፅንሱ ከወጣ ከ3 ወይም ከ4 ሳምንታት በኋላ ምንም አይነት የጤና ችግር እንደሌለብሽ ለሚረጋገጥ ደግሞ ምርመራ ማድረግ ትችያለሽ። የተለያዩ አማራጭ የወሊድ መቆጣጠሪያ መንገዶችን ይጠቀሟችኋል።

በእንግሊዝ ወይም በሌሎች የአውሮፓ ሕብረት አባል አገሮች የጥገኝነት ጥያቄ እንዴት ማቅረብ እችላለሁ?
አብዛኛዎቹ በካሌ ያሉ ስደተኞች በእንግሊዝ ሀገር (ዩናይትድ ኪንግዶም) ጥገኝነት ማመልከት ስለሚፈልጉ ስኬታማ የጥገኝነት ማመልከቻ ሊያቀርቡ የሚችሉበትን ዕድል ከፍ ለማድረግ ጥቂት መረጃዎችን አካተናል። በሌሎች የአውሮፓ ሕብረት አባል ሀገራት ለጥገኝነት ማመልከት ተመሳሳይ ቢሆንም በእያንዳንዱ አገር ጥቂት ልዩነቶችም አሉ። እንደ ፈረንሳይ እና ጀርመን የመሳሰሉ ሌሎች አገራትን በተመለከተ ጥቂት መረጃ ያካተትን ቢሆንም እያንዳንዱን ነገር ለማብራራት ቦታ የለንም። ከነዚህ አገራት ውጭ ጥገኝነት ለመጠየቅ ከወሰናችሁ በመረጣችሁት ሀገር የሚሰራ ጠበቃ ወይም ስደተኞችን የሚደግፍ/የሚረዱ አካላትን እዚያ እንደደረሳችሁ ወይም እዚያ ከመድረሳችሁ በፊት እዚህ አድራሻቸውን በተመለከተ መረጃ ልታገኙ ትችላላችሁ። በመረጣችሁት ማንኛውም ሀገር እንዴት ለጥገኝነት እንደምታመለክቱ እነሱ የበለጠ ዝርዝር መረጃ ይሰጧችኋል።

በዩናይትድ ኪንግዶም (እንግሊዝ ሀገር) ጥገኝነት ስለመጠየቅ
የጥገኝነት አሰጣጥ ሥርዓቱ/ደንቡ ውስብስብ ነው። ሥርዓቱ እንዴት እንደሚፈፀም ከተረዳችሁ የተሻለ ዕድል ይኖራችኋል።
ጥገኝነት ምንድን ነው ?
በዩናይትድ ኪንግዶም (እንግሊዝ ሀገር) ጥገኝነት ስትጠይቁ እንደ ስደተኛ እውቅና ለማግኘት እየጠየቃችሁ ነው ማለት ነው። የስደተኛ ሕጋዊ ብያኔው :-
« በአንድ ማህብረሰብ ውስጥ በዘር፣ በሃይማኖት፣ በዜግነት፣ በፖለቲካ አመለካከት ወይም አባልነት የተነሳ ለመሰደድ የሚያበቃ ትልቅ ፍርሃት ያለበት ሰው ማለት ነው »
በቅጥታ በእናንተ የወደፊት ሕይወት ላይ (በሌሎች የወደፊት ሕይወት ላይ ያለ ስጋት ምክንያት አይሆንም) የተረጋገጠ እውነተኛ ስጋት መኖሩን እና በየትኛውም የሀገራችሁ ክፍል ድህንነታችሁ ሊጠበቅ እንደማይችል የማሳየት ወይም የማስረዳት ግዴታ አለባችሁ። በተጨማሪም ለምን የእንግሊዝ መንግሥት ድህንነታችሁን ለመጠበቅ ኃላፊነት እንዳለበት የማሳየት ወይም የማስረዳት ግዴታ አለባችሁ።
ልብ በሉ :- ከሀገራችሁ የወጣችሁት ሥራ ለማግኘት ወይም የተሻለ ሕይወት ለመኖር ከሆነ በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት እንደ ስደተኛ አትቆጠሩም። በተቻለ መጠን ወዲያውኑ ዩናይትድ ኪንግዶም (እንግሊዝ ሀገር) እንደገባችሁ የጥገኝነት ጥያቄያችሁን ማቅረብ አለባችሁ። በጣም ቆይቶ የሚቀርብ የጥገኝነት ጥያቄ የተቀባይነት ዕድሉ በጣም አነስተኛ ከመሆኑም ባሻገር እንደ መኖሪያ ቤት እና ምግብ የመሳሰሉ እርዳታዎችን ከመንግሥት ላታገኙ ትችላላችሁ። ነገር ግን አሳማኝ ምክንያት ካላችሁ ዘግይቶም ቢሆን የጥገኝነት ጥያቄ ማቅረብ ትችላላችሁ። ለምሳሌ ከዚህ በፊት ጥያቄያችሁን ለማቅረብ ወደ ክሮይዶን (Croydon) ለመሄድ ሳትችሉ ከሆነ ወይም በሕገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች ጥቂት ቀናት አንድትቆዩ ተነግሯችሁ ከሆነ ወይም በሌላ አሳማኝ ምክንያት።
የደብሊን ስምምነት/ደንብ (Dublin Convention)
ደብሊን ሦስተኛ ምንድን ነው ?
የደብሊን ደንብ አንድን የጥገኝነት ጥያቄ የትኛው የአውሮፓ ሀገር መመርመር እንዳለበት ለመወሰን የሚያስችል ነው። የጥገኝነት ጥያቄያችሁ ሊታይ የሚችለው እነሱ እናንተ መጀመሪያ የገባችሁበት የአውሮፓ ሀገር የሄ ነዉ ብለው በሚያረጋገጡት መሠረት ነው። አሁን ካለችሁበት የአውሮፓ ሀገር ከመምጣችሁ በፊት በሌላ የአውሮፓ ሀገር የጣት አሻራ በዪሮዳክ (Eurodac) ሰጥታችሁ ከሆነ ወደዚያ አንድትመለሱና የጥገኝነት ጥያቄያችሁ በዚያው አገር እንዲታይ ነው የሚደረገዉ። ይህን በተመለከተ ሌላ ምንም አማራጭ የላችሁም። አንዳንድ አባል አገራት  አስገድደው የጣት አሻራ ይወስዳሉ። በሌላ አገር በኩል መምጣታችሁ በሌላ መረጃ ሊያረጋግጡ ይችላሉ (ለምሳሌ እናንተ ከነገራችኋቸው)። ጉዟችሁን አስመልክቶ በቃለ-መጠይቅ ጊዜ የምትሰጡት ማንኛውም ዝርዝር መረጃ ጉዳያችሁ በደብሊን ደንብ መሠረት መታየት አለበት ወይስ የለበትም የሚለውን ይወስናል። አሁን ወዳላችሁበት ሀገር የገባችሁት በቀጥታ በረራ ከሆነ ወይም በምድር ትራንስፖርት በመሀል የትም ቦታ ሳይቆም ከመጣችሁ እና የሌላ አባል አገር ድንብር አቆርጣችሁ መግባታችሁን (ለምሳሌ በተዘጋ የጭነት ተሽከርካሪ ስትጓዙ) እንዳላወቃችሁ ማስረዳት ከቻላችሁ ለሌላ ወይም ለመጀመሪያው ሀገር ተላልፋችሁ ልትሰጡ አይገባም። የቃለ-መጠይቁ አሰራር/አደራረግ በእያንዳንዱ አባል ሀገር ትንሽ ይለያያል። የደብሊን ሦስተኛ ደንብ እንዴት እንደሚተገበር ዝርዝር መረጃ ሊኖራችሁ ይገባል።
የትኛው አባል ሀገር ጉዳያችሁን የማየት ኃላፊነት እንዳለበት ለማወቅ ቃለ-መጠይቅ ይደረግላችኋል። አሁን ያላችሁበት ሀገር የጥገኝነት ጥያቄያችሁ በሌላ አባል ሀገር እንደሚስተናገድ ከወሰነ ወደዚያ እንድትዛወሩ ይጠይቃል። ሁለተኛው አባል አገር ሊወስዳችሁ ከተስማማ በደብዳቤ ይገለፅላችኋል።
ለምሳሌ :- ጀርመን ሀገር ለጥገኝነት አመልክታችሁ ቢሆን ነገር ግን በቃለ-መጠይቅ ወቅት ለሦስት ሳምንት ስፔን መቆየታችሁን ከተናገራችሁ በደብሊን ሦስተኛ ደንብ መሠረት ምናልባት ወደ ስፔን እንድትመለሱ እና የጥገኝነት ጥያቄያችሁን እዚያ እንድታቀርቡ ሊደረግ ይችላል።
ቤተሰብ :- በሌላ አባል አገር ጥገኝነት ፈላጊ ወይም ስደተኛ ባል፣ ሚስት ወይም ልጅ (ከ18 ዓመት በታች የሆነ ልጅ) ጋር ለመቀላቀል እንደምትፈልጉ ለባለሥልጣናት ከነገራችሁ በደብሊን ሦስተኛ ደንብ መሠረት ምናልባት ወደዚያ ሀገር ልትዛወሩ ትችላላችሁ።
ዝውውር :- ወደሌላ አባል አገር መዛወራችሁ (ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አዎንታዊ መልስ ካገኘ) አባል አገራት በዝውውሩ ሁኔታ ላይ ይስማማሉ። ባለጉዳዩ ከአገር ወጥቶ ወይም ታስሮ ካልሆነ በስተቀር የደብሊን ደንብ አፈፀፀሞ ከ11ወር ውስጥ ቢያንስ ለአምስት ወራት ኖራችሁ ከሆነ የአገሩ መንግሥት የጥገኝነት ጥያቄያችሁን የማየት ኃላፊነት አለበት።
አባል አገራት :-ኦስትሪያ፣ ቤልጅየም፣ ቡልጋሪያ፣ ክሮሺያ፣ ቆጵሮስ (ሳይፕረስ)፣ ቼክ ሪፐብሊክ፣ ዴንማርክ፣ ኤስቶኒያ፣ ፊንላንድ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ግሪክ፣ ሀንጋሪ፣ አየርላንድ፣ ኢጣሊያ፣ ላትቪያ፣ ሊቱዋንያ፣ ሉክሰምቡርግ፣ ማልታ፣ ኔዘርላንድ፣ ፖላንድ፣ ፖርቱጋል፣ ስሎቫክያ፣ ስሎቬንያ፣ ስፔን፣ ስዊድን፣ እንግሊዝ (ዩናትድ ኪንግዶም)፣ ኖርዌይ፣ አይስላንድ፣ ስዊዘርላንድ እና ሊሽተንሽታይን ናቸው።
የደብሊን ደንብን መቃወም እችላለሁ?
ምንም እንኳ ከአንድ የአውሮፓ ሕብረት አባል አገር ወደ ሌላ አባል አገር ተላልፎ መስጠትን በተመለከተ ጥቂት የሕግ ሂደቶች (የአቤቱታ/ተቃውሞ) ቢኖሩም የደብሊን ደንብን መቃወም በጣም አስቸጋሪ ነው። ወደ ዩናይትድ ኪንግዶም (እንግሊዝ) ከመምጣታችሁ በፊት የጣት አሻራችሁ ተወስዶ ከሆነ የጥገኝነት ጥያቄ ከማቅረባችሁ በፊት ምክር ማግኘት ጠቃሚ ይሆናል። (ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት በጐ አድራጊ ድርጅቶች እና ማህበራት አንዱን አነጋግሩ።)
የደብሊን ደንብ እንዲወገድላችሁ ልትጠይቁ ይምትችሉባቸው ጥቂት ምክንያቶች።
« ኢ.ሲ.ኤች.አር » (የአውሮፓ ሕብረት የሰብዓዊ መብት ደንብ) አንቀፅ 3 ሕግ ሲጣስ :- ኢሰብዓዊ በሆነ ወይም ሰብዓዊ ክብርን ለሚያዋርድ ድርጊት ሲፈፀምባችሁ (ይህ ገዳይ በአሁን ጊዜ በግሪክ ያለ ሲሆን በሌሎች የአውሮፓ ሕብረት አባል አገራትም የሚነሱ ተቃውሞዎች አሉ።)
በእንግሊዝ አገር (ዩናይትድ ኪንግዶም) ቤተሰብ ካለዎት።
እንግሊዝ አገር (ዩናይትድ ኪንግዶም) ወደ ሌላ አውሮፓ ሕብረት አባል አገር ልትመልሳችሁ ከፈለገች እና ይሄኛው አገር መልሶ እንግሊዝ ሰዎችን ልትልክ/ልትመልስ ወደ ማትችልበት ሌላ አገር የመመለስ አዝማሚያ ካለው።
የአካላዊ ስቃይ ስለባ ሆናችሁ ከነበረ ወይም ከፍተኛ የጤና ችግር ካለባችሁ።
እነዚህ የደብሊን ደንብን ማስወገጃ ምክንያቶች ሳይሆኑ ምክር የምታገኙበት ተጨማሪ ጊዜ የሚያሰጧችሁ ናቸው።

« ዲቴይንድ ፋስት ትራክ » ምንድን ነው ?
እንዳንዴ ጉዳያችሁ « ዲቴይንድ ፋስት ትራክ » በሚባል ፈጣን ዘዴ ሊታይ ይችላል። ይህ ማለት ጥይቄያችሁ እስከሚታይ ድረስ ወደ ማቆያ ማዕከል (የስደተኛ እስር ቤት) ትላካላችሁ። ምናልባት እንደመጣችሁበት አገር (የትውልድ አገር) ሁኔታ ጉዳያችሁ በማያሻማ መልኩ አሳማኝ አለመሆኑ በግልፅ ከተረጋገጠ ይህ ሊገጥማችሁ ይችላል። ነገር ግን በደንብ በመዘጋጀት እና ጉዳያችሁን በመረጃ በማስደገፍ ይህ እንዳይሆን ማድረግ ትችላላችሁ።
ስለ « ዲቴይንድ ፋስት ትራክ » ማወቅ የሚገባችሁ :-
በዚህ ዘርፍ የሚቀርቡ ጉዳዮች ሁሉም ለማለት በሚያስችል ሁኔታ ተቀባይነት አጥተዋል። 99 በመቶ በሓርሞንድስዎርዝ ያልተሳካ ሲሆን፣ ከዚህ ዉስጥ ደግሞ 93 በመቶ የሚሆነዉ ይግባኝ የተጠየቀበትና ያልተሳካ ነዉ።
በውሳኔ ላይ የይገባኝ ጥያቄ ለማቅረብ የሁለት ቀናት ጊዜ አላችሁ።
አጠቃላይ ሂደቱ በማቆያ ማዕከሉ የሚከናወን ሲሆን ውሳኔውም የይግባኝ ጥያቄዉም በፍጥነት ይስተናገዳል፤ ምንም እንኳ ከሀገር የምትወጡበት እዉነተኛዉ ጊዜ በጣም ሊረዝም ቢችልም።
የይገባኝ ጥያቄ ማንኛውም እናንተን ከሀገር የማስወጣት ሙከራን ሊያዘገይ ወይም ሊያስቆም/ሊያሳግድ ይገባል። ጉዳያችሁ ከሀገር እንድትወጡ የተላለፈዉን ትዕዛዝ ለማስቆም/ለማገድ የማያበቃ ምክንያት አይኖረዉም ተብሎ ከተፈረጀ  አቤቱታ የማቅረብ መብት የላችሁም።

የዩናይትድ ኪንግዶም (እንግሊዝ) የጥገኝነት ጉዳይ ሂደት (ከ « ዲቴይንድ ፋስት ትራክ »ውጭ)
በ020 8196 4524 በተቻለ መጠን ወዲያውኑ ከ « ሉናር ሃውስ » የጥገኝነት ጥያቄ ሂደትን ከሚያሳውቀው ክፍል በመደወል የጥገኝነት ጥይቄ ለማቅረብ ቀጠሮ ያዙ። እነሱ ጥቂት መሠረታዊ ጥይቄዎችን ይጠይቁችኋል። እንደ አማራጭ ወደ ፖሊስ ጣቢያ መሄድ ትችላላችሁ፤ እነሱ ከስደተኞች ጉዳይ ተቋም (ኢሚግሬሽን) ጋር ያገናኟችኋል። ከዚያ ወደሚቀጥለው ደረጃ ለመሄድ ቃለ-መጠይቅ ያደርጉላችኋል። እንዴት ወደ እንግሊዝ (ዩናይትድ ኪንግዶም) እንደመጣችሁ ትጠየቃላችሁ፤ የጣት አሻራችሁን እና ፎቶ ይወስዱና ለሌላ የአውሮፓ ሕብረት አባል አገር አሳልፈዉ አንደሚሰጧችሁ ወይም እንደማይሰጧችሁ ይወስናሉ።የጥገኝነት ጥያቄያችሁን በተመለከተ አጫጭር መሠረታዊ መረጃዎችን ልትስጡዋቸው ይገባል።
ሪፖርት ያደረጋችሁበት የመጀመሪያ ቀን :- ጉዳያችሁን የሚከታተለውን ሠራተኛ ታገኛላችሁ፤ እሱም የጥገኝነት ጉዳይ ሂደቱን የተለያዩ ገፅታዎች ሊያስረዳችሁ ይገባል።
ዕድሜ ማረጋገጫ :- ይህ የሚሆነው ለአቅመ አዳም ወይም ለአቅመ ሔዋን ላልደረሱ እና ይህን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ለሌላቸው ነው።
የጥገኝነት ጥያቄውን የተመለከተ ቃለ-መጠይቅ :- ይህ ለምን ከሀገራችሁ እንደወጣችሁ እና ለምን የጥገኝነት ፍቃድ እንደሚያስፈልጋችሁ የምትጠየቁበት ዋናው ቃለ-መጠይቅ ነው።
ተጨማሪ ማስረጃዎች ቃለ-መጠይቁ ከተካሄደ በኋላ ባሉት አምስት ቀናት ውስጥ ሊሰጥ ይገባል።
የጉዳያችሁን ውሳኔ የያዘ ደብዳቤ በፖስታ ሊደርሳችሁ ይገባል።
ቃለ መጠይቆችን በተመለከተ (ከሌሎች የአውሮፓ ሀገራት ጋር የሚመሳሰል)
ሁለት ጊዜ ቃለ መጠይቅ ይደረግላችኋል። በሁለቱ ቃለ መጠይቆች ወቅት የሰጣችሁት መረጃ ይነፃፀራል፤ ስለዚህ በሁለቱም ቃለ መጠይቆች ወቅት የሰጣችሁት መረጃ የግድ አንድ ዓይነት መሆን አለበት።
የመጀመሪያ ቃለ መጠይቅ :- ይህ የመለያ ቃለ መጠይቅ ሲሆን ሰለናንተ የግል መረጃ (ስም፣ ዜግነት፣ የልደት ቀን፤ ወዘተ)፣ ቤተሰብን የሚመለከት መረጃ (የልጅ ወይም የባለቤት ወዘተ) እና ትንሽ መረጃ ጥገኝነት ስለጠየቁበት ምክንያት። እነሱ የሚጠይቁት ወሳኙ ጥያቄ ወደ ዩናይትድ ኪንግዶም የመጣችሁበትን ጉዞ የተመለከተ ነው። በሌላ የአውሮፓ አገር በኩል ወደ እንግሊዝ (ዩናይትድ ኪንግዶም) እንደገባችሁ ከነገራችኋቸው ወደዚያ ሊመልሷችሁ ይሞክራሉ።
ሁለተኛ ቃለ መጠይቅ :- ይህ ወሳኙ ቃለ መጠይቅ ሲሆን የጥገኝነት ጥያቄ ቃለ መጠይቅ በመባልም ይታወቃል።፡ይህ ዋናው ቃለ መጠይቅ ሲሆን የጥገኝነት ጉዳያችሁ ላይ ያተኩራል። ረጅም እና ከባድ ቃለ መጠይቅ ነው። በቃለ መጠይቁ ወቅት ስህተት እንድትሰሩ ወይም እርስ በርሱ የሚፃረር ነገር እንደትናገሩ ለማስገደድ አንድን ጥያቄ በተለያየ መልኩ ይጠይቋችኋል። ረጋ ብላችሁ መረጃችሁን ስጡ። ከፈለጋችሁ በቃለ መጠይቅ ውቅት እረፍት መጠየቅ ትችላላችሁ፤ እንደገና ለምሳሌ ስሜታችሁ ጥሩ ካልሆነ ወይም ከሚናገሩት ዉስጥ የሆነ ነገር ካልገባችሁ። አስተርጓሚ እንዲመደብላችሁ የመጠየቅ መብት አላችሁ። በቃለ መጠይቁ ወቅት የሰጣችሁትን መረጃ የፅሑፍ ቅጂ የማግኘት መብት አላችሁ። ነገር ግን የይዘቱን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ከመፈረማችሁ በፊት መጀመሪያ ልታነቡት ይገባል። ከሁለተኛው ቃለ መጠይቃችሁ በኋላ ጥያቄያችሁ ተቀባይነት ማግኘቱን ወይም አለማግኘቱን የሚያሳወቅ ውሳኔ ይደርሳችኋል።
ማስረጃ
ከቃለ መጠይቅ በፊት በተቻለ መጠን ብዙ ማስረጃ ማዘጋጀት የተሻለ ነው። ይህም የሚከተሉትን ሊያካትት ይችል ይሆናል :-
ማንነትን የሚገልፁ ወረቀቶች
ጠቃሚ የጋዜጣ ፅሑፎች
የግድያ ዛቻ ወይም የማስፈራሪያ ደብዳቤዎች
የፓርቲ ወይም ድርጅት አባልነት መታወቂያ
አባል ከሆናችሁበት የፖለቲካ / የሃይማኖት / የማህበራዊ ቡድን ሌሎች አባላት የተላኩና የናንተን አባልነት ወይም በአባልነታችሁ ምክንያት የተቃጠባችሁን አደጋ የሚያስረግጡ ደብዳቤዎች።
እናንተን ለማሰር የወጣ የእስር ትዕዛዝ
የፍርድ ቤት መጥሪያ ወረቀት
የሕክምና ወይም የሕግ ሪፖርቶች
ከጓደኞች ወይም አፍቃሪዎች የተላከ የፅሑፍ ቃል (በወሲብ ባሕሪዎ ምክንያት ጥገኝነት ጠይቀው ከሆነ)።
ከነዚህ ማስረጃዎች የተፃፉበትን ቀን የሚገልፁ፣ የተፈረመባቸው እና በሁለት ሌሎች ሰዎች መመስከር አለበት። እነዚህም መስክሮች ዝርዝር የግል መረጃቸውን እና የመታወቂያ ካርዳቸውን ፎቶ ኮፒ (ቅጂ) መስጠት አለባቸው።
በተልኮ የሚደርሳችሁን ማስረጃ በተመለከተ በፖስታ ቤት ተመዝግቦ የሚደርሳችሁን ኦሪጂናል እና ታሽጐ የመጣበትን ኤንቨሎፕ አስቀምጡ። የላካላችሁ ሰው ደብዳቤዉ ሲደርሳቸው የተመዝገበበትን ቁጥር ላኩለት እና በትክክል መደርሱን አረጋግጡ። የጐደለ ማስረጃ ካለ አሁን ለምን ሊደርስ እንዳልቻለ አስረዱ (ለምሳሌ ምንም ዓይነት የፖስታ መገናኛ ዘዴ በሀገሩ ወይም በክልሉ ያለመኖሩ።) ከተቻለ ከቃለ መጠይቁ በፊት የሕግ ባለሙያ ወይም ጠበቃ አግኙና በማስረጃዎቻቸው ላይ ተወያዩ።
የሚጠበቁ ውጤቶች
ስደተኛ ከሆናችሁ አምስት ዓመታት የመቆየት ፍቃድ ያሰጣችኋል። የመስራት፣ ከመንግሥት የሚገኙ ጥቅማ ጥቅሞችን የማግኘት እና ከትውልድ ሀገራችሁ በስተቀር ወደ ሌሎች ሀገራት የመሄድ መብት አላችሁ።፡ከአምስት ዓመታት በኋላ በሀገራችሁ ያለው ሁኔታ ከተሻለ ወደዚያው ሊመልሷችሁ ይችላሉ። ካልተሻሻለ ደግሞ ለተጨማሪ ለሌላ 5 ዓመታት ማመልከት ትችላላችሁ። በእንግሊዝ በሕጋዊ ነዋሪነት ለ10 ተከታታይ ዓመታት ከኖራችሁ እዚያው ለመቅረት (ቋሚ ነዋሪነት) ማመልከት ትችላላችሁ።
የእንግሊዝ ፓስፖርት ማግኘት « ናቹራላይዜሽን » ይባላል። በሕጋዊ መንገድ ከ5ዓመታት በላይ በእንግሊዝ ከኖራችሁ በኋላ ለናቹራላይዜሽን ማመልከት ትችላላችሁ። ነገር ግን ወዲያውኑ አይሰጥም። በጣም ውድ እና ፈተና ያለው ሲሆን ጥሩ ባሕሪ ወይም ሥነ-ምግባር እንዳላችሁ ማሳየት መቻላችሁን ከግምት ያስገባል።
ጥገኝነት ካልተሰጣችሁ ለሰብዓዊ ጥበቃ ወይም እንደ ግለሰቡ ሁኔታ በቆይታ ታይቶ ለሚሰጥ ፍቃድ ማመልከት ትችላላችሁ። በሀገራችሁ ወገን የማይለይ ግጭት ምክንያት ሕይወታችሁ አደጋ ላይ ከሆነ (ለምሳሌ ጦርነት ካለ) የሰብዓዊ ጥበቃ ለ 5 ዓመት ይሰጣል። እንደ ግለሰቡ ሁኔታ በቆይታ ታይቶ የሚሰጥ ፍቃድ ለ3 ዓመት በተለያዩ ምክንያት ሊሰጥ ይችላል። (ለምሳሌ ግለሰቡ ለአቅመ አዳም/አቅመ ሔዋን ያልደርሰ ከሆነ)። እነዚህን አማራጮች በተመለከተ የጥገኝነት ጥይቄያችሁ አካል (እንደሆኑ) አድርጋችሁ ከጠበቃችሁ ጋር ተነጋገሩባቸው። ለጥገኝነት ካመለከታችሁበት ጊዜ ጀምሮ ሰብዓዊ ጥበቃ የምታገኙበት መንገድ አብሮ ሊታይ ይችላል፤ ነገር ግን ይህን በተመለከተ ጠበቃችሁን መጠየቃችሁን አትርሱ።
ወይም
ጥገኝነት ካልተሰጣችሁ እናንተን ከእንግሊዝ አገር የሚያስወጡበትን ሂደት ይጀምራሉ ማለት ነው። የመልቀቂያ መመሪያ (የምትወጡበት ቀን እና ሰዓት) ይሰጣችኋል። ቀደም ብለው በማቆያ ማዕከል አስገብተዋችሁ ካልሆነ ከዚህ በኋላ ይዘው ሊያስገቧችሁ ይችላሉ። አብዛኞቹ የጥገኝነት ጠያቄዎች ተቀባይነት የላገኙ ቢሆንም እንኳ አብዛኛው ጊዜ ለጥገኝነት ማመልከት የተሻለ አማራጭ ነው። አዎንታዊ መልስ ካላገኛችሁ በአስር ቀናት ውስጥ አቤቱታ ማቅረብ ትችላላችሁ (ውሳኔ ከተለጠፈ ከሁለት ቀናት በኋላ ጀምሮ ዉሳኔዉ እንደደረሳችሁ/እንዳወቃችሁት ይታሰባል)። በማቆያ ማዕከል ውስጥ ያሉ ደግሞ ውሳኔው ከተለጠፈ ከ5 ቀናት በኋላ ጀምሮ እንዳወቁት ተደርጐ ይታሰባል። ተጨማሪ ማስረጃ ማቅረብ ሊያስፈልጋችሁ ይችል ይሆናል ወይም እንደ አዲስ የጥገኝነት ጥያቄ ማቅረብ ሊያስፈልጋችሁ ይችል ይሆናል (በሌላ የተለያዩ ምክንያቶች ጥገኝነት መጠየቅ ማለት ነው)። ከሀገር የመውጣታችሁን ውሳኔ በመቃወም ጉዳያችሁ እንደገና በፍርድ ቤት እንዲታይ ማመልከት ትችላላችሁ። እነዚህን አማራጮች ከጠበቃችሁ ጋር ተወያዩባቸው። ጠበቃችሁ በእናንተ ጉዳይ መቀጠል ካልፈለገ ሌላ ጠበቃ ለማግኘት ሞክሩ።
መያዝ (ዲቴንሽን)
ለአስተዳደራዊ ጉዳይ መያዝ ሊፈፀም ይሚችለው ሰዎች ወደ ዩናይትድ ኪንግዶም (ኢንግሊዝ) በሕገወጥ መንገድ እንዳይገቡ ለማድረግ ወይም ሰዎችን ከእንግሊዝ  እንዲወጡ ለማድረግ ነው። የአንድ ሰው መያዝ እነዚህን የሕግ መሠረቶች የተከተለ መሆን አለበት። በንድፈ ሃሳብ ደረጃ መያዝ ዘፈቀዳዊ ሊሆን አይችልም። በእንግሊዝ ሀገር የሰዎችን መያዝ በተመለከተ የተወሰነ የጊዜ ገደብ የለም። « ኤይ.ኤስ 91 አር » (IS91R) የሚባል የተያዛችሁበትን ምክንያት የሚያስረዳ ወረቀት ሊሰጣችሁ ይገባል። ተይዛችሁ ከቆያችሁ ደግሞ መቆየታችሁ ያስፈለገበትን ምክንያት የሚያስረዳ « አይ.ኤፍ 151 ኤፍ » (IF151F) የሚባል ወራዊ ሪፖርት ሊሰጣችሁ ይገባል። በተጨማሪም « ቤይል ሰመሪ » (Bail summary, ከእስር ለመፈታት የተከፈለ ገንዘብ መግለጫ) ከእስር ቤት ለመውጣት ባመለከታችሁበት ጊዜ ጉዳያችሁን በሚከታተለዉ ሰራተኛ የሚዘጋጅ ሰነድ ሊሰጣችሁ ይገባል። ከእስር ለመፈታት አመልካታችሁ ከሆነ ይህን የሚመልከቱትን ወረቀቶች፣ ከእስር እንዳትፈቱ የወሰኑበት የፍርድ ቤት ወረቀት እና ከእስር እንዳትፈቱ የተወስነበትን ምክንያት የሚያስረዱ ወረቀቶች መያዝ እና ማጣቀስ ይገባችኋል። እነሱ ልጆችን፣ አረጋዊያንን፣ ነፍሰ ጡር ሴቶችን፣ ከባድ የአካል ወይም የአዕምሮ ጤና ችግር ያለባቸውን ሰዎች፣ ከዚህ በፊት የከፍተኛ ስቃይ ስለባ የሆኑ ሰዎችን፣ በሕገ ወጥ አዘዋዋሪዎች የመጡ ሰዎችን እና ከፍተኛ የአካል ጉዳት ያለባቸውን ሰዎች እንዲያስሩ አይጠበቅም። እንደ እውነቱ ከሆነ ግን ያስራሉ፤ በተለይ የአዕምሮ ጤና ችግር ያለባቸውን ሰዎች፣ ለአካለ መጠን ያልደረሱትን እና ከዚህ በፊት ከፍተኛ ስቃይ የደረሰባቸውን ሰዎች ያስራሉ።
ቤይል (Bail)
አንዳንዴ አሳሪው ቢሮ  ታሳሪውን በጊዜያዊነት ሊያስር ይችላል።፡ማንኛውም ታሳሪ በዚህ መልኩ ለመፈታት ጉዳዩን ከዚያው ሠራተኛ መጠየቅ ይችላል። ይህ ሊሆን ካልቻለ በክፍያ ለመፈታት የምታመለክቱ ከሆነ ለዚህ የሚጠቅማችሁን ደብዳቤዎች ማስቀመት ይገባችኋል። ይህም ከእስር ለመውጣት የወስዳችሁትን ጥረት ለማሳየት ይረዳል፤ ወይም ከቢሮው መልስ ካላገኛችሁ በቂ ምክንያት እንዳላችሁ ለማሳየት ይረዳችኋል። በአብዛኛው ማለትም ታሳሪዎች በእንግሊዝ አገር ከ7 ቀናት ለበለጠ ጊዜ ቆይተው ከሆነ ገንዘብ ከፍሎ ለመፈታት ማመልከት ይችላሉ።
ጠቃሚ አድራሻዎች
የሕግ መረጃ ለማግኘት :-
ukba.homeoffice.gou.uk
freemovement.wordpress.com (ስደትን የተመለከቱ ሕጐችን የሚዳሰስ ጦማር)
languages.refugeecouncil.org.uk (የስደተኞች ጉዳይን በተመለከተ በብዙ ቋንቋዎች መረጃን የሚሰጥ ድረ-ገፅ)
ጠቃሚ ምክሮች
refugeecouncil.org.uk (በብዙ ቋንቋንዎች የሚሰጠውን ነፃ የምክር አገልግሎት ለማግኘት በ 0808-808-2255 ደውሉ)
asylumaid.org.uk (የምክር አገልግሎት የምታገኙት ማክሰኞ ከ7እስከ 10 ሰዓት ከሰዓት በኋላ /1-4 p.m.)
lawcentres.org.uk
citizensadvice.org.uk
praxis.org.uk (ምክር እና ትርጉም፤ ቤትናል ግራን)
airecentre.org (በአውሮፓ እና ደብሊን ጉዳዮች ምክር)
kalayaan.org.uk (ስደተኛ ለሆኑ ሰራተኞች ምክር)
freedomfromtorture.org (ሕጋዊ የሕክምና ሪፖርቶችን የሚያዘጋጅ ተቋም)
medicaljustice.org.uk (ለሕጋዊ የሕክምና ሪፖርቶች)
hackneymigrantcentre.org.uk
migranthelpline.org.uk
biduk.org

ልዩ ጉዳዮች
ከዚህ በፊት የስቃይ ጉዳተኛ የሆንኩ ቢሆንስ ?
ከዚህ በፊት ስቃይ ደርሶባችሁ ከሆነ በየትኛውም የአውሮፓ ሕብረት አባል አገር በትሆኑ ይህን በቃለ መጠይቁ ውስጥ ግልፅ ልታደርጉ ይገባል። ስለስቃይ ማውራት ሊከብድ ይችላል። ነገር ግን በተቻለ መጠን ቶሎ ማሳወቅ ጠቃሚ ነው። ከዚህ በፊት ስቃይ የደረሰባቸው ሰዎች በአውሮፓ ሕብረት የጥገኝነት ጉዳይ አስተያየት እንደ ተጋላጭ ሰዎች ይቆጠራሉ፤ ምናልባትም ከሌሎች የጥገኝነት አመልካቶች በተለየ ሁኔታ ሊታዩ ይችላሉ (ለምሳሌ ሊታሰሩ አይገባም)።
የወንድ-ለወንድ / የሴት-ለሴት / ከወንድም-ከሴትም ጋር ወሲብ የማድረግ ባህሪ ያለኝ ቢሆንስ ?
ከላይ በርዕሱ የተጠቀሱት ባህሪያት ካላችሁ በነሱ ምክንያት አንዳንዴ የጥገኝነት ጥያቄ ማቅረብ ይቻላል። በአውሮፓ ሕብረት የጥገኝነት ሕግ መሠረት እነዚህ ባሕሪያት ያላቸው ሰዎች የአንድ ሕብረተሰብ ክፍል አባል በመሆናቸው ጥቃት የሚደርሰባቸው ናቸዉ በማለት ይቀበላቸዋል (የጄኔቭ ደንብ)። እነዚህን የወሲብ ባህሪያቶች መሠረት አድረገው የጥገኝነት ጥያቄ ስታቀርቡ በእነዚህ የወሲብ ባህሪያት የተነሳ በትውልድ ሀገራችሁ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ (ልትቀጡ እንደምትችሉ) እንደምትቀጡ ማረጋግጫ የማቅረብ ግዴታ አለባችሁ።
የተለያዩ ሀገራት እነዚህ ባህሪያት ያላቸው ስደተኞች ወይም የተመሳሳይ ፆታ ወሲብ ግንኙነት ወንጀል ከሆነበት ሀገር የመጡ ሰዎችን የሚይዙበትና እንዲሁም ከፆታ ከጓደኞቻቸው (ፍቅረኛቸው) ጋር መቀላቀል ይችላሉ ወይስ አይችሉም የሚለውን  የሚዳኙበት የየራሳቸዉ የተለያዩ ሕጐች አሏቸው።
ጀርመን :- በነዚህ የወሲብ ባህሪያት ምክንያት በጀርመን ሀገር ጥገኝነት የሚጠይቅ ስደተኛ በነዚህ ባህሪያት የተነሳ በሀገሩ የሚደርስበት ቅጣት « ከባድ እና ሊቀበሉት የማይችሉት እና በማንኛውም መስፈርት ምክንያት የለሽ » መሆኑን የማረጋገጥ ወይም የማሳየት ግዴታ አለበት።
ፈረንሳይ :- ማህበረሰቡ ወግ አጥባቂ ከሆነ ሀገር የመጣን ስደተኛ በእነዚህ የወሲብ ባህሪያት ምክንያት፤ ምንም እንኳን ግለሰቡ የወንጀል ክስ ያልቀረበበት ቢሆንም በማህብረሰቡ ውስጥ  የተመሳሳይ ፆታ ወሲብ ባህርይ/ድርጊት ላይ ያለውን/የሚደርሰዉን መጠን ሰፊ ማህበራዊ ውግዘት የማሳየት ግዴታ አለበት። ይህን በማረጋግጥ ብቻ የጥገኝነት ጥያቄው ተቀባይነት ሊያገኝ ይችላል።
የፈረንሳይ ፍርድ ቤቶች የጥገኝነት ጥያቄ ጉዳይ እነዚህ የወሲብ ባህሪያት ያሏቸውን ሰዎች በግልፅ እንደ አንድ ተጠቂ የማህበረሰብ ክፍል ተመልክቷቸዋል።
ፈረንሳይ የስደተኞች ምንጭ የሆኑ እና እነዚህን የወሲብ ባህሪያት የሚቀጡ ማህበረሰቦች ያሉባቸውን ሀገራት ዝርዝር አውጥታለች። በዚህ ዝርዝር ከተጠቀሱት አብዛኞቹ ሀገራት ውስጥ የተመሳሳይ ፆታ ወሲብ ወንጀል ነው።
ሉክሳምቡርግ :- በሉክሳምቡርግ የጥገኝነት ጥያቄን የሚመለከተው ወኪል ድርጅት በተመሳሳይ ፆታ ወሲብ ምክንያት የሚደርስ ጥቃት ግለሰባዊ እና ተጠቂዎቹም በሀገራቸው ሌላኛው አካባቢ በመሄድ ከጥቃቱ ሊያመልጡ ይችላሉ በማለት ወስኗል። የሉክሳምቡርግ ሕግ የተመሳሳይ ፆታ ፍቅረኛ (ተጓዳኝ) ያለውን የጥገኝነት አመልካች ስደተኛ ተጓዳኙን እንደ ቤተሰብ አባል ይቆጥርለታል። ይህ የሚሆነው ግን የመጣበት ሀገር የሁለቱን ፆታዊ ግንኙነት ሲያረጋገጥ ብቻ ነው።
ቤልጅየም :- በቤልጅየም ዉስጥ ከወሲብ ባህሪ ጋር የተያያዘ የጥገኝነት ጥያቄ በቂ ምክንያት እንደሆነ ይረዳሉ። በስደተኞች እና በመንግሥት-አልባ-አገር ሰዎች ጉዳይ ዋና ከሚሽነር ቢሮ ውስጥ ከፆታ ወይም ወሲብ ባህሪያት እና ማንነት ጋር በተያያዘ የሚቀርቡ የጥገኝነት ጥያቄዎችን የሚመለከት ሠራተኛ አለ።
ኔዘላንድ :- በኔዘርላንድ የጥገኝነት ፖሊሲ መሠረት በፆታ እና በወሲብ ባሕሪያት ምክንያት ጥገኝነት እንደሚሰጥ በግልፅ ተቀሞጧል። ነገር ግን ጥገኝነት ጠያቂው ሰው ከመጣበት ሀገር ውስጥ የተመሳሳይ ፆታ ወሲብ ባህሪ ወንጀል መሆኑ ጥገኝነት ለመስጠት በቂ ምክንያት አይደለም። ከፍተኛ አካላዊ ስቃይ እና እንግልት ለደረሰባቸው ሰዎች ኔዘርላንድ ተጨማሪ ጥበቃ ታደርጋለች። በሕጉ አግባብ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ባሕሪያት ያላቸው ሰዎች ይህን ባህሪያቸውን በትውልድ ሀገራቸው የመደበቅ ግዴታ ካለባቸው በስደት ካሉበት ሀገር እንዲወጡ ሊደረግ አይገባም። ለጥገኝነት ጥያቄ ጉዳይ ያልተጋቡ ተፋቃሪዎች እንደ አንድ ቤተሰብ አባላት ይቆጠራሉ።
ዴንማርክ :- የዴንማርክ የጥገኝነት ሕግ ፆታዊ (የወሲብ) ባሕሪያት ሰዎችን ለመሰደድ እና ጥገኝነት ለመጠየቅ የሚያደርሱ ናቸው ብሎ አይቀበልም። ነገር ግን በዚህ ምክንያት ሀገራቸው ቢመለሱ የሞት ወይም ተከፍተኛ አካላዊ ስቃይ (ኢሰብዓዊ እና አዋራጅ አመለካከት እና አያያዝን ጨምሮ) ስለሚደርስባቸው ሰዎች የዴንማርክ መንግስት የመኖሪያ ፍቃድ ይሰጣል። የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ባህሪያ ያላቸው ሰዎች ላይ የሚደርስ ማንኛውም የግል ጥቃት በአጠቃላይ እንደ ወንጀል ይታያል እንጂ ለስደት ያበቃል ተብሎ አይታመንም። ያልተጋቡ የተመሳሳይ ፆታ ተፋቃሪዎች እውቅና ለማግኘት አብሮ የመኖር ግዴታ አለባቸው።
ስዊድን :-የስዊድን የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት መብቶች ፊዴሬሽን ለስዊድን የስደተኞች ጉዳይ ቦርድ አባላት የፆታ ባህሪይ እና ፆታዊ ማንነትን በሚመለከት ስልጠና ስጥቷል። የስልጠናው ዓላማ ከግንዛቤ ማነስ የሚመጡ ችግሮችን ለመቀነስ ነው። ከዚህ በተጨማሪ ፌዴሬሽኑ በየጊዜው የጥገኝነት ጣቢያዎችን (ጥገኝነት ፈላጊዎች ለጥያቄያቸው የመጨረሻ ውሳኔ እስኪያገኙ ድረስ ሊኖሩ የሚችሉበት ነገር ግን የማይገደዱበት ማዕከል ነው) ይጐበኛል። ፌዴሬሽኑ ከዚህ በፊት የተመሳሳይ ፆታና ወሲብ ባህሪያት ጋር በተያያዘ ጥገኝነት የጠየቁ እና ወደ ሀገራቸው ቢመለሱ ከፍተኛ ጥቃት እንደሚደርስባቸው በግልፅ እየታወቁ ከሀገር እንዲወጡ የተወስነባቸው ጥገኘነት አመልካቶች  መኖራቸውን በሪፖርቱ ገልጿል። የተመሳሳይ ፆታ ተጋቢዎች፤ ጥንዶች ወይም ተፋቃሪዎች አንደኛው የሌላኛው ጥገኝነት ጠያቂ የቤተሰብ አባል እንደሆኑ ግንዛቤ ይወሰዳል።
ዩናይትድ ኪንግዶም (እንግሊዝ) :- እንግሊዝ ውስጥ ከተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ጋር ተያይዘው የቀረቡ የጥገኝነት ጥያቄዎች ምንም እንኳ ከመጡበት ሀገር የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት በሚያደርጉ ሰዎች ጥላቻ ቢኖርም እና እነዚህ ሀገራት የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ወንጅል መሆኑን ቢደነግጉም፤ በዚህ ምክንያት ያመለከቱ አብዛኞቹ አመልካቶች ጥገኝነት አልተሰጣቸውም። ምንም እንኳ በትውልድ ሀገራችሁ በድብቅ ለመኖር (በእነዚህ ባህሪያት የተነሳ) እንደሚከብዳችሁ ብታስረዱም እንኳ አብዛኛውን ጊዜ ጥገኝነት አታገኙም።

በአውሮፓ ውስጥ ለመጓዝ ጠቃሚ ምክሮች
አውሮፓ ውስጥ በነፃነት መጓዝ እችላለሁ ?
ምንም እንኳ በሀሳብ ደረጃ ሸንገን ክልል የሚባል በአብዛኛው የአውሮፓ ክፍል ሰዎች በነፃነት የሚጓዙበት ክልል ቢኖርም፣ ምናልባት ከዚህ ቀደም አስተውላችሁ ሊሆን እንደሚችለው በምትጓዙበት ወቅት በተለይ የሀገር ድንበር ስታቋርጡ የፓስፖርት ቁጥጥር ሁሌም ሊኖር ይችላል።
ለመጓዝ የተሻለው አማራጭ / መንገድ ምንድን ነው ?
ከተቻለ በመኪና መጓዝ የተሻለ ነው፤ ቁጥጥሩ በባቡር እና በአውቶቡስ ላይ ካለው ቁጥጥር ያነሰ ሊሆን ይችላል። ሌላው አማራጭ በቤት መኪናቸው ለሚጓዙ ባለመኪናዎች ከፍሎ አብሮ መጓዝ የተለመደ ስለሆነ በዚያ መጠቀም ነው። የእነዚህን ባለመኪና መንገደኞች አድራሻ ከ « blablacar.com » ወይም « covoiturage.fr » ድረ ገፆች ላይ ማግኘት ይቻላል። በርግጥ አንዳንዴ ሹፌሩ ለፖሊስ ሊያሳውቅ እና ሊያሲዛችሁ የሚችልበት አደጋ ሊኖር ይችላል።
ታክሲ መጠቀም ይቻላል ግን ረጅም ርቀት የምትጓዙ ከሆነ ዋጋዉ በጣም ውድ ይሆናል። እንዲሁም ወረቀት የሌላቸውን ሰዎች ለፖሊስ የሚያጋልጡ የታክሲ ሹፌሮች እንዳሉ ስምተናል። በአብዛኛው የፓስፖርት ቁጥጥር የሚደረገው የሀገር ድንበር ተሻጋሪ በሆኑ አውቶቡሶች እና ባቡሮች ላይ ነው። ነገር ግን ሁል ጊዜ ቁጥጥር አይኖርም ስለዚህ እናንተም እድላችሁን ሞክሩ። እንደ « uk.megabus.com » ፣ « eurolines.com » እና ሌሎችም የአውቶቡስ ድርጅቶች አሉ። እኛ እስከምናውቀው ድረስ ረጅም ርቀት ከሚጓዙት አውቶቡሶች ይልቅ አጭር ረቀት የሚጓዙት አውቶቡሶች ላይ ቁጥጥሩ ሊያንስ ወይም ላይኖር የሚችልበት አጋጣሚ የሰፋ ነው። ስለዚህ በአንድ አውቶቡስ ረጅም ርቀት ከምትጓዙ ይልቅ አጭር ርቀት በሚጓዙት አየቀጠላችሁ ብዙ ጉዞ በማድረግ ይምትፈልጉበት ቦታ መደረስ የተሻለ ነው።
በፈረንሳይ ውስጥ ብቻ  የምትጓዙ ከሆነ (የፈረንሳይን ድንበር የማትሻገሩ ከሆነ) ብዙ ሳይከፍሉ በባቡር የሚሄዱ ሰዎች አሉ። በርግጥ ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚመጣ አደጋ ሁሌም አለ !
በምጓዝበት ወቅት ሌላ ላስብበት የሚገባኝ ነገር ምንድን ነው ?
የምትፈልጉበት ቦታ ከደረሳችሁ በኋላ እንዴት እዚያ እንደደረሳችሁ የሚያስረዳ ታሪክ የማዘጋጀት ግዴታ አለባችሁ። ምናልባት የጥገኝነት ጥያቄ ማቅረብ የምትችሉት መጀመሪያ የገባችሁበት የአውሮፓ ሀገር ብቻ ሊሆን እንደሚችልም አስታውሱ።
ስለዚህ ለምሳሌ በስዊድን ሀገር ጥገኝነት እየጠየቃችሁ ቢሆን በሌሎች የአውሮፓ ሀገሮች ሳትቆዩ እንዴት ስዊድን እንደ ደረሳችሁ ማስረዳት መቻል ይገባችኋል። ከደረሳችሁ በኋላ የምትፈልጉት ወዲያውኑ ጥገኝነት መጠየቅ ነው ወይስ ትንሽ ቀን መጠበቅ የሚለውን አስቡ።፡በሕግ አግባብ የጥገኝነት ጥያቄያችሁን በተቻለ መጠን ከደረሳችሁ በኋላ ወዲያውኑ ማቅረብ አለባችሁ። ነገር ግን ጥገኝነት ከመጠየቃችሁ በፊት የሕግ አማካሪዎችን ማነጋገር አለባችሁ። ወዲያው እንደ ደረሳችሁ ለምን እንዳላመለከታችሁ የማስረዳት ግዴታ አለባችሁ (ሕገ ወጥ አዘዋዋሪዎች ጥቂት ቀን እንድትቆዩ ነግረዋችሁ ከነበረ እና በሌላ ተመሳሳይ ምክንያቶች ከሆነም ይህን የማስረዳት ግዴታ አለባችሁ)። በራሳችሁ እርግጠኞች ካልሆናችሁ ጥገኝነት በመጠየቅ ጉዳይ ስደተኞችን የሚረዱ እና የሚደገፍ ድርጅቶችን አግኙና አነጋግሩ።

ፈረንሳይ
አብዛኛዉን ጊዜ ቁጥጥር የሚደረግባቸዉ ቦታዎች የትኞቹ ናቸው ?
የባቡር ጣቢያዎች፣ የሕዝብ ትራንስፖርት የጉዞ ትኬት መቆጣጠሪያዎች፣ ከአንድ ጉዞ ወደ ሌላ ጉዞ መሻጋገሪያ ቦታዎች፣ የሕዝብና የቱሪስት ቦታዎች፣ መንገድ ላይ እና ምርጫ ጣቢያዎች።
የጥገኝነት ጥያቄ ሂደት እንዴት ይፈፀማል ?
መጀመሪያ የፈረንሳይ የስደተኞች ጉዳይ ቢሮ (OFII – Office Français de l’Immigration et de l’Intégration) ማነጋገር ትችላላችሁ። እነሱ በሂደቱ ላይ ሊረዷችሁ የሚችሉትን እና እውቅና ያላቸውን ድርጅቶች አድራሻ ይሰጧችኋል። በተሻለ ሁኔታ ሊረዱዋችሁ የሚችሉ ነፃ ድርጅቶችን ማግኘት ትፈልጉ ይሆናል።፡ጠበቃም ማነጋገር ትችላላችሁ፤ ወይም ደግሞ ያለማንም እርዳታ እራሳችሁ ማመልከት ትችላላችሁ። በፈረንሳይ ውስጥ የፈረንሳይ የስደተኞችና ዜግነት የሌላቸዉ ሰዎች ጥበቃ ቢሮ (OFPRA – Office Français de Protection des Réfugiés et des Apatrides) የጥገኝነት ጥያቄያችሁን ከተቀበለ በኋላ ስደተኛ ናችሁ ወይም አይደላችሁም የሚለውን ይወስናል።
ፕሬፌክቱር (በየወረዳ የአስተዳደር ቢሮ) ለፈረንሳይ የስደተኞችና ዜግነት የሌላቸዉ ሰዎች ጥበቃ ቢሮ የምትሰጡትን የመጀመሪያዎቹን ወረቀቶች ከመስጠት ባሻገር ጊዜያዊ የመኖሪያ ፍቃድ የማግኘት ዕድላችሁን ይከታተላል (ይመረምራል)።
በፈረንሳይ ሁለት ዓይነት የጥገኝነት ማመልከቻዎች አሉ።
የተለመደው ሂደት፤ በ21 ቀናት ውስጥ ማመልከቻውን ለፈረንሳይ የስደተኞች እና ዜግነት የሌላቸዉ ሰዎች ጥበቃ ቢሮ (OFPRA) መላክ ነዉ።
በበፈጣን ሂደት ሊታይ የሚችለው :-
ደህና ከሚባሉት አገራት የመጣችሁ ከሆነ (በየካቲት 2015 በመጣው ማውጫ መሠረት ደህና የሚባሉት አገራት ዝርዝር የሚያካትተው አልባኒያ፣ አርሜንያ፣ ቤኒን፣ ቦስኒያ ሄርዜጐቪና፣ ኬፕ ቨርድ፣ ጆርጂያ፣ ጋና፣ ሕንድ፣ መቄዶንያ፣ ሞሪሽየስ፣ ሞልዶቫ፣ ሞንጐሊያ፣ ሞንቴኔግሮ፣ ሴኔጋል፣ ሰርቢያ፣ ታንዛኒያ ናቸው።)
ፈረንሳይ መቆየታችሁ ለሕዝብ ደህንነት አደገኛ ነው ብላ ካሰበች።
የጥገኝነት ማመልከቻችሁ በአጭበርባሪ ሰነዶች/ማስረጃ የተደገፈ ከሆነ (የማጭበርበር ዓላማ ወይም የደበዘዘ የጣት አሻራ)
ፈጣን ሂደት ካጋጠማችሁ በ15 ቀናት ውስጥ ለፈረንሳይ የስደተኞች እና ዜግነት የሌላቸዉ ሰዎች ጥበቃ ቢሮ (OFPRA) ማመልከት አለባችሁ። በቁጥጥር ስር ውላችሁ ከሆነ ደግሞ በ5 ቀናት ውስጥ ማመልከት አለባችሁ። ማመልከቻችሁን ለምርመራ ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የፈረንሳይ የስደተኞች እና ዜግነት የሌላቸዉ ሰዎች ጥበቃ ቢሮ 15 ቀናት (በቁጥጥር ማዕከል ከሆናችሁ 96ሰዓታት) ይፈልጋል።
ደብሊን ሦስተኛ ደንብ :- ፈረንሳይ የደብሊን ደንብን ፈርማለች። ከዚህ በፊት በሌላ ሀገር የጣት አሻራ ሰጥታችሁ ከሆነ ይህ ሀገር የጥገኝነት ጥያቄያችሁን የማየት ኃላፊነት አለበት። ፈረንሳይ ወደዚህ ሀገር ልትመልሳችሁ ትሞክራለች።
ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል ?
በትክክል ለመናገር ይከብዳል።፡በፈረንሳይ የሰደተኞችና ዜግነት የሌላቸዉ ሰዎች ጥበቃ ቢሮ (OFPRA) ለሚደረገው ሂደት በአብዛኛው ከ6 ወራት እስከ አንድ ዓመት ይወስዳል። በጥገኝነት መብቶች ብሄራዊ ፍርድ ቤት (CNDA – Cour Nationale du Droit d’Asile) የሚደረገው ሂደት የሚወስደዉ ጊዜ ከሞላ ጐደል ተመሳሳይ ነው።
ውሳኔ እስከማገኝ ድረስ እንዴት መኖር እችላለሁ ? አበል አገኛለሁ ?
በሕጉ መሠረት መንግስት ቤት ሊሰጣችሁ ይገባል (የጥገኝነት ፈላጊዎች የመኖሪያ ማዕከል – CADA – Centre d’Accueil des Demandeurs d’Asile) እንዳንዴ ደግሞ በሆቴል ወይም በድንገተኛ የመጠለያ ማዕከል ሊሆን ይችላል። የአኗኗር ሁኔታችሁን (ብቸኛ ናችሁ ወይስ ቤተሰብ አላችሁ የሚለዉን) መሠረት ያደረገ ትንሽ ገንዘብም ይሰጣችኋል። እንደ እውነታው ከሆነ ግን ከፍተኛ የሆነ የቤት እጥረት አለ፤ እናም በክፍያ ለመኖር ልትገደዱ ትችላላችሁ፤ በወር እስከ 320 ዩሮ (€)። ይህን አማራጭ ባትቀበሉና ቤቱን ብትለቁ ማንኛውም ከመንግስት የሚደረግላችሁ እርዳታ ይቋረጣል።
በ « ፓስ » (PASS) ተቋም ነፃ የሕክምና አገልግሎት የማግኘት መብት አላችሁ (የጉዳያችሁ ሂደት እስከሚያልቅ ድረስ)። ጊዜያዊ የመኖሪያ ፍቃድ ካገኛችሁ ከ3 ወራት በኋላ ፓስ የመንግሥት ነፃ እርዳታ እንድታገኙ ሊረዳችሁ ይችላል።
አቤቱታ :-
የጥገኝነት ጥያቄያችሁ ተቀባይነት ካላገኘ በጥገኝነት መብቶች ብሄራዊ ፍርድ ቤት አቤቱታ ለማቅረብ የአንድ ወር ጊዜ ይኖራችኋል። ከጠበቃ የሕግ እርዳታ የማግኘት መብት አላችሁ። ጉዳያችሁ በፈጣን ሂደት የታየ ከሆነ ግን የሕግ እርዳታ የማግኘት መብት የላችሁም፤ አቤቱታ በምታቀርቡበት ጊዜም በማንኛውም ሰዓት ሊከሰት ከሚችል ከሀገር የመውጣት ግዴታ የሚያስጥላችሁ የለም።ነገር ግን በተለምዶ ባለስልጣናት እናንተን ከሀገር ለማስወጣት ከማስገደዳቸው በፊት የጉዳያችሁን የመጨረሻ ውሳኔ ይጠብቃሉ።
ዕድሜዬ ከ 18 ዓመት በታች ቢሆንስ ?
በወላጅ ወይም አሳዳጊ ስር ያሉ ሰዎች የሕግ ሁኔታ በወላጆቻቸዉ የህግ ሁኔታ ላይ የተመሰረተ ነዉ። ነገር ግን ወላጆቻቸው ወይም አሳዳጊዎቻቸዉ ከሀገር እንዲወጡ ቢደረግ 18 ዓመት ያልሞላቸዉ ልጆቻቸው ወይም ሌሎች የቤተሰብ አባላት መቆየት ይችላሉ (ወላጆቻቸው/ አሳዳጊዎቻቸው ከፈቀዱ)።
ከወላጆቹ ወይም አሳዳጊዎቹ ተነጥሎ ብቻውን ያለ ሰው ከሀገር እንዲወጣ ሊገደድ አይችልም። ይህ/ይህቺ ሰው በሌላ አውሮፓ አገር ከሚገኙ ወላጆቹ/ቿ ወይም አሳዳጊው/ዋ ወይም ዘመዱ/ዷ ጋር የመቀላቀል ዕድል ይኖረዋል/ይኖራታል። ከ18 ዓመታት በታች የሆነ ሰው ጥገኝነት ቢጠይቅ በማህበራዊ ሰራተኞች ከሚተዳደር ድንገተኛ ጊዜያዊ መጠለያ ቤት ሊያገኝ ይችላል/ትችላለች። የጥገኝነት ጥያቄው ተቀባይነት ቢያገኝ 18 ዓመት እስኪሞላው/ላት ድረስ በዚያ ሀገር ውስጥ የመቆየት መብት አለው/አላት። በሕገ ወጥ መንገድ ከቆየ/ከቆየች አሁንም በድንገተኛ ጊዜያዊ መጠለያ ውስጥ ቦታ ሊያገኝ/ልታገኝ ይችላል/ትችላለች።
ቤተሰቤስ?
ከ18 ዓመት በላይ ከሆንክ/ንሽ እና የጥገኝነት ጥያቄህ/ሽ በሂደት ላይ ከሆነ ዘመዶችህ (ባለቤትህ/ሽ እና ልጆችህ/ሽ) ወደ አንተ/አንቺ ሊመጡ የሚችሉበት ዕድል ሊኖር ይችላል። ዝምድናችሁን በማስረጃ ማረጋገጥ (የጋብቻ ወይም የልደት ሰርተፍኬት) ያስፈልጋል። ስደተኛ መሆንህን/ሽን ካረጋገጥክ/ሽ ልጆችህ/ሽ እና ባለቤትህ/ሽ ፈረንሳይ መምጣትና መኖር ይፈቀድላቸዋል። ሂደቱ ረጅም ጊዜ ሊወስድ ይችላል (እስከ 2 ዓመት)። ቤተሰብን የማቀላቀል ጉዳይ የጥገኝነት ጥያቄ ሳይሆን የአንድ ቤተሰብ አባላት አንድ ላይ እንዲኖሩ መርዳት ሲሆን ፍቃዱን የሚሰጠዉ አካል የግዴታ የፈረንሳይ የስደተኞች ጉዳይ ቢሮ  (OFII) መሆን አለበት።
መማርና መስራት እችላለሁ ?
ከአንድ ዓመት በኋላ ጊዜያዊ የስራ ፍቃድ መጠየቅ ይቻላል። ቅጥር ወይም የስራ ኮንትራት ማግኘት ያስፈልጋችኋል። ከዚያም ሕጉ ለውጭ ዜጐች በሚፈቅደው የስራ ሁኔታ መስራት ይቻላል። ከ16-18 ዓመት ዕድሜ ክልል ውስጥ ያለ ሰዉ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የስራ ፍቃድ ያገኛል/ታገኛለች። የስደተኝነት ወረቀት ካገኛችሁ እንደ ማንኛውም ዜጋ የመማርና የመስራት መብት አላችሁ።
ከ18 ዓመት በታች ክሆንክ/ሽ ትምህርት ቤት መግባት ይፈቀድልሃል/ሻል። ከ16 ዓመት በታች ከሆንክ/ሽ ግን ትምህርት ቤት የመግባት ግዴታ አለብህ/ሽ።
በመርህ ደረጃ የጥገኝነት ጥያቄያችሁ እየታየ እያለ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት መከታተል ትችላላችሁ። ጥሩ የፈረንሳይኛ ቋንቋ ችሎታ እና ለዩኒቨርሲቲው ማቅረብ የሚገቧችሁ አንዳንድ ወረቀቶች (የዲፕሎማ ስርተፍኬት፣ ወዘተ) ያስፈልጋሉ። የስደተኝነት ወረቀት ካለህ ፈረንሳይ ውስጥ መማር እና የሚያስፈልግህ/ሽ ከሆነ ከመንግስት የገንዘብ እርዳታ ማግኘት ይፈቀድልሃል/ሻል። አሁንም የፈረንሳይኛ ቋንቋ ችሎታ እና የትምህርት ማስረጃ ማቅረብ ያስፈልጋል። የፈረንሳይኛ ቋንቋ ትምህርት እና የስራ ስልጠና በስራ ማዕከል (pôle emploi) መውሰድ ትችላላችሁ።
ጥገኝነት ባይሰጡኝ ወይም ከሀገር እንድወጣ ብገደድ ምን ሊፈጠር ይችላል ?
የጥገኝነት ጥያቄያችሁ ውድቅ ከተደረገ ለጥገኝነት መብቶች ብሄራዊ ፍርድ ቤት (CNDA – Cour Nationale du Droit Asile) አቤቱታ ማቅረብ ትችላላችሁ። ለዚህም የሚበቃ የአንድ ወር ጊዜ ይኖራችኋል። ይህን ጊዜ ገደብ ከማሳለፍ ይልቅ ያልተሟላም ቢሆን ያላችሁን መረጃ ማቅረብ የተሻለ ነው ቀሪውን መረጃ ፍርድ ከመሰጠቱ በፊት በማንኛውም ጊዜ ማሟላት ይቻላል። በኋላ የሚጨመረዉ ሰነድ አዲስ ማስረጃዎችን የያዘ መሆን አለበት። በፈጣን ሂደት በታየ ጉዳይ ላይ አቤቱታ መቅረቡ ከሀገር የመልቀቅ ግዴታን ተፈፃሚነት ሊያቆይ አይችልም።
የጥገኝነት ጥያቄያችሁ ውድቅ ከሆነ ፈረንሳይን ለቃችሁ እንድትወጡ ይነገራችኋል። ይህም ሰነድ (OQTF – Obligation de Quitter le Territoire Français) የፈረንሳይን ምድር የመልቀቅ ግዴታ ይባላል። ጉዳዩ እንደገና እንዲመረመር ለፈረንሳይ የስደተኞችና ዜግነት የሌላቸዉ ሰዎች ጥበቃ ቢሮ (OFPRA) ማመልከት ይቻላል። ከዚያ በመጀመሪያው የጥገኝነት ማመልከቻ ውስጥ ያልተካተቱ አዳዲስ ማስረጃዎችን ማቅረብ ያስፈልጋል። ነገር ግን ቢሮው በድጋሚ አልመረምርም ሊል ይችላል። ለማመልከት የ8ቀናት ጊዜ ይኖራል።
በፈረንሳይ ላሉት የሌላ ሀገር ኤምባሲዎች የጥገኝነት ማመልከቻ ብታስገቡ እና የማመልከቻ ደረሰኙን በታስቀምጡት ምናልባት ለጉዳያችሁ ያላችሁን ፅናት እና እውነተኛነት ለማሳየት ይጠቅማል። ለወደፊት ከፈረንሳይ ወይም ከሌላ ሀገር አዎንታዊ መልስ ሊያስገኝ ይችላል።
በሌላ ምክንያት (ጤና፣ ስራ፣ ወዘተ) የመኖሪያ ፍቃድ ማግኘት ይቻላል።
በደብሊን ደንብ መሰረት፤ ለፈረንሳይ መንግስት የጣት አሻራ ሰጥታችሁ ከሆነ ቢያንስ ለቀጣዮቹ 10 ዓመታት በሌላ የአዉሮፓ ሀገር ጥገኝነት መጠየቅ አትችሉም (ቢያንስ ለ3 ወራት ከሽንገን ክልል ውጭ ካልቆያችሁ በስተቀር)።
ሁሉም አቤቱታዎች ውድቅ ከሆኑ በፈረንሳይ ምድር አጋላጭ ሁኔታ ውስጥ እንዳላችሁ ማወቅ አለባችሁ። ከሀገር ሊያስወጧችሁ ይችላሉ። ከሀገር እንዲወጡ የሚደረጉ ሰዎች ወደ ማቆያ ማዕከል ሊወሰዱ ይችላሉ። ወይም ደግሞ በቤት ዉስጥ መታሰር (እስር) ሊጠበቁ ይችላሉ።
ከሀገር ሲያስወጡኝ ወደ የት ነው የሚወስዱኝ ?
ሦስት አማራጮች አሉ :-
በደብሊን ሦስተኛ ደንብ መሠረት ፤ ወደ ሌላ አውሮፓ ሀገር መወሰድ
የጥገኝነት ጥያቄ ውድቅ በመሆኑ ወደ ትውልድ ሀገራችሁ ሊመልሷችሁ ይችላሉ።
አንዳንድ ጊዜ እርስዎን ሊመልሱ በፈለጉበት ሀገር ዉስጥ ባለው ሁኔታ ምክንያት ወደዚያ መወሰዳችሁ ተፈፃሚ ላይሆን ይችላል። በዚህ ጊዜ ቁርጡ ባልታወቀ ሁኔታ በፈረንሳይ ትቆየላችሁ ማለት ነዉ።
ያለወረቀት እዚህ መኖር ምን ያህል ቀላል ነው ?
በትልቅ ከተማ ከሆኑ በነፃ የሚታከሙበት እና ሀኪም ሊያማክሩ የሚችሉበት ፓስ (PASS) ነፃ ክሊኒክ አለ። የእርግዝና ክትትል እና ፅንስ ማቋረጥ በፈረንሳይ ሀገር በነፃ ይደረጋል። በአንዳንድ ከተሞች ሊረዷች የሚችሉ የስደተኞች የመረጃ ቡድኖች እና ስደተኞችን የሚደግፉ ቡድኖች (Collectifs de Sans-Papiers) አሉ።
ስራ ከሠራችሁ በተቻለ መጠን አንዳንድ የክፍያ ሰነዶችን (የደሞዝ ክፍያ ደረሰኝ) ያስቀምጡ፤ ከማህበረሰቡ ጋር ለመቀላቀላችሁ ማስረጃ ይሆናል። አሁን ባለው ሕግ መሰረት አንድ ሰው ከፈረንሳይ ማህበረሰብ ጋር መቀላቀል እና የመኖሪያ ፍቃድ ማግኘት የሚችለው ከ5 ዓመት በኋላ ነው። በፈረንሳይ ሀገር እየኖራችሁ፣ ለተወሰነ ሰዓት እየሰራችሁ  እንደሆነና የፈረንሳይኛ ቋንቋ ችሎታችሁ እየተሻሻለ እና ልጆቻችሁ ትምህርት ቤት እየተማሩ እንደሆነ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ያስፈልጋችኋል።
ማግባት ትችላላችሁ።
የድንገተኛ ጊዜ መጠለያ ቦታዎችን መጠቀም ትችላላችሁ።
የባንክ ደብተር ልታወጡ ትችላላችሁ።
ጠቃሚ አድራዎች :-
ብትታሰሩ ወይም ከሀገር እንድትወጡ የተላለፈዉን ዉሳኔ ለመከራከር:- sanspapiers.internetdown.org
የሕግ መረጃ :- GISTI : Groupe d’Information et de Soutien des Immigré-e-s :  http://wws.gisti.org
Cimade (ሲማድ) http://www.lacimade.org
Federation of Associations in Solidarity with All Immigrants (FASTI – ስደተኞችን የሚደግፉ ማህበራት ፌዴሬሽን) :-  http://www.fasti.org
Ministère de la regularisation de tous les sans-papiers (ወረቀት የሌላቸው ሕጋዊ ሰነዶች እንዲያገኙ የሚጥር መንግሥታዊ ያልሆነ ቡድን) :- http://ministere-de-la-regularisation-de-tous-les-sans-papiers.net/joomla1.5/
Welcome to Europe («እንኳን ወደ አውሮፓ በደህና መጣችሁ !» የሚባል ቡድን) :- http://www.w2eu.info
Education Without Borders (Education Sans Frontières – «ትምህርት ያለድንበር» የሚባል የተማሪዎች ጥበቃ ቡድን) :- http://www.educationsansfrontieres.org
የስደተኞች መረጃ እና ድጋፍ ቡድኖች፣በፈረንሳይ ዉስጥ በየከተማዉ በማህበረሰብ ደረጃ አሉ።ከዚህ ቀጥሎ በተሰጠዉ ድረ-ገፅ አማካኝነት ዝርዝራቸውን ማግኘት ይቻላል :- http://www.gisti.org/spip.php?article1506
በፈረንሳይ ጥገኝነት ለመጠየቅ የሚረዳ መረጃ (ለሴቶች)
ሴቶች፤ በፈረንሳይ ወይም በሌላ የአውሮፓ ሀገር ጥገኝነት ለመጠየቅ የሚከተለውን መረጃ ከግንዛቤ ማስገባት ትፈልጉ ይሆናል።በሴቶች ላይ የሚነጣጠሩ ጥቃቶች (ሴቶችን ለስደት የሚዳርጉ ጥቃቶች) እንዳሉ በአውሮፓ የጥገኝነት ሕግ ዉስጥ በግልፅ ተቀምጧል።ነገር ግን እንደ አለመታደል ሆኖ ሁል ጊዜ አይተገበርም። እነዚህ ጥቃቶች የቤት ውስጥ ግጭት፤ ድብደባ፤ ጥቃት ፣ የሴት ልጅ ግርዛት፣ የግዴታ ጋብቻ፣ መደፈር እና የግዴታ ሴተኛ-አዳሪነትን ያካትታሉ። ጥገነኝነት ለማግኘት ምክንያት የሚሆኑት ግን ከእነዚህ ጥቃቶች መካከል የደረሰባችሁ ካለና በትውልድ ሀገራችሁ ከነዚህ ጥቃቶች ራሳችሁን ለመጠበቅ በፖሊስ እና በፍርድ ቤት ተቋማት ላይ እምነት ከሌላችሁ ነዉ።
የሴት ልጅ ግርዛት
በሊል ከተማ (Lille)፤ ከካሌ በባቡር የአንድ ሰዓት ርቀት ላይ ያለ ከተማ) ለተገረዘች ሴት የሚደረግ የህክምና እና ማህበራዊ እንክብካቤ ማግኘት ትችላላችሁ። ለጥገኝነት ማመልከቻ የሚረዳና መገረዝሽን የሚያረጋግጥ ሕጋዊ ማስረጃ ሰርተፍኬት ከሆፒስታል ማግኘትትችያለሽ።
አድራሻ :-
Hôpital Saint Vincent de Paul, (ቅዱስ ቫንሳን ጳውሎስ ሆስፒታል)
Boulevard de Belfort, 59 000 LILLE, (በሊል ከተማ፤ የቤልፎር መንገድ)
የስልክ ቁጥር ;- 03 20 87 48 48
http://www.ghicl.fr
Dr. Richard Matis (ዶክተር ሪሻር ማቲስ)

GAMS Nord-Pas-de-Calais
የስልክ ቁጥር :- 06 87 71 67 64
http://www.federationgams.org
ዋና አስተዳደሪ :- ወይዘሮ ኤሊያን አይሲ

ኔዘርላንድ (ሆላንድ)
ምን ዓይነት ቋንቋዎች ይነገራሉ ?
የስራ ቋንቋዎች :- ደች፣ ዌስት ፍሪዚያን፣ እንግሊዝኛ
ከካሌ ምን ያህል ይርቃል ?
የኔዘርላንድ ድንበር ከካሌ በስተምስራቅ 140 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ነው። ትላልቅ ከተሞች ሮተርዳም (290 ኪሎ ሜትር) እና አምስተርዳም (360 ኪሎ ሜትር) ርቀት ላይ ይገኛሉ። የባቡር መስመር በቤልጅየም በኩል ነው የሚያልፈው።
የጥገኝነት ጥያቄ ሂደት እንዴት ይፈፅማል ?
በ48 ሰዓታት ውስጥ ፖሊስ ጣቢያ በመሄድ ማመልከት አለባችሁ።፡በምድር ትራንስፖርት ከገባችሁ ምዝገባ በሚካሄድበት በማዕከላዊ የስደተኛ መቀበያ ቦታ ቀርባችሁ ማመልከት አለባችሁ። የስደተኛ እና የዜግነት አገልግሎት ቢሮ ጥገኝነት ጠያቂውን ግለሰብ የመመዘገብ ኃላፊነት አለበት። የውጭ ዜጐችን የሚመለከተው ቢሮ የተለያዩ ግለሰባዊ መረጃዎችን ይወስዳል። በአውሮፕላን ጣቢያ የማመልከቻ ማዕከል ቢኖርም በዚህ በኩል ያለው ሂደት በ « ሮያል ወታደራዊ ፖሊስ » በኩል ስለሚፈጸም በመጨረሻ ልትያዙ እና ወደ ማቆያ ክፍል ልትወሰዱ ትችላላችሁ።
የጥገኝነት ጥያቄ ባቀረባችሁበት ቀን የስደተኞች እና ዜግነት አገልግሎት ቢሮ ማንነታችሁን፣ ዜግነታችሁን፣ እና የመጣችሁበትን የጉዞ መስመር ለማጣራት የመጀመሪያውን ቃለ መጠይቅ ያደርጋል። ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ጠበቃ ይመደባል። ይህን የማጤን ዕድል ይኖራችኋል። ሁለተኛው ዙር ቃለ መጠይቅ ጥገኝነት የጠየቃችሁበትን ምክንያት ይመለከታል። አስተርጓሚ ይመደብላችኋል። እያንዳንዱ ጥገኝነት ጠያቂ ሰዉ ነፃ የሕግ አገልግሎት እርዳታ የማግኘት መብት አለው።
በተራዘመ የጥገኝነት ጥያቄ ሂደት እና በሚቀርቡ አቤቱታዎች ወቅት ወደ አገራችሁ እንድትመለሱ አትገደዱም/ አይመልሷችሁም። አቤቱታ መቅረብ ያለበት የጥገኝነት ጥያቄው ውድቅ በሆነ በአራት ሳምንታት ውስጥ ነው። በአጭር እና በተራዘመ የጥገኝነት ጥያቄ ሂደት የክልሉ ምክር ቤት በወሰነው ውሳኔ ላይ ወደ መንግስት ምክር ቤት በመሄድ አቤቱታ ማቅረብ ይችላል። ነገር ግን በዚህ ወቅት ወደ አገራችሁ እንድትመለሱ የማትገደዱበት ምንም ዋስትና የለም (ሊመልሷችሁ ይችሉ ይሆናል)።
የስደተኞች እና የዜግነት አገልግሎት ቢሮ ቅድሚያ የሚሰጠው ለሶሪያ ዜጐች ነው። ይህ የሆነው ከየካቲት 2013 ጀምሮ ሲሆን እስከመቼ እንደሚቀጥል አይታወቅም።
ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል ?
በአጭር ሂደት እስከ 8 ቀናት ሲሆን ለአቤቱታ ደግሞ ከ6 ወራት በላይ ይወስዳል። የመጀመሪያውን ቀለ መጠይቅ ለማድረግ ሳምንታት ወይም ወራት ልትጠብቁ ትችላላችሁ። ጥገኝነት የጠየቃችሁበት ምክንያት ደካማ ነው ከተባለ በ8 ቀናት ውስጥ ውሳኔ ታገኛላችሁ። ይህ ማለት መጠለያውን በ4 ሳምንታት ውስጥ መልቀቅ አለባችሁ ማለት ነው። በዚህ ወቅት ይህን ውሳኔ በመቃወም ወደ ፍርድ ቤት በመሄድ አቤት ማለት ትችላላችሁ። በፍርድ ቤት ካሸናፋችሁ የጥገኝነት ጥያቄ ሂደቱ እንዲቀጥል እና ለረጅም ጊዜ የመቆየት መብት ይኖራችኋል። ጥገኝነት የጠየቃችሁበት ምክንያት አደገኛ ወይም ጠንካራ ነው ከተባለ የመጀመሪያ ውሳኔ የሚሰጡበት ጊዜ ለጥቂት ወራት ሊዘገይ ይችላል።
ውሳኔ በመጠበቅ ላይ ሳለሁ እንዴት መኖር እችላለሁ ? አበል አገኛለሁ ?
የመኖሪያ ቤት ይሰጣችኋል፤ ለምግብ፣ አልባሳት እና ሌሎች የግል ወጪዎች፤ ለጥገኝነት ጉዳይ የሕግ አገልግሎት እርዳታ ወደ ሚሰጥበት ቦታ ለመሄድ እና ለመመለስ የሕዝብ ትራንስፖርት ቲኬት፣ ለመዝናኛና ለትምህርታዊ እንቅስቃሴዎች እና ለሕክምና ወጪ የሚሆን ሳምንታዊ አበል ይኖራችኋል። የመኖሪያ ፍቃድ ያገኙ ጥገኝነት ጠያቂዎች (ቤት እስከሚገኝላቸው ጊዜ ድረስ) በስደተኛ መቀበያ ማዕከል ውስጥ መቆየት ይችላሉ/ ይፈቃድላቸዋል።በስደተኞች መቀበያ ማዕከል ያሉ ነዋሪዎች የሚኖሩት አንድ ክፍል ውስጥ በጋራ ከ5-8 ሰዎች በመሆን ነው። በኔዘርላንድ እንደሚኖር ማንኛውም ሌላ ሰው ጥገኝነት ጠያቂዎች ለሕክምና አገልግሎታቸው አጠቃላይ ሓኪም፣ አዋላጅ ሀኪም ማግኘት ወይም ደግሞ ሆስፒታል መሄድ ይችላሉ። ለማንኛውም የጤና ጉዳይ መጀመሪያ መሄድ ያለባችሁ ወደ ስደተኞች የጤና ማዕከል(Gezondheids-centrum Asielzoekers) ነው።
ከ18 ዓመት በታች ከሆንኩስ ?
ልጆች ያሏቸው ቤተሰቦች በማቆያ የሚያዙት ቢበዛ እስከ 14 ቀናት ነው። ከወላጆቻቸው የተነጠሉ ልጆች በወጣቶች ማህበራት በተዘጋጀ አነስተኛ መጠለያ ይኖራሉ። የልጆች የመኖሪያ ክፍል እስከ 12 ልጆችን ይንከባከባል፤ 24 ሰዓታት ክትትል ያደርጋል። ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ልጆች ትምህርት ቤት ለመሄድ ይገደዳሉ።
ቤተሰቦቼስ ?
የተጋቡ ጥንዶች ብቻ እንደ ቤተሰብ ይታያሉ። ከዚህ ውጭ ሊታይ የሚኖር ጉዳይ ቢኖር በአገራቸው መጋባት ላልቻሉ ጥንዶች (ለምሳሌ የተመሳሳይ ፆታ እንደ ወንድ እና ወንድ ወይ ሴት እና ሴት) ብቻ ነው። ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች ሊመጡ ይችሉ ይሆናል።
መስራት እና መማር እችላለሁ?
የጥገኝነት ጥያቄያችሁ እንደደረሰበት ደረጃ እየታየ አዋቂዎች ፕሮግራሞችን እና የምክር አገልግሎቶችን መከታተል ይችላሉ። በማዕከሉ ውስጥ ያሉ ስራዎችን መስራት ትችላላችሁ፤ ለምሳሌ በሕንፃዉ ውስጥ ያሉ የጋራ ቦታዎችን በማፅዳት እስከ 13.80 ዩሮ (€) በሳምንት ልታገኙ ትችላላችሁ። ለጥገኝነት ካመለከታችሁ ከ6 ወራት በኋላ የስራ ፍቃድ ይኖራችኋል። የመማሪያ ቁሳቁሶችን ለመጠቀም እና ከቤተሰብ እና ጓደኞች ጋር መረጃ ለመለዋወጥ « open Leercentrum » ድረ-ገፅ መጐብኘት ትችላላችሁ። ጥገኝነት ጠያቂዎች መስራት የሚፈቀድላቸው አጠቃላይ የጊዜ ብዛት ከ12 ወራት ውስጥ 24 ሳምንታት ብቻ ነው። መስራት ከመጀመራችሁ በፊት ቀጣሪያችሁ ለናንተ የስራ ፍቃድ (tewerkstellingsvergunning) መጠየቅ አለበት።
ጥገኝነት ከተሰጠኝ በኋላ ምን ይሆናል ?
የጥገኝነት መኖሪያ ፍቃድ ካገኛችሁ ከማህበረሰቡ ጋር እንድትቀላቀሉ እና እንድትለምዱ የሚያግዙ ከርሶችን የመውሰድ ግዴታ አለባችሁ። መስራት እና መማር ትችላላችሁ። የጥገኝነት ጠያቂዎች ተቀባይ በሆነዉ ማዕከላዊ ኤንጀንሲ (COA) በኩል መኖሪያ ቤት ታገኛላችሁ።
ጥገኝነት ካላገኛሁ እና ከሀገር እንድለቅ ቢወሰንስ ? አሉታዊ ውሳኔ በተላለፈ በ4 ሳምንታት ውስጥ የመቀበያ ማዕከሉን የመልቀቅ አለባችሁ።
ከታሰርኩስ ?
ከታሰራችሁ መብታችሁ ይነገራችኋል ነገር ግን በምንም ዓይነት መልኩ በፅሑፍ አያሳያሳዩም ወይም አይሰጧችሁም። አስተርጓሚ እና ጠበቃ የማግኘት መብት አላችሁ። በጠበቃችሁ በኩል ለዘመዶቻችሁ መልዕክት ማስተላለፍ ትችላላችሁ።
የማቆያ ሂደቶች እና መብቶች
በኔዘርላንድ ሕግ መሰረት በጥገኝነት ጥያቄ ሂደት ላይ ያሉ ሰዎች ተይዘው ወደ ማቆያ ሊወሰዱ ይችላሉ። በዚያም እስከ 18 ወራት ሊቆዩ ይችላሉ፤ እንዳንዴም በመደበኛ እስር ቤት ሊሆን ይችላል። የጤና እንክብካቤ ሊቀርብላችሁ ይገባል።
እዚህ ያለመኖሪያ ፍቃድ መኖር ምን ያህል ቀላል ነው?
እጅግ ብዙ ስደተኞች በጐዳና ላይ እየኖሩ ነው። ከመንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እርዳታ ሳያገኙ አገልግሎት እና እንክብካቤ የሚያገኙ በጣም ጥቂቶች ናቸው። ብዙ ጊዜ ስደተኞች መክፈል ለማይገባቸው ወጪ  ደረሰኝ ላይ እንዲፈርሙ ይደረጋሉ። ወረቀት ለሌላቸው ስደተኞች መንግስት አስፈላጊ ለሆነ የሕክምና አገልግሎት ውጪውን ይሸፍናል(በCollegie Voor Zorgcversicheringen በሚባል ተቋም በኩል)። ስራ መስራት ይቻላል። ሕፃናትን መንከባከብ፣ በግንባታ ሥራ ውስጥ ያሉ ስራዎችን፣ አትክልት መንከባከብ እና በምግብ ቤት ውስጥ መስራት ይቻላል። የስራ ተቆጣጣሪ ድርጅት እንዳንዴ ድርጅቶች ሕገ ወጥ ስራተኞች እንዳላቸው እና እንደሌላቸው ሊመረምር ይችላል። ከተገኘባቸው በአንድ ሕገ ወጥ ሥራተኛ ከ4000 እስከ 8000 ዩሮ (€) ሊቀጡ ይችላሉ። በሕገ-ወጥ መንገድ ሲሰራ የተገኘ ሊታሰር ወይም ወደ ማቆያ ሊወሰድ ይችላል እንጂ በገንዘብ አይቀጣም። የምትሰሩ ከሆነ በሥራ ሕግ መሠረት መብታችሁ የተጠበቀ ነው። ያላችሁበትን ጥሩ ያልሆነ ሁኔታ መሠረት እድርገው ቀጣሪዎች ያለፍቃዳችሁ ወይም በማይገባ ሁኔታ ውስጥ እንድትስሩ ሊፈልጉ ይችላሉ (ለምሳሌ በወሲብ ሥራ ላይ መስራት)። እነዚህን ስራ ለመስራት ካተገደዳችሁ፣  ቀጣሪያችሁን ለፖሊስ ማሳወቅ ትችላላችሁ። ከዚያም የሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን በሚመለከተው « B-9» (ቢ-ናይን) በሚባል ደንብ የመቆየት መብት ልታገኙ ትችሉ ይሆናል።
ማን ሊረዳ ይችላል ?
ነፃ የሕግ አገልግልት እና እርዳታ ለማግኘት :- የስደተኞችን ጉዳይ የሚመለከት የደች ምክር ቤት (« ደች ካውንስል ፎር ሪፈዉጂስ » የሚባል መንግሥታዊ ያልሆነ የእርዳታ ቡድን) http://www.vluchtelingenwerk.nl
ነፃ የሕክምና አገልግሎት በአምስተርዳም ከተማ :-
ክሩይስፖስት (Kruispost) ወረቀት የሌላቸው እና ቤት ለሌላቸው የሕክምና አገልግሎት ይሰጣል።
አድራሻው :- Oudezijds Voorburgwal 129, 1012 EP Amsterdam
ስልክ :- 020 – 624 90 31,
ፋክስ :- 020 – 428 83 30,
ኢሜል አድራሻ :- kruispost@oudezijds100.nl

የዓለም ቤት (The Worldhouse (Wereldhuis)) በዶክቶር ለመታየት ቀጠሮ ለመወስድ ብቻ እንጂ ሙሉ የሕክምና አገልግሎት አይስጥም።
አድራሻ:- Nieuwe Herengracht 20 (በWaterloo-pleinአካባቢ), 1018 DP Amsterdam
ስልክ :- 06 22821472,
ኢሜል አድራሻ : info@wereldhuis.org,
ድረ-ገፅ : http://www.wereldhuis.org

ወረቀት ለሌላቸው ሰራተኞች :-
ስልክ :- 010 7470156
ኢሜል :- info@stichtinglos.nl
Vestigingsadres per 1 augustus 2014: Mauritsweg 20
3012 JR Rotterdam
ድረ-ገፅ : http://www.stichtinglos.nl

ለስደተኛ ተማሪዎች የቆመ ፋውንዴሽን (Foundation for Refugee Students) :- በኔዘርላንድ ዩኒቨርሲቲዎች ለማጥናት የሚረዳ
ድረ-ገፅ :- http://www.uaf.nl/home/english

ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ :- http://www.nidos.nl/Default.aspx

ጀርመን
ምን ዓይነት ቋንቋ ይነገራል ?
የስራ ቋንቋ ጀርመንኛ ሲሆን እንግሊዝኛ በትላልቅ ከተሞች ውስጥ ይነገራል።

ከካሌ ምን ያህል ይርቃል ?
የጀርመን ድንበር ከካሌ በስተምስራቅ 340 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል። ትላልቅ ከተሞች ኮልን (400 ኪሎ ሜትር)፣ ሐምቡርግ (770 ኪሎሜትር) ፍራንክፈርት (600 ኪሎ ሜትር) እንዲሁም ዋና ከተማዉ በርሊን (950 ኪሎ ሜትር) ረቀት ላይ የገኛሉ። ጀርመን ፈረንሳይን በስተምስራቅ በኩል ታዋስናታለች። የባቡር መስመር በቤልጅየም እና በኔዘርላንድ በኩል ያልፋል።

የጥገኝነት ጥያቄ ሂደቱ እንዴት ይፈፅማል ?
የጥገኝነት ጥያቄ በማንኛውም የስደት እና ስደተኞች ጉዳይ ፌዴራል ቢሮ (Bundesamt für Migration und Flüchtlinge: BAMF) ማስገባት ትችላላችሁ። በሌላ መንግስታዊ ኤጀንሲ (ፖሊስ፣ የአካባቢ የስደት ወይም የውጭ ዜጐች ጉዳይ ቢሮ) ካመለከታችሁ ወደ የስደት እና ስደተኞች ጉዳይ ፌደራል ቢሮ ይልኳችኋል። ቢሮዎቹ የሚገኙበት ቦታ ለደህንነት አስተማማኝ ስላልሆኑ ከሌላ ሰው ጋር አብሮ መሄድ የተሻለ ነው።
በፌዴራል ቢሮ ግለሰባዊ መረጃችሁን እንድትሰጡ ትጠየቃላችሁ። ፎቶግራፍ ይወስዳሉ (ለደብሊን ሦስተኛ ደንብ)። እስከ 25 የሚደርሱ ጥያቄዎችን ሰለራሳችሁ ልትጠየቁ ትችላላችሁ። (ለምሳሌ እንዴት ጀርመን እንደገባችሁ፤ ለመጨረሻ ጊዜ የኖራችሁበት ቦታ)። የምትሰጡት ምላሽ በድምፅ ይቀዳና በኋላ በዋናው ቃለ መጠይቅ ጊዜ ይቀርባል። በህጉ መሠረት በሁለቱም ቃለመጠየቅ ወቅት አስተርጓሚ ሊመደብላችሁ ግዴታ ነው። ለቃለ መጠይቅ የሰጣችሁት መልስ በፅሑፍ ሲቀርብላችሁ ስለትክክለኛነቱ እርግጠኛ ስትሆኑ ብቻ ፈርሙበት። ነፃ የሕግ አገልግሎት እርዳታ ማግኘት ከባድ ነው።

ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል ?
ሂደቱ ከ6 እስከ 12 ወራት ጊዜ ሊወስድ ይችላል።

ውሳኔ በመጠበቅ ላይ ሳለሁ እዚህ እንዴት መኖር እችላለሁ? አበል አገኛለሁ?
ውስን የመኖሪያ ጊዜ ፍቃድ (Aufenthaltsgestattung) ይሰጣችኋል። ኢዚ (EASY) የተባለ አሰራር ጥገኝነት ጠያቂዎችን በሙሉ በመላው የጀርመን አካባቢዎች ይበትናል። የመኝታ አልጋ በጋራ የመኖሪያ ቤት (Erstaufnahmelager) ውስጥ ይሰጣችኋል። እነዚህ ቤቶች ውስጥ ያለው ሁኔታ ይለያያል። አንዳንዶቹ በከተማ ይገኛሉ፤ ሌሎቹ ደግሞ በገጠር። ወደ ፈለጋችሁበት ቦታ መጓዝ አትችሉም። ለመጀመሪያዎቹ አራት ወራት ውስጥ በተወሰኑ ቦታዎች ብቻ እንድትጓዙ ነው የሚፈቀደው። የተወሰነ ገንዘብ ይሰጣችኋል።

ከ18 ዓመት በታች ከሆንኩስ ?
ሌሎች ከ18 ዓመት በታች ከሆኑ ሰዎች ጋር በአንድ ቤት ውስጥ ቦታ ይሰጣል። አልጋ፣ ምግብ፣ ትንሽ ገንዘብ እና የማህበራዊ ሥራ ባለሙያዎችን ያገኛሉ። ትምህርትና የሥራ ስልጠና ማግኘት ይቻላል። የቤተሰባችሁን አባላት ከሌላ ቦታ ማምጣት እና ከእናንተ ጋር እንዲቀላቀሉ ማድረግ ከባድ ነው። 18 ዓመት ከሞላችሁ በኋላ ከሀገር እንድትወጡ ልትገደዱ ትችሉ ይሆናል።

ቤተሰቦቼስ?
የመኖሪያ ፈቃድ አግኝታችሁ ከሆነ ምናልባት ለቤተሰቦቻችሁም (ባል/ሚስት/ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች) ሊሰጥ ይችል ይሆናል። ከሌላ ቦታ መጥተው እዚህ ቤተሰቦቻቸውን የተቀላቀሉ ሰዎችም የመስራት መብት አላቸው።

መስራት እና መማር እችላለሁ ?
የጥገኝነት ጥያቄ ከቀረበ ከ3 ወራት በኋላ ግለሰቡ ለስራ ፈቃድ ማመልከት ይችላል። ይህ ፈቃድ የሚሰጠው ሥራ ባለባቸው የጀርመን አካባቢዎች ነው።

ምን ዓይነት እርምጃዎች መወሰድ አለብኝ?
የስራ ፈቃድ ለማግኘት ለፌደራል የቅጥር መስሪያ ቤት (Bundesagentuer für Arbeit) ማመልከት አለባችሁ።

ጥገኝነት ካገኘሁ ምን ይሆናል?
የጀርመን ነዋሪ ከሆናችሁ በኋላ ስራ የማግኘት ዕድላችሁን ከፍ ለማድረግ ነፃ የጀርመንኛ ትምህርቶች መውሰድ ትችላላችሁ። ራሳችሁን ማስተዳደር እስክትችሉ ድረስ አስፈላጊው ሁሉ ይደረግላችኋል። ምናልባት ወደ ሌሎች የአውሮፓ ሕብረት አባል አገራት መሄድ ትችሉ ይሆናል፤ ነግር ግን መኖር አትችሉም።

ጥገኝነት ካለገኘሁስ ? ከሀገር እንድወጣ ቢወሰንስ ?
ከሀገር እንደትወጡ ከተወሰነ ነገር ግን መጓዝ ካልቻላችሁ ወይም የጉዞ ፓስፖርት ከሌላችሁ ወይም የትውልድ ሀገራችሁ ካለው ሁኔታ አንፃር ብትመለሱ ሕይወታችሁ አደጋ ላይ የሚወድቅ ከሆነ ይታገሷችኋል። ለሳምንታት ቆይታ የሚሆን የአጭር ጊዜ ስምምነት ትፈርማለችሁ ነገር ግን ለአያሌ ዓመታት ሊታደስ ይችላል። ለመስራት በሕግ የተፈቀደላችሁ ቢሆንም ለመጀመሪያዎቹ አራት ዓመታት በተግባር እንደታየዉ በጣም ከባድ ነው። የስራ ስልጠና ማግኘት ይቻላል።
ጥገኝነት እንደማይሰጣችሁ የፌዴራል ቢሮ በፅሑፍ ካሳወቀ በኋላ በፅሑፍ ማመልከቻ በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ አቤቱታ ማቅረብ ይቻላል። ለሕግ አገልግሎት እርዳታ ማመልከት ትችላላችሁ ነገር ግን ላይሰጣችሁም የሚችልበት ጊዜ ይኖራል። ከሀገር ለቃችሁ ከመውጣታችሁ በፊት እስከ 18 ወራት ያህል በተዘጋ ማዕከል ውስጥ ልትቆዩ ትችላላችሁ።

ከታሰርኩስ?
ከታሰራችሁ መብቶቻችሁን ይነግሯችኋል። የመብታቻሁን ዝርዝር ዓይነት በፅሑፍ አስፍረዉ በጀርመንኛ ያሳዯችኋል። ጀርመንኛ የማትረዱ ከሆነ የተዘረዘሩትን መብቶች አስተርጓሚ ያስረዳችኋል። ከዚያም መብታችሁን እንዳወቃችሁ (እንደተነገራችሁ) እንድታረጋግጡ ያስፈርሟችኋል። አስተርጓሚ በነፃ ይመደብላችኋል።

ያለመኖሪያ ፈቃድ እዚህ እንዴት መኖር እችላላሁ ?
በጀርመን ውስጥ ያሉ ወረቀት የሌላቸው ሰዎች ቁጥር በግምት ከ500.000 እስከ 1.500.000 ይደርሳል። አንዳንዶች ጀርመን ውስጥ ለመስራት በሚስጥር ይገባሉ። ሌሎች ደግሞ በአንድ ወቅት የመኖር መብት የተሰጣቸዉ ነገር ግን በኋላ ላይ ይህን መብት የተከለከሉ ናቸው። ተጨማሪ ሌሎች ደግሞ አሉ፤ የጥገኝነት ጥያቄያቸው ውድቅ ከሆነ በኋላ ተደብቀው የሚኖሩ ናቸዉ። በሕገ-ወጥ የሚኖሩ ሰዎች የኑሮ ሁኔታ በጣም ዝቅተኛ ነው። የማግህበራዊ አገልግሎት መብት የላቸውም። የህክምና እርዳታ አያገኙም። ሕገ-ወጥ ሠራተኞ እንደመሆናቸው በአሠሪያቸው ይበዘበዛሉ።

ማን ሊረዳኝ ይችላል ?
ያለምንም ወረቀት የሕክምና እርዳታ ለማግኘት በብዙ የጀርመን ከተሞች የሕክምና ጣቢያዎች አሉ። ከዚህ በታች በተሰጠው ድረ-ገፅ ላይ ካርታ እና የአድራሻ ዝርዝር አለ። በእነዚህ የህክምና ቦታዎች በአያሌ ቋንቋዎች ያስተናግዳሉ። http://medibueros.m-bient.com

ፕሮ አሲል (PRO ASYL) የሚባል ነፃ የሰብዓዊ መብት ድርጅት
ስልክ:- 0049 (0)69-23 06 88
ፋክስ-: 0049 (0)69-23 06 50
ኢሜል:- proasyl@proasyl.de
ድረ-ገፅ:- proasyl.de

ከሞላ ጐደል በሁሉም የጀርመን ከተሞች የስደተኞች ጉዳይ ምክር ቤት (Flüchtlingsräte) አለ። ጠቃሚ መረጃ እና ድጋፍ ሊሰጡ ይችላሉ።

የበርሊን ከተማ የስደተኞች ጉዳይ ምክር ቤት አድራሻ :-
Flüchtlingsrat Berlin
Georgenkirchstraße 69-70, 10249 Berlin
ስልክ :- 0049(0)30-24344-5762
ፋክስ :-  0049(0)30-24344-5763
ኢሜል :-buero@fluechtlingsrat-berlin.de
ድረ-ገፅ :-http://www.fluechtlingsrat-berlin.de

ከቤተሰባቸው የተነጠሉ እና ከ18 ዓመት በታች እና በቸኛ ለሆኑ ሰዎች ሙንሽን (ሙኒክ) ከተማ ዉስጥ ከዚህ ከታች በተጠቀሰዉ አድራሻ የሚገኘዉ ተቋም ድጋፍ ሊሰጥ ይችላል :-
Bundesfachverband Unbegleitete Minderjährige Flüchtlinge e.V. Nymphenburger Str. 47
80335 München
ስልክ:- 0049(0)89 / 20 24 40 13
ፋክስ ፮ 0049(0)89 / 20 24 40 15
የስራ ሰዓት :- ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከጧቱ አራት ሰዓት እስከ ስድስት ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከሰባት እስከ አስር ሰዓት። (Monday-Thursday 10-12 a.m / 7-10p.m.)
ድረ-ገፅ :- http://www.b-umf.de

ዴንማርክ
ምን ዓይነት ቋንቋዎች ይነገራሉ?
የስራ ቋንቋ ዳኒሽ ነው። አንግሊዝኛ በስፋት ይነገራል።

ከካሌ ምን ያህል ይርቃል?
ቶንደር 900 ኪሎ ሜትር እና ዋና ከተማው ኮፐንሃገን 1200 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛሉ። የባቡር መስመር በቤልጀየም እና በጀርመን በኩል ያልፋል።

የጥገኝነት ጥያቄ ሂደቱ እንዴት ይፈፀማል?
ዴንማርክ ውስጥ ፖሊስ ጣቢያ ወይም ሳንድሆልም በተባለው የመኖሪያ ማዕከል አሌሮድ (Allerød) ጣቢያ አጠገብ ይገኛል። በአካል በመገኘት የጥገኝነት ጥያቄ ማቅረብ ይቻላል። ዴንማርክ ድንበር ውጭ ሆኖ የጥገኝነት ጥያቄ ማቅረብ አይቻልም። ወደ ዴንማርክ ሲገባ ድንበር ላይ ያልተከለከለ ሰው ሁሉ መመዝገብ ይችላል። ፎቶግራፍ እና የጣት አሻራው ይወሰዳል ከዚያም ወደ ሳንድሆልም የሚባል በቀይ መስቀል ማህበር የሚተዳደር የመጠለያ ማዕከል ይወሰዳል። የጥገኝነት ጥያቄ ሂደቱ የሚጀምረው እዚያ ነው። በጣም ከባድ እና ማስረጃ ሊቀርብበት የሚችል የአዕምሮ ወይም የአካል ህመም ካለባችሁ እና ለዚያ የሚሆን የሕክምና አገልግሎት በትውልድ ሀገራችሁ የሌለ ከሆነ የበጐ አድራጎት መኖሪያ ፈቃድ ለማግኘት ከጥገኝነት ጥያቄው ሂደት ውጭ በተናጠል መጠየቅ ትችላላችሁ።

ውሳኔ በመጠበቅ ላይ ሳለሁ እንዴት መኖር እችላለሁ ? አበል አገኛለሁ ?
ዴንማርክ ውስጥ የጥገኝነት ጥያቄያቸው በሂደት ላይ የሆኑ ሰዎች በማዕከል ውስጥ እንዲኖሩ ይጠየቃሉ።ጥገኝነት የጠየቁ ሰዎች ልጆች የዴንማርክ ነዋሪ ከሆኑ ልጆች እኩል የጤና አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ።ጥገኝነት የጠየቁ አዋቂ ሰዎች ሕክምናው አስፈላጊ እና አስቸኳይ ከሆነ ወይም ግለሰቡ በህመም ስቃይ ላይ ካለ የሕክምና ወጪው በዴንማርክ የስደተኛ ጉዳይ አገልግሎት ቢሮ ይሸፈናል። ነፃ የቤት እና የምግብ (በካፍቴሪያ ወይም አብስላችሁ የምትበሉት) እና መሠረታዊ የልብስ አቅርቦት ይኖራችኋል።
ለስልክ እና ለግል ንፅህና መጠበቂያ ለመሳሰሉት ገንዘብ ሊሰጣችሁ ይገባል።በማዕከል የምትኖሩ ካልሆነ በስተቀር (እዚያ ነፃ ምግብ ስለሚቀርብ) ለምግብ የሚሆን ገንዘብም ሊሰጣችሁ ይገባል። እንዲሁም አስፈላጊ ለሆኑ የጤና አገልግሎቶች፣ ለትምህርት እና ሌሎች ጉዳዮችም፣ መጠለያ በጥገኝነት ማዕከል ይሰጣል፤ ወደ ባለስልጣናት ቢሮ ለመሄድ እና ለመመለስ የሚሆን የትራንስፖርት ወጪ ለመሳሰለው ድጋፍ ልታገኙ ይገባል። ተጨማሪ አበል የሚሰጠው ልጆችን በተመለከተ ብቻ ነው።

ውሳኔ ለማግኘት ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል ?
በወቅቱ ያለውን የስደተኞች ቁጥር እና ለጥገኝነት ያቀርባችሁትን ምክንያት መሠረት በማድረግ ከሦስት ወራት እስከ አንድ ዓመት ጊዜ ሊወስድ ይችላል።

መስራት እና መማር እችላለሁ ?
ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ሰው ውሳኔ በመጠበቅ ላይ ሳለ የስራ ፈቃድ ለማግኘት ለዴንማርክ የስደተኞች ጉዳይ አገልግሎት ቢሮ ከስድስት ወር በኋላ ማመልከት ይችላል። ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ማንኛውም ጥገኝነት ጠያቂ ሰው በጥገኝነት ማዕከሉ የሚዘጋጀውን ትምህርት መውሰድ አለበት። ጥቂት የመማር ዕድሎች አሉ፤ በተለይ እንግሊዝኛ መናገር ይምትችሉ ከሆነ። ሁሉም ሰው የዳኒሽ ወይም የእንግሊዝኛ ትምህርት የመወሰድ ዕድል ይኖረዋል። በ7 እና በ16 ዓመት ዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ልጆች ልዩ ትምህርት ይሰጣቸዋል። ልጆች ዳኒሽ፣ እንግሊዝኛ እና ሌሎች የትምህርት ዓይነቶችን በዴንማርክ አንደኛ ወይም መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ይወስዳሉ።

ከ18 ዓመት በታች ከሆንኩስ?
ከ18 ዓመት በታች የሆነ እና ብቸኛ የሆነ ሰው በዴንማርክ የስደተኞች ጉዳይ ቢሮ ሰራተኛ ያልሆነ ተወካይ ይመደብለታል። ማመልከቻችሁ በፍጥነት ሊታይ ይገባል፣ አስከዚያው ድረስ በልዩ የመጠለያ ማዕከል ትኖራላችሁ። « በቂ የብስለት ደረጃ » ላይ ናችሁ ብለው ካመኑ (አብዛኞቹ ወጣት አመልካቶች በሳል ናቸው/ያዉቃሉ/ ተብሎ እንደሚታሰበዉ) የጥገኝነት ጥያቄያችሁን ይቀበላሉ።ካልሆነ ግን ቤተሰብ ከሌላችሁ ወይም በትውልድ ሀገራችሁ የሕዝብ አገልግሎት አቀርቦት ከሌላችሁ፤ የመኖሪያ ፈቃድ ሊሰጣችሁ ይገባል። በዚህ ወቅት የናንተን የጤና ወይም የልዩ አገልግሎት ፍላጐት ወይም እርዳታ፤ እንዲሁም በትውልድ አገራችሁ ያለውን አጠቃላይ ሁኔታ የሚመለከት መረጃ ከግንዛቤ ውስጥ ይገባል። የመኖሪያ ፈቃድ ለማግኘት በትውልድ ሀገራችሁ አቀባበል ወይም የእንከብካቤ ማዕከል የማይደረግላችሁ መሆን አለባችሁ።

ጥገኝነት ከተሰጠኝ ምን ይሆናል ?
የሚሰጣችሁ የመኖሪያ ፈቃድ ጊዜያዊ እና ለ5 ዓመት ብቻ የሚያገልግል ነው። ከ5 ዓመት በኋላ አስፈላጊውን መስፈርት ካሟላችሁ ሊራዘም ወይም ወደ ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ሊቀየር ይችላል። ለመጀመሪያዎቹ ሦስት ዓመታት ከአካባቢው ሕብረተሰብ ጋር ሊያቀላቅላችሁ የሚችል ፕሮግራም ውስጥ ትገባላችሁ። እዚያም ቤት የቋንቋ እና የስራ ስልጠና ፕሮግራም ይዘጋጅላችኋል። በአጠቃላይ ስደተኞች ከሌላው ማንኛውም ዜጋ ጋር እኩል የሆነ የጤና እና የማህበራዊ አገልግሎት የማግኘት መብት አላቸው። ዴንማርክ የመኖሪያ ፈቃድ ከተሰጣችሁ ቀን ጀምሮ ለብዙ ሰዓት የዳኒሽ ቋንቋ እንድትማሩ ይደረጋል።

ቤተሰቦቼን ማምጣት እችላለሁ?
አግብተህ/ሽ ከሆነ የተመዘገበ ፍቅረኛ ካለህ/ሽ ወይም ዴንማርክ የመኖሪያ ፈቃድ ካለው/ላት ሰው ጋር አብረህ/ሽ እየኖርክ/ሽ ከሆነ ለቤተሰብ ቅልቅል ማመልክት ትችላለህ/ያለሽ። ዕድሜያቸው ከ15 ዓመት በታች ከሆነ ልጆችህ/ሽ ጋር መቀላቀል ትችላለህ/ያለሽ። በአንዳንድ ጉዳዮች ከ15 ዓመት በላይ ከሆኑ ልጆች ግራም መቀላቀል ሊፈቀድ ይችላል። ሕገ ወጥ ሆናችሁ ነገር ግን ዴንማርክ ውስጥ ማግባት/ጋብቻ መፈፀም/ ከፈለጋችሁ መጠንቀቅ አለባችሁ ምክንያቱም ባለሥልጣናቱ የሚጋቡ ሰዎችን ስም ዝርዝር አንድ በአንድ ለፖሊስ ያሳውቃሉ። ዴንማርክ ውስጥ ከቤተሰብ ጋር ለመቀላቀል በወረቀት ላይ የሚሞላ ፎርም መሙላት እና አስፈላጊውን መረጃ ሁሉ መስጠት አለባችሁ። የማመልክቻውን ቅፅ በስደተኞች ጉዳይ አገልግሎት ቢሮ፤ በአካባቢው የፖሊስ ፅሕፈት ቤት፤ ወይም በትውልድ ሀገራችሁ ባለው የዴንማርክ ኤምባሲ  ወይም ቆንፅላ ጽሕፈት ቤት በኩል ማግኘት ትችላላችሁ።

ጥገኝነት ካላገኘሁ ወይም ከሀገር እንድወጣ ከተወሰነብኝስ?
ማንኛውም ተቀባይነት ያላገኘ የጥገኝነት ማመልከቻ በዚያው ወደ ስደተኞች የአቤቱታ ቦርድ ይላካል። የአቤቱታ ማመልከቻችሁ ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ ዴንማርክ ውስጥ መቆየት ይችላላችሁ። ከዚህ ውሳኔ በኋላ ሌላ አቤቱታ ማቅረብ አይቻልም። አቤቱታው ውድቅ ከሆነ ግለሰቡ በ15 ቀናት ውስጥ ዴንማርክን እንዲለቅ ይጠየቃል። ነገር ግን ፓስፖርት ወይም የጉዞ ወረቀት ለእናንተ መስጠት ካልተቻለ ለ18 ወራት የሚያገልግል ጊዜያዊ የመኖሪያ ፈቃድ ሊሰጣችሁ ይችል ይሆናል። ነገር ግን ብዙ ጊዜ እንደዚህ አይደለም ምክንያቱም በፍቃዳችሁ ለቃችሁ እንድትወጡ ስለሚያስፈርሟችሁ እና ፖሊስ ስለሚከታተል። እናንተን ከሀገር ከማስወጣቷ በፊት ዴንማርክ የትውልድ ሀገራችሁ ልትቀበላችሁ እስከምትፈቅድ ድረስ ትጠብቃለች።በዴንማርክ አንድ ማቆያ መዕከል አለ። እሱም ኤልቤክ የሚባል ሲሆን ሳንድሆልመን ከሚባለው የጥገኝነት ካምፕ አቅራቢያ ይገኛል። ሰዎችን በኤልቤክ ማዕከል ማቆየት የሚቻለው ቢበዛ ለ18 ወራት ነው። በአብዛኛው ሰዎች በማቆያ መዕከል ሊቆዩ የሚችሉት ለአጭር ጊዜ ነው። በማቆያ ማዕከል (እስርቤት) ውስጥ ካሉ ሌሎች ሰዎች ተነጥላችሁ እንድትኖሩ ሊያደርጓችሁ ይችላሉ። ጠበቃ፣ ሐኪም፣ ቄስ፣ የቅርብ ጓደኛ እና ቤተሰብ እንዲጐበኛችሁ የማድረግ መብት አላችሁ። ለዝቅተኛ ክፍያ የመስራት መብት አላችሁ።

ያለመኖሪያ ፈቃድ እዚህ መኖር ምን ያህል ከባድ ነው ?
በዚህ ሁኔታ የጤና እና ሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶችን ማግኘት በጣም ከባድ ነው። በሕገ-ወጥ መንገድ ለመስራት ዕድል ይኖራል። የጥገኝነት ማመልከቻቸው ውድቅ ከሆነ በኋላ ምናልባት ግለሰቡ ያለወረቀት በዴንማርክ መኖርን ሊመርጥ ይችላል።

ከታሰርኩ ምን ይሆናል ?
ማንነታችሁን በተመለከተ ፖሊስ ጥርጣሬ ካለው ማንነታችሁን ለማጣራት ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሊወስዳችሁ ይችላል። ፍርድ ቤት ከመቅረባችሁ በፊት ለ72 ሰዓታት ልትታሰሩ ትችላላችሁ። ጠበቃ ይሰጣችኋል።

ማን ሊረዳ ይችላል ?
ነፃ የሕግ ምክር አገልግሎት :-

« ዘ ትራምፖሊን ሀውስ » የሚባል ማህበር
አድራሻ :- The Trampoline House
Thoravej 7, ground floor DK-2400 Copenhagen NV Denmark
ስልክ :- Tel: (+45) 32 20 02 25
ኢሜል :- info@trampolinehouse.dk
ድረ-ገፅ :- http://www.trampolinehouse.dk

Asylret (« የጥገኝነት መብት » የሚባል ማህበር)
ኢሜል:- info@asylret.dk
ድረ-ገፅ:-http://www.asylret.dk

Refugees Welcome (የስደተኞች ተቀባይ)
አድራሻ :- Dronningensgade 14 DK-1420 Copenhagen K Denmark
ስልክ :- (+45) 50 55 80 11
ኢሜል:- kontakt@refugeeswelcome.dk
ድረ-ገፅ :- http://www.refugeeswelcome.dk

RUSK (« ሩስክ » የሚባል ቡድን)
ድረገፅ :- http://www.rusklaw.org
አድራሻ :- Baggesensgade 6, kld. th. 2200 København N
የሥራ ሰዓት : – ሰኞ ማታ ከ12 እስከ አንድ ሰዓት ድረስ።
ስልክ :- 28 25 53 20
ኢሜል :- kontakt@rusklaw.org

LGBT Denmark(የተመሳሳይ ፆታ የወሲብ ባህሪያት ላላቸው ሰዎች የሕግ ምክር አገልግሎት ሰጪ እና የፖለቲካ ቡድን ነው።)
ፖስታ :- Postboks 1023, 1007 København K
አድራሻ: ፮ Nygade 7, 2., 1164 København K
ኢሜል:- lgbt@lgbt.dk
ስልክ :- 33 13 19 48

LGBT Asylum (ይህም የተመሳሳይ ፆታ የወሲብ ባህሪያት ላላቸው ሰዎች የሕግ ምክር አገልግሎት ሰጪ እና የፖለቲካ ቡድን ነው።)
ድረ-ገፅ :- http://www.lgbtasylum.dk
ስልክ :- 45 71 52 33 97
ኢሜል :-: lgbtasylumdk@gmail.com

የዴንማርክ የስደተኞች ጉዳይ ምክር ቤት (Danish Refugee Council) መንግሥታዊ ያለሆነ ድርጅት ነው
አድራሻ :-Borgergade 10 DK – 1300 København K
ስልክ :-33 73 50 00
ፋክስ:- 33 91 45 07
ኢሜል :- drc@drc.dk
ድረ-ገፅ :- http://www.flygtning.dk

የጤና አገልግሎት የሚሰጡ ክሊኒኮችና ተቋማት :-
ወረቀት ለሌላቸው ስደተኞች የጤና አገልግሎት የሚሰጥ ክሊኒክ በኮፐንሀገን ይገኛል። የሚተዳደረው በዴንማርክ የቀይ መስቀል ማህበር፣ በስደተኞች ጉዳይ ምክር ቤት እና በዴንማርክ የሕክምና ባለሙያዎች ማህበር ነው።
አድራሻ :-  Rewentlowsgade 10, 1651 København V
ዘ ትራምቦሊን ሀውስ የተባለው ድርጅትም ዘወትር ረቡዕ ከ10 እስከ 12 ሰዓት (ከሰዓት በኋላ) የሕክምና ምክር አገልግሎት ይሰጣል።

ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ ሰዎች የዴንማርክ የሕፃናት አድን ድርጅት (ሬድ ባርኔት)
አድራሻ :- Save the Children Denmark (Red Barnet) Rantzausgade 60 2200 Copenhagen N Denmark
ስልክ :- +45/35.36.55.55
ፋክስ :- +45/35.39.11.19 ኢሜይል: SK@redbarnet.dk
ድረ-ገፅ :- http://www.redbarnet.dk

ቤልጅየም
ምን ዓይነት ቋንቋ ይናገራሉ ?
ሦስት የስራ ቋንቋዎች አሉ። ፈረንሳይኛ፣ ደች (የኔዘርላንድ ቋንቋ) እና ጀርመንኛ ናቸዉ።

ከካሌ ምን ያህል ይርቃል ?
የቤልጅየም ድንበር ከካሌ በስተምስራቅ 60 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል። ትላልቅ ከተሞች ብሩዥ (110 ኪ.ሜ.) እና ዋና ከተማዉ ብራስልስ (200 ኪ.ሜ.) ርቀት ላይ ይገኛሉ።

የጥገኝነት ጥያቄ ሂደቱ እንዴት ይፈፅማል?
የጥገኝነት ጥያቄ ስደተኛው ቤልጅየም በገባ በ8 ቀናት ውስጥ በውጭ ዜጐች ጉዳይ ቢሮ ወይም በፌዴራል ፖሊስ ቢሮ መቅረብ አለበት። ማመልከቻውን አጥንቶ ውሳኔ የሚሰጠው (ጥገኝነት ለመስጠት፣ ለከልከል ወይም ልዩ ጥብቃ ለማድረግ) የስደተኞች እና ዜግነት የሌላቸዉ ሰዎቸ ጉዳይ ዋና ኮሚሽነር ቢሮ ነው። ቃለ መጠይቅ ይደረግላችኋል የምትሞሉት መጠይቅ ፎርም ይሰጣችኋል። አስተርጓሚ እንዲሰጣችሁ መጠየቅ አለባችሁ። ጠበቃ ወይም የምታምኑት ሰው መኖር አለበት። ለሕግ የምክር አገልግሎት እርዳታ ማግኘት ትችላላችሁ።

ሂደቱ ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል ?
ለመጀመሪያ ማመልከቻ ቢያንስ 6 ወራት ጊዜ ይፈጃል።

ውሳኔ በመጠበቅ ላይ ሳለሁ እንዴት መኖር እችላለሁ? አበል አገኛለሁ?
በሂደቱ ወቅት በመቆያ ማዕከል ውስጥ (ከ75 እስከ 800 የሚሆኑ አልጋዎች አሉ) ቦታ ይሰጣችኋል። ምግብ፣ አልባሳት፣ የቀን አበል፣ የሕክምና፣ የማህበራዊ እና ሥነ-ልቦናዊ ድጋፍ፣ የሕግ ጉዳይ ውክልና እና ትርጉም፤ እና ስልጠናም ሊሰጣችሁ ይገባል። የሕክምና ምርመራ ይደረግላችኋል፤ መብታችሁን የሚያስረዳ በራሪ ወረቀት ይሰጣችኋል። ከ4 ወራት በኋላ በአንድ ቤት ውስጥ ቦታ ሊሰጣችሁ ይገባል። የሕክምና አገልግሎት አቅርቦት በአስቸኳይ የሕክምና እርዳታ ተቋም ወይም « CPAS/OCMW) በኩል ልታገኙ ይገባል። የመኖሪያ ቤታችሁን እና መደበኛ የማደሪያ ቦታችሁን አድራሻ ማሳወቅ ያስፈልጋችኋል። ሐኪም ዘንድ መሄድ የሚያስችላችሁን ሰርተፍኬት ሊሰጧችሁ ይገባል። በጥቂት ከተሞች መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የጤና አገልግሎቶችን በተመለከተ ሌሎች አማራጮችን ያቀርባሉ።

አቤቱታ :- የደብሊን ሦስተኛ ደንብ እና የቤልጅየም የአቤቱታ ሥርዓት የሰብዓዊ መብቶችን በመጣስ ተተችቷል። አቤቱታዎች በ10 ቀናት ውስጥ (ለፈጣን ሂደት) ወይም በ30 ቀናት ውስጥ (ለመደበኛ ሂደት) ለውጭ ዜጐች ጉዳይ የሕግ ክርክር ምክር ቤት (Conseil du contentieux des étrangers: CCE በፈረንሳይኛ / Raad voor Vreemdelingenbetwistingen: RvV በደች) የግድ ማቅረብ አለበት። አቤቱታ ለሁለተኛ ጊዜ ለመንግሥት ምክር ቤት (Conseil d’Etat : CE በፈረንሳይኛ / Raad van State : RvS በደች) ሊቀርብ ይችላል።

ከ18 ዓመት በታች ከሆንኩስ?
ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች እና ቤተሰቦቻቸው ወደ ማቆያ ማዕከል አይገቡም። 18 ዓመት አስኪሞላቸው ድረስ ልጆች ትምህርት መከታተል እና መሠረታዊ የደች ቋንቋ ትምህርት ሊወስዱ ይገባል። ምንም እንኳ ሕጋዊ ነዋሪ ባትሆኑም የፈተና ሰርተፍኬት ማግኘት ትችላላችሁ። ከቤተሰቦቻቸው የተነጠሉ ልጆች በፍርድ ቤት የሚወክላቸው ተንከባካቢ በመንግሥት ይመድብላቸዋል።

ቤተሰቦቼስ?
ቤተሰቦቻችሁን ለማምጣት እና እንዲቀላቀሏችሁ ለማድረግ ምናልባት ረጅም ጊዜ ሊወስድ ይችላል። ቤተሰብ የሚባለው ባል/ሚስት፤ ወይም የተመዘገበ ፍቅረኛ፣ ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች፤ ወይም ከ18 ዓመት በላይም ቢሆን የካል ጉዳተኛ ከሆነ፤ ወይም ወላጆች (ስደተኛው ግለሰብ ከ18 ዓመት በታች ከሆነ እና ብቸኛ ከሆነ) ያካትታል። ከአንድ በላይ ሚስት ወይም ባል እውቅና አይሰጠውም። ከተለያዩ ሰዎች የተወለዱ ልጆች ግን እውቅና ይሰጣቸዋል።

መስራት እና መማር እችላለሁ?
ለጥገኝነት ከመለካታችሁ ከ6 ወራት በኋላ ለስራ ፈቃድ ማመልከት ትችላላችሁ። ከ18 ዓመት በታች የሆነ ሰው ትምህርት የመከታተል መብት አለው። ሕጋዊ ወረቀት የሌላቸው አዋቂዎች በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመከታተል አልተፈቀደላቸውም። ከ18 ዓመት በታች የሆነን ሰው ትምህርት ቤቶች ለምዝገባ አይከለክሉም። ትምህርት ቤቱ ድጐማ ስለሚያገኝ የሕይወት ዋስትና (ኢንሹራንስ) ይገባላቸዋል። የትምህርት ቤት ወጪያችሁን መሸፈን ካልቻላችሁ ጉዳዩን ለትምንህርት ቤቱ ወይም ለአስቸኳይ የሕክምና እርዳታ ተቋም (OCMW) ማሳወቅ ትችላላችሁ።

መማር :- በቤልጅየም ሕጋዊ ወረቀት የሌላቸውና በዩኒቨርሲቲ ወይም ኮሌጅ የሚማሩ ሰዎችን የሚመለከት የተለየ ሕግ  የለም። ለመማር መጠየቅ ያለባችሁ ራሱ የዩኒቨርሲቲውን ነው፤ እያንዳንዱ ዩኒቨርሲቲ የራሱን አሰራር ሕግ ነው የሚከተለው።

ስራ :- ጊዜያዊ የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ሰዎች የስራ ፈቃድ (arbeidskaart) ጠይቀው መስራት ይችላሉ። የስራ ፈቃዳቸው የሚያገለግለው ጊዜያዊ የመኖሪያ ፈቃዳቸው ሕጋዊነት እስከሚያበቃበት ጊዜ ብቻ ነው። በዚህ የስራ ፈቃድ (work permit C) የተወሰኑ የስራ ዓይነቶችን ብቻ ነው መስራት ይሚቻለው። አሰሪው/ቀጣሪው ድርጅት (ተቀጣሪው አይደለም) ለግለሰቡ የስራ ፈቃድ መጠየቅ አለበት። የስራ ፈቃድ ካልሰጧችሁ አቤቱታ ማቅረብ ትችላላችሁ።

ጥገኝነት ከተሰጠኝ ምን ይሆናል ?
እውቅና የተሰጣቸው ስደተኞች የስራ ፈቃድ አያስፈልጋቸውም። እንደ ማንኛውም የቤልጅየም ዜጋ በተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ መስራት ይችላሉ።

ጥገኝነት ካላገኘሁ ወይም ከሀገር እንድወጣ ከተወሰነስ ?
በ30 ቀናት ውስጥ ከሀገር እንደትወጡ እስኪደረግ ድረስ ወደ መቀበያ ማዕከሉ እንድትመለሱ ትጠየቃላችሁ።

ከታሰርኩስ ?
ምንም ነገር ያለመናገር መብት አላችሁ፤ መብታችሁ እና የቀረበባችሁ ክስ እንዲነገራችሁ እንዲሁም ነፃ አስተርጓሚ እንዲኖራችሁ መብት አላችሁ። የሕግ አገልግሎት እርዳታ መጠየቅ ትችላላችሁ።

የማቆያ አፈፃፀም እና መብቶች
ቤልጅየም ውስጥ ወደ ማቆያ ማዕከል የምትወሰዱት ድንበር ላይ ወደ ቤልጅየም ስትገቡ ፖሊስ በያዛችሁ ወቅት ነው። ከ2 እስከ 8 ወራት በማቆያ ማዕከል ዉስጥ ልትቆዩ ትችላላችሁ። ከዚያ ውጪ ወደ ማቆያ የምትወሰዱት የጥገኝነት ማመልከቻ አቀራረብ ሂደቱን በትክክል ሳትከተሉ ስትቀሩ ወይም ከዚህ በፊት በሌላ ሀገር የጥገኝነት ጥያቄ አቅርባችሁ ከሆነ ነው። የማቆያ ቦታዎች ዝግ ማዕከል ሲሆኑ የሚተዳደሩት በውጭ ዜጐች ጓዳይ ቢሮ ነው።

ያለወረቀት መኖር እዚህ ምን ያህል ቀላል ነው?
ቤልጅየም ውስጥ ያለወረቀት ራስን ማቆየት እና ስራ መፈለግ ይቻላል።

ማን ሊረዳ ይችላል ?
ቤልጅየም ውስጥ የሕክምና እርዳታ ለማግኘት :-
Medimmigrant (ሜዲሚግራንት)
አድራሻ :- Gaucheretstraat 164 B – 1030 Brussel (በብሩሰልስ ከተማ)
ስልክ :- tel: +32 (2) 274 14 33
ፋክስ:- +32 (2) 274 14 48
ኢሜል :- secr@medimmigrant.bemedimmigrant.be

ለሥራ :-
ORCA – Organisatie voor Clandestiene Arbejdsmigranten (ወረቀት የሌላቸው ስደተኛ ሠራተኞች ድርጅት)
አድራሻ :- Gaucheretstraat 164 B – 1030 Brussel (በብሩሴል ከተማ)
ስልክ :- +32 2 274 14 31 f
ፋክስ :- +32 2 274 14 48
ኢሜል :- info@orcasite.beorcasite.be

የቤልጅየም የስደተኞች ጉዳይ ምክር ቤት (Belgian Refugee Council : መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ነው)
ለጥገኝነት ጥያቄዎች ሂደቱን በተመለከተ ጥያቄዎችን የመመለስ የማብራራት አገልግሎት በሳምንቱ የስራ ቀናት ከ8 እስከ 11 ሰዓት ከሰዓት በኋላ አገልግሎት ይሰጣሉ። በማቆያ ማዕከል ያሉ ሰዎችን ወይም የቤተሰብ መቀላቀልን በተመለከተ ሊረዱ ይችላሉ።አድራሻ :- Rue des palais 154 1030 SCHAERBEEK (ሻኤርቤክ ከተማ)
ስልክ :- Phone: 02/537.82.20
ኢሜል :- info@cbar-bchv.becbar-bchv.be (በእንግሊዝኛ፣ ፈረንሳይኛ እና ደች ቋንቋዎች መረጃ ይሰጣል)

የተፈናቃይ ሰዎች እርዳታ (Aide aux personnes déplacées / መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ነው)
አድራሻ :- Rue du Marché 35 B – 4500 Huy (ሁይ ከተማ)
አስተናጋጅ:- Régine Thiebaut (ወ/ሮ ሪዢን ቲቦ)
ስልክ: +32 (0) 85 21 3481
ፋክስ :- +32 (0) 85 23 0147
ኢሜል :- apd.hvo.holsbeek@belgacom.net
ድረ-ገፅ :- http://www.aideauxpersonnesdeplacees.be

መንግሥታዊ ተቋም :- የስደተኞች እና ዜግነት የሌላቸዉ ሰዎች ጉዳይ ድርጅት የዋና ኮሚሸነር ቢሮ (Office of the Commissioner General for Refugees and Stateless Persons)
ድረ-ገፅ :- http://www.cgra.be

ስዊድን
ምን ዓይነት ቋንቋዎች ይነገራሉ ?
የስራ ቋንቋ ስዊድሽ (ስዊድንኛ) ሲሆን እንግሊዝኛም በስፋት ይነገራል።

ከካሌ ምን ያህል ይርቃል ?
በየብስ የስዊድን ድንበር ከካሌ በሰሜን-ምስራቅ 1200 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል። ድንበር እንደተሻገራችሁ የምታገኙት የመጀመሪያው ትልቅ ከተማ ማልሞ (Malmö) ይባላል።ዋና ከተማው ስቶክሆልም 1800 ኪሎ ሜትር ይርቃል። የባቡር መስመር በቤልጅየም፤ ጀርመን እና ዴንማርክ በኩል ያልፋል።

የጥገኝነት ጥያቄ ሂደቱ እንዴት ይፈፀማል?
የስዊድን ድንበር ውስጥ እንደገባችሁ (የአውሮፕላን ጣቢያዎችን ጨምሮ) ጥገኝነት መጠየቅ እንድምትፈልጉ ማሳወቅ ትችላላችሁ። ከዚያ ወደ አንዱ የስደተኞች ቦርድ ማመልከቻ ማዕከል ትወስዳላችሁ።

ውሳኔ ለማግኘት ምን ያህል ጊዜ ይፈጃል ?
የጥገኝነት ጥያቄ ውሳኔ በአማካይ በ147 ቀናት ይሰጣል። ለጥገኝነት ጥያቄ ያቀረባችሁት ምክንያት ደካማ ነው ከተባለ በፍጥነት ውሳኔ ልታገኙ ትችላላችሁ።

ውሳኔ በመጠበቅ ላይ ሳለሁ እንዴት መኖር እችላለሁ ? አበል አገኛለሁ ?
በመደበኛ የመኖሪያ አካባቢዎች ወይም በማዕከል ውስጥ በሚገኙ ሕንፃዎች ውስጥ ቦታ ይሰጣችኋል። ጥገኝነት ጠያቂዎች በማዕከል ለመኖር ሊመርጡ ይችላሉ። ነገር ግን በዚህ ጊዜ የስደተኞች ቦርድ ወደ ሚመድባቸው ከተማ መሄድ ያስፈልጋቸዋል።
ገንዘብ ካላችሁ የመጠለያ ቤት ወጪ መክፈል አለባችሁ። ካልሆነ ግን በነፃ መጠለያ ታገኛላችሁ። ብቻቸውን የሆኑ (ቤተሰብ የሌላቸው) ሰዎች አንድ የመኖሪያ ክፍል መጋራት ያስፈልጋቸዋል። ቤተሰብ የሆኑ ሰዎች የራሳቸው ክፍል ይኖራቸዋል። ነገር ግን የመኖሪያ ሕንፃ ከሌሎች ጋር ሊጋሩ እንደሚችሉ መጠበቅ አለባቸዉ። በሂደቱ ወቅት ወደ ሌላ አካባቢ (ቦታ) ልትዛወሩ ትችላላችሁ።
የጥገኝነት ጥያቄያችሁ በሂደት ላይ ባለበት ወቅት የወር አበል ይኖራችኋል። ይህ አበል ለልብስ፣ ለሕክምና አገልግሎት፣ ለጥርስ ህክምና፣ ለግል ንፅህና መጠበቂያ የሚውሉ ምርቶችን ለመግዛት እና ለሌሎች ለትርፍ ጊዜ የመዝናኛ ወጪዎች ታስቦ የሚሰጥ ነው። የሕክምና ወጪ በከፊል  ይደጐማል። ጥገኝነት ጠያቂዎች የቀን አበል የሚሰጣቸው በስደተኞች ቦርድ ከሆነ የባንክ ካርድ ተሰጥቷቸው ገንዘቡ ወደዚያ ይገባላቸዋል። ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሟሟላት የሚያስፈልጉ ለምሳሌ የብርድ ወቅት ልብሶች እና የዓይን መነጽር ለመሳሰሉት መግዣ ጥገኝነት ጠያቂዎች ተጨማሪ አበል መጠየቅ ይችላሉ። አበሉ በአንፃሩ ዝቅተኛ ነው (ብቻውን ለሚኖር አንድ አዋቂ ግለሰብ 252 €(ዩሮ) ነው)። ውሳኔ እስከምታገኙ ድረስ ሥራ መስራት ብዙውን ጊዜ ይፈቀዳል።

መስራት እና መማር እችላለሁ ?
ውሳኔ በመጠበቅ ላይ ሳላችሁ መማር ወይም የሥራ ፈቃድ ማግኘት ትችላላችሁ። ጊዜያዊ ወይም ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ካገኛችሁ እንደማንኛውም የስዊድን ዜጋ ስዊድን ውስጥ መማር እና መስራት ትችላላችሁ። ስዊድን ውስጥ የጥገኝነት የመኖሪያ ፈቃድ ካላችሁ በነፃ መማር ትችላላችሁ።

ጥገኝነት ከተሰጠኝ ምን ይሆናል?
ማመልከቻችሁ ተቀባይነት ካገኘ ምናልባት የስዊድን ቋንቋ ለመማር ብቁ ያደርጋችኋል። የመኖሪያ ፈቃድ ካገኛችሁ እና የመግቢያ ዕቅድ ከተፈቀደላችሁ የሕዝብ የቅጥር አገልግሎት ቢሮ ቤት እንድታገኙ ይረዳችኋል። የመኖሪያ ፈቃድ ያገኛችሁት በቅጥር ምክንያት ከሆነ ቤት በራሳችሁ የመፈለግ ግዴታ አለባችሁ። የመኖሪያ ቤታችሁን በራሳችሁ ካገኛችሁ ወጪውን ራሳችሁ የመሸፈን ግዴታ አለባችሁ። ወጪውን መሸፈን ካቃታችሁ የስደተኞች ቦርድ ወደ ሚመድባችሁ ማዕከል መዛወር ትችላላችሁ።

ጥገኝነት ካልተሰጠኝ ወይም ከሀገር እንድወጣ ቢወሰንስ?
የስደት ጉዳይ ቦርድ በራሳችሁ ስዊድንን ለቃችሁ በትወጡ ይመርጣል። የጉዟችሁን ጉዳይ ለመወያየት ቀጠሮ ይሰጣችኋል። እንድትለቁ ሊያደርጓችሁ ይሞክራሉ ነገር ግን ቢያንስ ውሳኔው ከተወሰነ በኋላ እስከ 3 ሳምንት ድረስ ይህን ማድረግ አይችሉም። እነሱ በሚሉት የምትስማሙ ከሆነ መረጃችሁን አሳልፈው ለፖሊስ ይሰጣሉ። በፊት የስራ ፈቃድ ተሰጥቷችሁ ከነበረ የጥገኝነት ጥያቄያችሁ ውድቅ ከሆነ በኋላ ዋጋ አይኖረውም። መደበኛ ስራ የነበራችሁ ከሆነና ግብር እየከፈላችሁ ከሆነ ምናልባት ልትቀጥሉ ትችላላችሁ (ቀጣሪያችሁ ካላወቀ ወይም የጥገኝነት ጥያቄያችሁ ውድቅ ለመሆኑ ግድ ከሌለው)።
የግብር መስሪያ ቤት ባለሥልጣናት የሰራተኞችን መረጃ ወዲያው ለፖሊስ አይሰጡም። ነገር ግን አንዳንዴ ከፖሊስ ጋር በመሆን በስራ ቦታ በመገኘት የሰራተኞችን የሥራ እና የመኖሪያ ፈቃድ ቁጥጥር ሊያካሄዱ ይችላሉ።

የማቆያ ሂደት እና መብቶች
ማንነታችሁን ለማጣራት፣ ከሀገር መዉጣት አለባችሁ ወይስ መቆየት ትችላላችሁ የሚለዉን ለመወሰን ወደ ማቆያ ማዕከል ሊውስዷችሁ ይችላሉ። በማቆያ ማዕከል ሊያስገቧችሁ የሚገባው ከሀገር እንድትወጡ ከተወሰነ እና ከመፈፀሙ በፊት ልትደበቁ ትችላላችሁ ብለው ያመኑበት ምክንያት ካላቸው ብቻ ነው። ማንነታችሁን ለማጣራት የሚደረግ ማቆየት ከ48 ሰዓት ሊበልጥ አይችልም። ከዚህ ውጭ በሆኑ ምክንያቶች ወደ ማቆያ ከተወሰዳችሁ ጊዜው ከ2 ሳምንት እስከ 2 ወር ሊረዝም ይችላል።

ከታሰርኩስ?
ፖሊስ ካሰራችሁ መብታችሁን የሚያስረዳ ፅሑፍ ሊሰጣችሁ ይገባል። (ስዊድንኛ የማትናገሩ ከሆነ ትርጉሙ በሌላ ቋንቋ ስለሚኖር ይሰጣችኋል)። ምናልባት ጠበቃ እና አስተርጓሚ ሊኖራችሁ ይችላል። ለዘመዶቻችሁ ማሳወቅ ትችላላችሁ።

ያለ መኖሪያ ፈቃድ እዚህ መኖር ይቻላል ?
ስደተኞች፤ ‹‹ጊዜ የማይሰጠው (ሊዘገይ የማይገባ) የሕክምና አገልግሎት›› በመባል ለሚታወቁ የተለያዩ የጤና አገልግሎቶች አቅርቦት በህግ የተፈቀደላቸው ነው። ይህንን ግን ሆስፒታሎች በተለያዩ መልኩ ነው የሚረዱት። የጤና አገልግሎት ስራተኞች በታማኝነት ያገለግሏችኋል፤ ይህም ማለት ፖሊስ እየፈለጋችሁ ካልሆነ እና በተለይ ስማችሁን ጠርቶ በሆስፒታል ካልጠየቀ በስተቀር ማንኛውንም እናንተን የሚመለከት መረጃ አሳልፈው ለባለሥልጣናት አይሰጡም።
ስዊድን ውስጥ እያንዳንዱ ትምህርት ቤት የውጭ ሀገር ዜጐች ልጆች በትምህርት ቤቱ ውስጥ መማር ይችላሉ ወይስ አይችሉም የሚለውን መምረጥ ይችላል። ሕጋዊ ያልሆነ አዋቂ ሰው የመማር መብት የለውም። ምናልባት የአዋቂዎች ከፍተኛ ትምህርት ቤት (folkhögskolor) መግባት ይችላል። ፖሊስ በስዊድን ያለመኖሪያ ፈቃድ እየኖራችሁ ነው ብሎ ለማመን ምክንያት ካለው የመታወቂያ ወረቀት የመጠየቅ እና የማረጋገጥ መብት አለው። ብዙውን ጊዜ መታወቂያ የሚጠይቁት በተደጋጋሚ ክንውኖች፤ ለምሳሌ የትራፊክ ቁጥጥር ጊዜ እና የሆቴልና የምግብ ቤት ፍተሻ ወቅት ነው።
የጥቁር ገበያ ሥራ ከሆነ የምትሰሩት ምንም ዓይነት የቅጥር ዋስትና ወይም የሕክምና ጊዜ ፈቃድ መብት የላችሁም። ነገር ግን ምን ጊዜም ቢሆን ምክንያታዊ የሆነ (ተገቢ እና ተመጣጣኝ) በሰዓቱ የሚፈፀም ክፍያ የማግኘት መብት አላችሁ። ሳክ (SAC) የተባለው የስራ ማህበር ይህን በተመለከተ ሊረዳችሁ ይችላል።

ማን ሊረዳ ይችላል ?

« ማንኛውም ሰው ሕገ-ወጥ አይደለም-ስዊድን » የተባለው መንግስታዊ ያልሆነ የእርዳታ ቡድን (No One Is Illegal – Sweden)
ኡፕሳላ ከተማ : –
ኢሜል :- uppsala@ingenillegal.org
ስልክ:- 073 – 95 96 150
ስቶክሆልም ከተማ :-
-ኢሜል :- stockholm@ingenillegal.org
-ስልክ :- 0707 – 33 61 07 (ይህ ስልክ ቁጥር ለሕግ ምክር አገልግሎት ብቻ ነው)
እስተርሱንድ ከተማ :-
-ኢሜል:-ostersund@ingenillegal.org
ግትቦርግ ከተማ :-
-ኢሜል:- goteborg@ingenillegal.org ወይም  momo@ingenillegal.org
-ስልክ:- 0704-37 75 24
ኖርቦተን ከተማ :-
-ኢሜል:-norrbotten@ingenillegal.org

ወረቀት ለሌላቸው እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ነፃ የሕክምና አገልግሎት የሚሰጡ የጤና ማዕከላት :-

Läkare i Världen i Stockholm (የዓለም ሐኪሞች – ስዊድን በስቶክሆልም ከተማ)
ስልክ: 08-6646687
ድረ-ገፅ :- http://www.lakareivarlden.org

Svenska Röda Korset (Stockholm) (የስዊድን ቀይ መስቀል ማህበር በስቶክሆልም ከተማ)
ስልክ: 0709-406723
ስልክ: 9.30-11.30
ድረ-ገፅ :- http://www.redcross.se

Rosengrenska stiftelsen (Göteborg) (የጤና አገልግሎት ማዕከል በግትቦርግ ከተማ)
ስልክ: 0704-066670
ኢሜል :- kliniken@rosengrenska.org
ድረ-ገፅ :- http://www3.rosengrenska.org

Deltastiftelsen (Malmö) (የጤና አገልግሎት ማዕከል በማልመ ከተማ)
ኢሜል deltastiftelsen@gmail.com
ድረ-ገፅ :- http://www.deltastiftelsen.se

Liljengrenska (Varberg) (የጤና አገልግሎት ማዕከል በቫርበርግ ከተማ)
ስልክ: 0768-939593 (ዘወትር ማታ ከ12 እስከ 1 ሰዓት)
ኢሜል :- liljengrenska@hotmail.com

Porten (Borås) (የጤና አገልግሎት ማዕከል በቦራስ ከተማ)
ስልክ:- 0735-632080 (ዘወትር ረቡዕ ማታ ከ11.30 እስከ 1 ሰዓት)
ኢሜል :- krook99@gmail.com

Tinnerökliniken (በእስተርግትላንድ፤ ሊንከፒንግ፤ እና ኖርከፒንግ ከተማዎች)
ስልክ :- 0733-225887 (ለታካሚ ደዋዮች መልዕክት የሚቀበል)
ኢሜል :- info@papperslosa.se

ከዚህ ቀጥሎ በተሰጠው ድረ-ገፅ በስዊድን ውስጥ ስላለው የጥገኝነት ሂደት አፈፃፀም የበለጠ መረጃ በእንግሊዝኛ፣ አረብኛ፣ እስፓኒሽኛ፤ እና በስዊድንኛ ማግኘት ትችላላችሁ።
ድረ-ገፅ :- http://www.ingenillegal.org/node/357

ኦስትሪያ
ምን ዓይነት ቋንቋ ይነገራል ?
የሥራ ቋንቋ ጀርመንኛ ነው። ምናልባት በትላልቅ ከተሞች እንግሊዝኛ ሊነገር ይችላል።

ከካሌ ምን ያህል ይርቃል ?
በየብስ የኦስትሪያ ድንበር ከካሌ በስተደቡብ-ምሥራቅ በኩል1050 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል። የኦስትሪያ ድንበር ውስጥ ከገቡ በኋላ የሚያገኙት የመጀመሪያው ትልቅ ከተማ እንስቡርግ ይባላል። ዋና ከተማው ቪዬና 1300 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል። የባቡር መስመር በጀርመን እና ስዊዘርላንድ በኩል ያልፋል።

የጥገኝነት ጥያቄ ሂደቱ እንዴት ይፈፀማል?
ጥገኝነት ለመጠየቅ ከሦስቱ ወደ አንዱ የመቀበያ ማዕከል (Erstaufnahmestelle) መሄድ አለባችሁ። ወደ ኦስትሪያ የገባችሁት በአዎሮፕላን ከሆነ በቪዬና/ሽዌሻት የአዉሮፕላን ጣቢያ ውስጥ ወይም ደግሞ በትሬሽክርሽን ከተማ (በቪዬና አካባቢ ይገኛል)፣በታልሀም ከተማ (በላይኛው ኦስትሪያ ሳልዝቡርግ፣ ቪልስ እና ሊንዝ አጠገብ ይገኛል) ለጥገኝነት ማመልከት ይቻላል። በፖሊስ ከተያዛችሁ እዚያው ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ጥገኝነት መጠየቅ ትችላላችሁ። ጥገኝነት እየጠየቃችሁ እንደሆነ በግልፅ አስረዱ። በጀርመንኛ ማለት ያለባችሁ « Ich moechte Asyl » ሲሆን በአማርኛ ፊደል « ኢሽ መሽተ አዚል » ይሆናል።ለሌላ አካል የሚያስተላልፋችሁ ከሆነ ይህንኑ ደጋግማችሁ አስረዱ። እናንተን የሚመለከት መረጃ ይፈልጋሉ፤ ስማችሁን፣ የትውልድ ቀናችሁን፣ ዜግነታችሁን እና የምትናገሩትን ቋንቋ ይጠይቋችኋል። የጣት አሻራችሁን ይወስዳሉ። የትውልድ ሀገራችሁን ለምን እንደለቀቃችሁ፣ ኦስትሪያ ከመግባታችሁ በፊት ከየት እንደተነሳችሁ እና እንዴት ኦስትሪያ እንደገባችሁ ይጠይቋችኋል። ይህን ካደረጉ በኋላ ወደ መቀበያ ማዕከል ሊወስዷችሁ ይገባል።

ምን ያህል ጊዜ ይፈጃል ?
ሂደቱ ሳምንታት ወይም ወራት ሊፈጅ ይችላል። ከዋናው ቃለ መጠይቅ በኋላ በሳምንታት ወይም ወራት ጊዜ ውስጥ የመጀመሪያውን ውሳኔ ታገኛላችሁ። ከተከለከላችሁ አቤቱታ የማቅረብ ዕድል አላችሁ። ይህ ዕድል ከውሳኔ በኋላ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚሰጥ ጠይቃችሁ እወቁ።

ጥገኝነት ከተሰጠኝ ምን ይሆናል?
ከጥገኝነት ጥያቄው ውሳኔ ውጭ ወደ ትውልድ ሀገራችሁ እንድትመለሱ ማድረግ የማይችሉ ከሆነ ምናልባት በየዓመቱ ሊራዘም የሚችል የአንድ ዓመት ቪዛ (subsidiärer Schutz) ሊሰጣችሁ ይችል የሆናል። የቪዛ ማራዘሚያ ቀነ-ገደቡን ጠይቃችሁ እወቁ። እንድትሰሩ የሚፈቀድላችሁ ሲሆን የማህበራዊ አገልግሎትም ታገኛላችሁ።

ውሳኔ በመጠበቅ ላይ ሳለሁ እንዴት መኖር እችላለሁ? አበል አገኛለሁ?
የኦስትሪያ መሠረታዊ አገልግሎቶች ሥርዓት (Grundversorgung) ለጥገኝነት ጠያቂዎች እና ከመደበኛው የማህበራዊ ሥርዓት ውጪ ለሆኑ የውጭ ዜጐች የቤት፣ የምግብ እና የሕክምና አገልግሎት ሊሰጥ ይገባል። መሠረታዊ እንክብካቤ አገልግሎት በሁለት መንገድ ይሰጣል፤ ሀ) በማዕከል መጠለያ ቤት አቅርቦት ለ)በራሳቸው ቤት እግኝተው ለሚኖሩ ለቤቱ አያያዝ የሚረዳ ድጎማ በመስጠት ነው። በመጠለያ ቤት ለሚኖሩ የሚደረገው እንክብካቤ አገልግሎት የቤት አቅርቦት፣ የጤና ኢንሹራንስ፣ የምግብ እና የኪስ ገንዘብ (40 ዩሮ በወር) ነዉ። በራሳቸው ለሚኖሩ ሰዎች የጤና ኢንሹራንስ፣ ቤቱን ደህና አድርጐ ለመያዝ (180 ዩሮ) እና ለቤት ኪራይ (110 ዩሮ) ይሰጣቸዋል። እንደ እውነቱ ከሆነ ብዙውን ጊዜ ለብቻ ለመኖር የገንዘብ ድጋፍ አይሰጥም። ወንጀል የሠራ እና የተረጋገጠበት ወይም ገቢ ያለው ሰዉ የሚሰጠው መሠረታዊ እንክብካቤ አገልግሎት ይቀነስበታል። ለመሠረታዊ እንከብካቤ አገልግሎት ለማመልከት ወረቀቶቻችሁን በመያዝ አገልግሎቱን የሚሰጡ ሰዎች ወዳሉበት ቦታ በመሄድ ቀጠሮ መውሰድ አለባችሁ። እንድትኖሩ ከተላካችሁበት ቦታ ይልቅ በሌላ አካባቢ/ቦታ መኖር ከመረጣችሁ ምንም ዓይነት ጥቅማ ጥቅም አታገኙም (Grundversorgung)።

መስራት እና መማር እችላለሁ ?

መማር (ትምህርት) :- የመኖሪያ ፈቃድ ይኑራቸውም አይኑራቸውም ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች መማር አለባቸው። ነገር ግን ትምህርት ቤቶች ልጆችን ላይቀበሉ ይችላሉ፤ በተለይ በማዕከል እና በካምፕ ውስጥ። የሥራ ጥልጠና ማግኘት የበለጠ ከባድ ነው። ዳኔይዳ የሚባል ድርጅት (ድረ-ገፅ :- http://www.danaida.at ) ነፃ የጀርመንኛ ቋንቋ እና ማንበብና መፃፍ የሚያስችሉ ትምህርቶች የውጭ ዜጋ ለሆኑ ሴቶች የሚሰጥ ከመሆኑም ባሻገር የምግብ ዝግጅት እና የኮምፒዩተር ትምህርትም ይሰጣቸዋል።

ሥራ :- የጥገኝነትጥያቄገናበሂደትላይእያለኦስትሪያውስጥሥራመስራትበሕግአልተፈቀደም።በሕገ-ወጥ መንገድ ኦስትሪያ ከተያዛቸው ሊያስሯችሁ ወይም ወደ ሀገራችሁ ሊመልሷችሁ ይችላሉ፤ ስለዚህ ተጠንቀቁ ! ለጥገኝነት ካመለከታችሁ ከ3 ወር በኋላ ሥራ የሚስጣችሁ ሰው ብታገኙ ይህ ሰው ለናንተ የሥራ ፈቃድ(Beschäftigungsbewilligung) ማመልከት ይችላል።

ጥገኝነት ከተሰጠኝ ምን ይሆናል?
ጥገኝነት ወይም ተጨማሪ ጥበቃ ከተሰጣችሁ ሥራ መስራት ትችላላችሁ። በመንግስት የስራ ማዕከል መመዝገብ አለባችሁ። ማዕከሉ የጀርመንኛ ቋንቋ ትምህርት ሊሰጣችሁ ይችላል። እነሱ ስራ ይፈልጉላችኋል ነገር ግን እናንተም በራሳችሁ ስራ ልትፈልጉ ትችላላችሁ። ኦስትሪያ ውስጥ ስራ ፈልጐ ማግኘት ከባድ ሊሆን ይችላል። ብዙ የሥራ ቦታዎች ጥሩ የጀርመንኛ ቋንቋ ክህሎት ይጠይቃሉ፤ አንዳንድ ሰዎች ደግሞ ስደተኛ አይቀጥሩም።

ቤተሰቦቼን ማምጣት እችላለሁ?
አንድ የቤተሰብ አባል ጥገኝነት ወይም ጥበቃ ካገኘ ሌሎቹም የቤተሰቡ አባላት ሊያገኙ ይገባል (ኦስትሪያ ውስጥ ምንም ዓይነት የወንጀል ክስ ከሌለባቸው)። የቤተሰባችሁ አባል የሆነ ሰው በኦስትሪያ ጥገኝነት ወይም ጥበቃ ከተሰጠው ኦስትሪያ መግቢያ ቪዛ ለማግኘት በትውልድ ሀገራችሁ ማመልከት የምትችሉ ሲሆን የሚመለከታቸው ባለሥልጣናት ማመልከቻችሁን ይገመግማሉ።ቪዛው የሚያገልግለው ለ4 ወር ነው። እንደ ቤተሰብ አባል የሚቆጠሩ ሰዎች ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች ወላጆች፣ ከሌላ ባል ወይም ሚስት የተወለዱ እና 18 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች ናቸው። የትዳር ጥንዶች በትውልድ አገራቸው መጋባት አለባቸው ካልሆነ ግን በሌላ ሕግ የሚታይ ይሆናል።

ጥገኝነት ካልተሰጠኝ ወይም ከሀገር እንደወጣ ቢወሰንስ ?
ከሀገር እንድትለቁ ከተወሰነ እና እስር ቤት (Schubhaft) ከገባችሁ ለጠበቃ ወይም ለጓደኛ መደወል ትችላላችሁ። ወደ ሀገራችሁ ሊመልሷችሁ ቀጠሮ ከሰጧችሁ ወዲያውኑ ለጠበቃችሁ ወይም ጓደኞቻችሁ አሳውቁ ! ፖሊስ በፍጥነት ሊያስወጣችሁ ካሰበ (ውሳኔው በተወሰነበት ቀን ወይም በሚቀጥለው ቀን) እና በቁጥጥር ስር ከሆናችሁ ለጠበቃችሁ እንድትድውሉ ምናልባት ላይፈቀድላችሁ ይችላል። በምትመለሱበት የትውልድ ሀገራችሁ የሚያስድዷችሁ ከሆነ ወይም ኢሰብዓዊ ቅጣት የሞት ቅጣት ወይም ስቃይ የሚደርስባችሁ ከሆነ ግን ከሀገር ማስወጣት አይፈቀድም። በውሳኔው ላይ አቤቱታ ማቅረብ ትችላላችሁ።  (ሀገር ለቆ የመውጣት ውሳኔ በተራዘመ ቁጥር የቆይታ ጊዜው አንድ ዓመት ነው)። ይህ መሆኑ ግን ፖሊስ ጓዳዩን እርግፍ አድርጐ ይተወዋል የሚል ዋስትና አይስጥም።

የማቆያ ሂደት እና መብቶች
ሀገር ለቃችሁ እንድትወጡ ትዕዛዝ ከተላለፈባችሁ እና ይህን ካልፈፀማችሁ እስከሚያስወጧችሁ ድረስ በእስር ቤት ልትቆዩ ትችላላችሁ። ሊያስወጧችሁ ከፈለጉ የወረቀት ሁኔታችሁን በሚያጠኑበት ጊዜ ወስደው ሊያስሯችሁ ይችላሉ። እስራቱ ለረጅም ጊዜ ሊሆን አይገባም ነገር ግን በ18 ወራት ውስጥ ለ10 ወራት ልትታሰሩ ትችላላችሁ። በታሰራችሁበት ወቅት በሙሉ እና ከዚያ በኋላ ባለው 6 ሳምንት ውስጥ የመቃወም እና አቤት የማለት መብት አላችሁ።

የቤተሰብ እና ልጆች እስራት
ቤተሰብ የሆኑ ሰዎች የሚታሰሩበት ማዕከል ከቪዬና ውጭ ይገኛል። ቤተሰብ የሆኑ ሰዎች ሊታሰሩ የሚችሉት ሀገር ለቀው ከመውጣታቸው በፊት ቢበዛ ለ48 ሰዓታት ነው። በኦስትሪያ የሚገኙ የእስር ማዕከላት ውስጥ ያለው የሕክምና አገልግሎት እና የሕግ ድጋፍ አገልግሎት እጥረት በተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን ተተችቷል። የኦስትሪያ የእስራት/የማቆየት ፖሊሲ ከሌሎች አውሮፓ ሕብረት አባል ሀገሮች ጋር ሲነፃፀር በጣም ሰፊ ነው።

ከታሰርኩስ?
ኦስትሪያ ውስጥ የታሰረ ሰው ለምን እንደታሰረ ሙሉ በሙሉ በሚረዳው ቋንቋ እንዲነገረው መብት አለው። እናንተ ከጠየቃችኋቸው መታሰራችሁን ለጓደኛ ወይም ጠበቃ የመንገር ጊዴታ አለባቸው። መታሰራችሁን በትውልድ ሀገራችሁ ለሚገኘው ኤምባሲ ወይም ቆንሱል ጽህፈት ቤት ሪፖርት ማድረግ አለበት።

ያለመኖሪያ ፈቃድ እንዴት መኖር እችላለሁ?
የጥገኝነት ጥያቄያቸው ውድቅ የሆነባቸው ስደተኞች መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች በሚተዳደሩ መጠለያዎች ዉስጥ ለአጭር ጊዜ መቆየት ይችላሉ። የመሬት ከበርቴዎች ሠራተኞቻቸው የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማረጋገጥ አለባቸው። ነገር ግን ወረቀት ለሌላቸው ሰዎች ቤት የሚያከራዩ አያሌ ማህበራት አሉ። ወረቀት የሌላቸው ሰዎች የጤና ኢንሹራንስ የማግኘት መብት የላቸዉም። የድንገተኛ አደጋ ጊዜ አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ፤ ነገር ግን ወጪውን በራሳቸው መክፈል ይጠበቅባቸዋል። በአጠቃላይ በኦስትሪያ የጤና እንክብካቤ አገልግሎት ማግኘት ከባድ ነው፤ በተለይ ከትላልቅ ከተሞች ውጭ እና በእስር ማዕከላት ዉስጥ።

ማን ሊረዳ ይችላል?
ሥራ በተመለከተ :-
አንዶክ ተብሎ የሚጠራ ወረቀት የሌላቸው ሰዎችን የሚረዳ የንግድ ማህበር ምክር ማዕከል አለ። ወረቀት ለሌላቸው ሰዎች በተለያዩ ቋንቋዎች የምክር አገልግሎት ያቀርባል።
አድራሻ:- ÖGB (Catamaran)
Lift D, 1. Stock, Raum 1913
Johann-Böhm-Platz (ዮሃንበህም አደባባይ) 1
1020 Wien (ቪዬና ከተማ)
ድረ-ገፅ :- http://www.undok.at

የሕግ-ነክ እርዳታ :-
Asyl in Not (የሕግ ምክር አገልግሎት የሚሰጠው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት),
Währinger Straße (ቬሪንገር ስትራብ) 59/2/1,
1090 Wien (ቪና ከተማ)
ስልክ :- 01/408 42 10
ኢሜል :- office@asyl-in-not.org

Deserteurs- und Flüchtlingsberatung (የጥገኝነት ጥያቄያቸው ውድቅ ለሆነባቸው ሰዎች እንዴት አቤቱታ ማቅረብ እንዳለባቸው ድጋፍ ይሰጣል።የጀርመንኛ ቋንቋ ትምህርት እና ካውንስሊንግ አገልግሎትም ይሰጣል።)
Schottengasse 3a/1/59,
1010 Wien (ቪዬና ከተማ), Austria
ስልክ :- + 43/1/533.72.71
ኢሜል: deserteursberatung@utanet.at
ድረ-ገፅ :- http://www.deserteursberatung.at

Caritas Flüchtlings- und Migrantenberatung (ለመመለስ ልዩ አገልግሎት ይሰጣል። የሕግ አገልግሎት እና የማማከር አገልግሎት እርዳታ የጥገኝነት ጥያቄያቸው ውድቅ ለሆነባቸው ሰዎች ያቀርባል።
አድራሻ :- Keplerstrasse (ክለፐር ስትራሰ) 82,
8020 Graz (ግራዝ), Austria,
ስልክ :- + 43/316/8015-0,
ኢሜል:-office@caritasgraz.at
ድረ-ገፅ :- http://www.caritas-graz.at

Zebra (ዜብራ የሚባል ድርጅት ለሕግ ነክ ጥያቄዎች፣ የቤት ጉዳይ እና የሕክምና አገልግሎትን በተመለከተ መረጃ እና የምክር አገልግሎት ይሰጣል።)
አድራሻ :- Granatengasse 4/III,
8020 Graz,
ስልክ :- +43/ 316/ 83 56 30 – 0
ኢሜል:-office@zebra.or.at

ጤና :- ወረቀት ወይም ኢንሹራንስ ለሌላቸው ሰዎች በነፃ የሚሰጥ የሕምክና አገልግሎት)
Krankenhaus der Barmherzigen Brüder
አድራሻ :- Grofle Mohrengasse 9 (ሞህረንጋስ)
1020 Vienna ( በቪዬና ከተማ)
ስልክ :- 0043 (0)1 – 21 121-0
ድረ-ገፅ :- http://www.barmherzige-brueder.at/

MAIZ (ሆስፒታል አይደለም ነገር ግን የት መሄድ እንዳለባችሁ ይነግሯችኋል።)
አድራሻ :- Hofgasse 11,
4020 Linz (ሊንዝ ከተማ)
ስልክ:- 0043 (0)732 – 77 60 70,
ድረ-ገፅ :- http://maiz.at

በግራዝ ከተማ: Marienambulanz (ማሪዬንአምቡላንዝ)
አድራሻ :- Keplerstrafle 82/1, 8020 Graz,
ስልክ :-  0043 (0)316/8015 361
ድረገፅ :- http://www.caritas-steiermark.at/hilfe-einrichtungen/fuer-menschen-innot/gesundheit/marienambulanz/

በቪዬና ከተማ : የጤና እንክብካቤ፣ የቤት እና የልብስ እርዳታ: Verein Ute Bock
A-1020 Wien: Grofle Sperlgasse 4
ስልክ :- 0043 (0)1 929 24 24 – 24 ,
ድረ-ገፅ :- http://www.fraubock.at
“Verein Menschenrechte Österreich” በካምፕ ውስጥ የሚሰራና ከመንግሥት ጋር ጥብቅ ግንኙነት ያለው ነገር ግን ጥገኝነት እንድታገኙ የመርዳት ዝንባሌ የለውም።

Diakonie (ዲያኮኒ)
የስራ ሰዓት ዘወትር ማክሰኞ እና ሐሙስ ከጧቱ 3 ሰዓት እስከቀኑ 10 ሰዓት (የመመዝገቢያ ሰዓት ከ3 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት)
አድራሻ :- Josef-Ferschner-Str. 20/II (ዦዜፍ-ፈርሽነርሽትራሰ)
2514 Traiskirchen (በትራይኪርሸን ከተማ ከባቡር ጣቢያው ባሻገር የሚገኝ)
ስልክ :-  0043-(0)2252 / 547 26

Volkshilfe Oberösterreich (የህዝብ እርዳታ በኦስትሪያ)- Volkshilfe Fluchtlings- & MigrantInnenbetreuung
አድራሻ በሊንዝ ከተማ:- Stockhofstrafle 40, 4020 Linz,
ስልክ :- 0043-(0)732/603099

Fluchtpunkt (ፍሉሽፑክት – ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ያላገኙ እና በአስቸጋሪ የሕግ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ ስደተኞች የምክር አገልግሎት የሚሰጥ።)
አድራሻ በኢንስብሩክ ከተማ:- A-6020 INNSBRUCK, Jahnstrasse 17 (ዣንሽትራስ የቤት ቁጥር 17)
ድረ-ገፅ :- http://www.fluchtpunkt.org/
ስልክ :- +43.512.581488